diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/01.md b/src/am/ss/2025-01/01/01.md new file mode 100644 index 0000000000..e41f443360 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/01.md @@ -0,0 +1,15 @@ +--- +title: እግዚአብሔር እንዲሁ ይወዳል +date: 28/12/2025 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ዘጸ. 33:15–22፤ ሆሴዕ 14:1-4፤ ራእይ 4:11፤ ዮሐንስ 17:24፤ ማቴ. 22:1–14፤ ዮሐንስ 10:17፣ 18 + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “ቁጣዬ ከእርሱ ዘንድ ተመልሶአልና ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፣ በገዛ ፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ” ሆሴዕ 14፡4 + +ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ጴጥሮስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ ቢክደውም፣ (ማቴ. 26፡34) ክህደቶቹ ግን የታሪኩ መጨረሻ አልነበሩም። ከትንሣኤ በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው። ደግሞ ሁለተኛ፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ፡- የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፡- ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፡ - በጎቼን አሰማራ አለው” (ዮሐንስ 21፡15–17)። ጴጥሮስ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ እንደካደው ሁሉ፣ ኢየሱስም “ትወደኛለህን?” በሚለው ወሳኝ ጥያቄ አማካኝነት ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ የራሱ አድርጎታል። ምንም እንኳን እኛ ያለንበት ሁኔታ ከጴጥሮስ የተለየ ቢሆንም፣ መርሆው ግን በብዙ መልኩ ተመሳሳይ ነው። ኢየሱስ ጴጥሮስን የጠየቀውን ጥያቄ፣ እግዚአብሔር በእኛ ዘመንና በምንኖርበት ቦታ ለእያንዳንዳችን የሚያቀርበው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡ - ትወደኛለህን? + + +_ሁሉም ነገር ለዚህ ጥያቄ በምንሰጠው ምላሽ ላይ የተመረኮዘ ነው። የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/02.md b/src/am/ss/2025-01/01/02.md new file mode 100644 index 0000000000..0e083748f2 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/02.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ከምንገምተው በላይ +date: 29/12/2025 +--- + +እግዚአብሔር እኛን "ትወደኛለህን" ብሎ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ራሱ እያንዳንዱን ሰው እንዲሁ ይወዳል። በእርግጥ እርሱ ልትገምተው ከምትችለው በላይ አንተን እንዲሁ ይወድሃል። ይህንን ፍቅር በዘመናት ሁሉ ለሕዝቡ ባደረገው ድርጊት እናውቃለን። + +`ዘጸ. 33፡15–22ን ያንብቡና የጥቅሶቹን አውድ እና የተገለጹበትን ሁኔታ ያስቡ። ይህ ክፍል በተለይም ቁጥር 19 ስለ እግዚአብሔር ፈቃድና ፍቅር ምን ይገልጻል?` + + +ሁሉም ነገር ያበቃለት ይመስል ነበር። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ባርነት በድንቅ ሁኔታ ነፃ ካወጣ በኋላ፣ ብዙም ሳይቆይ እሥራኤላውያን በእግዚአብሔር ላይ ዓምፀው የወርቅ ጥጃ አመለኩ። ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ፣ ያደረጉትን አየና አሥርቱን ትእዛዛት የያዙትን ጽላቶች ጥሎ ሰበራቸው። ምንም እንኳን ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዲሁ የሰጣቸውን የቃል ኪዳኑን ዕድሎች እና በረከቶች የማግኘት መብታቸውን ቢያጡም፣ ምንም እንኳን የኪዳኑ በረከቶች የማይገባቸው ቢሆንም፣ እግዚአብሔር በኪዳኑ ከእነርሱ ጋር ለመቀጠል እንዲሁ መረጠ። + +በዘፀአት 33፡19 ላይ፡- “ይቅር የምለውን ይቅር እላለሁ፣ የምምረውንም እምራለሁ” የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ እግዚአብሔር በዘፈቀደ ለአንዳንዶች ሩኅሩኅና መሃሪ፣ ለሌሎች ግን እንዳልሆነ ተደርጎ ይስተዋላል። ነገር ግን እንደ አውዱ ከሆነ፣ እግዚአብሔር አንዳንዶችን ይቅር ብሎ እንደሚምር እና ሌሎችን ግን ችላ እንደሚል እየተናገረ አይደለም። እግዚአብሔርም የሚሠራው በዚህ መልኩ አይደለም፤ እንዲያውም እግዚአብሔር አንዳንዶቹን እንዲጠፉና ለዘለዓለም እንዲኮነኑ አስቀድሞ ወስኗል የሚለውን የተሳሳተ ግን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን የሥነ-መለኮት አስተምሮ ይቃወማል። + +ታዲያ እግዚአብሔር እዚህ ላይ ምን እያለ ነው? እግዚአብሔር የሁሉ ፈጣሪ ስለሆነ፣ ለማይገባቸው ሰዎች እንኳን ፣ ጸጋን እና ርኅራኄን እንዲሁ የመስጠት መብትና ሥልጣን እንዳለው እያወጀ ነው። የወርቅ ጥጃ በማምለክ ቢያምፁም፣ ምንም እንኳን የማይገባቸው ቢሆኑም፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ለሕዝቡ ለእሥራኤል መሃሪ መሆኑን ያሳያል። + +`ይህ እግዚአብሔር ፍቅሩን ከምንገምተው በላይ ከገለፀባቸው ከብዙ አጋጣሚዎች አንዱ ነው። ለሁላችንም መልካም ዜና አይደል? እግዚአብሔር ለአንተ ከምትገምተው በላይ ፍቅሩን አየገለጸ ያለው በምን በምን መንገዶች ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/03.md b/src/am/ss/2025-01/01/03.md new file mode 100644 index 0000000000..2d09120949 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/03.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: ምላሽ የተነፈገው ፍቅር +date: 30/12/2025 +--- + +እግዚአብሔር ለወደቀው የሰው ዘር ያለውን አስገራሚ ፍቅር በሆሴዕ ታሪክ ውስጥ እናገኛለን። እግዚአብሔር ነቢዩን ሆሴዕን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና ሂድ፤ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው” (ሆሴ. 1፡2):: ሆሴዕ እና ታማኝ ያልሆነችው ሚስቱ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ላልሆኑትና በመንፈሳዊ ግልሙትና ለተዘፈቁት እሥራኤላውያን ያለውን ፍቅር የሚያሳዩ ሕያው ምስክሮች መሆን ነበረባቸው። ይህም ለማይገባቸው ሰዎች እንዲሁ የተበረከተው የእግዚአብሔር ፍቅር ታሪክ ነው። + +እግዚአብሔር ታማኝ እና አፍቃሪ ቢሆንም፣ ሕዝቡ በእርሱ ላይ ደግመው ደጋግመው አመፁበት። ስለዚህ ቃሉ እግዚአብሔርን፣ በተደጋጋሚ ታማኝ ያልሆነችውን የባለቤቱን ፍቅር ምላሽ የማይጠብቅ አፍቃሪ አድርጎ ይመስለዋል። እርሱ ሕዝቡን በፍፁም ታማኝነት ወደዳቸው፤ እነርሱ ግን ንቀውት ሌሎች አማልክትን በማገልገልና በማምለክ እጅግ አሳዘኑት፤ ሊጠገን የማይችል እስኪመስል ድረስ ኪዳኑን አፈረሱ። + +`ሆሴዕ 14:1–4ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ለሕዝቡ ስላለው ጽኑ ፍቅር ምን ይገልፃሉ?` + +ሕዝቡ በተደጋጋሚ ካመፁም በኋላ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- “ዓመፃቸውን እፈውሳለሁ፣ በገዛ ፈቃዴም እወድዳቸዋለሁ።” “በገዛ ፈቃዴም እወድዳቸዋለሁ” በሚለው ሐረግ ውስጥ የሚገኘው “በፈቃዴ” የሚለው ቃል የተተረጎመው ነዳባ ከሚባለው የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን በፈቃደኝነት የተለገሰን ነገር ያመለክታል። በመቅደስ አገልግሎት ውስጥ በገዛ ፈቃድ የሚሰጥ ስጦታን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለው ተመሳሳይ ቃል ነው። + +በሆሴዕ እና በሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው አስደናቂ ታማኝነትና ርኅራኄ ይታያል። ምንም እንኳን ደጋግመው ሌሎች አፍቃሪዎችን ቢከተሉም፣ ሊጠገን የማይችል እስኪመስል ድረስ የቃል ኪዳኑን ግንኙነት ቢያፈርሱም፣ እግዚአብሔር በገዛ ፈቃዱ ፍቅሩን በነሱ ላይ ማፍሰሱን ቀጠለ። ሕዝቡ የእግዚአብሔር ፍቅር አይገባቸውም ነበር፤ እንዲያውም ፍቅሩን ንቀውት መብታቸውን አጥተው ነበር። ቢሆንም እግዚአብሔር ማንም ሳያስገድደው ፍቅሩን መለገሱን ቀጠለ። ቃሉ የእግዚአብሔርን ፍቅር ነፃ እና በፈቃዱ የሚሰጥ መሆኑን ያሳያል። + +`ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ሩቅ፣ ጨካኝ ገዥ እና ዳኛ አድርገው ያስቡታል። እግዚአብሔር ታማኝ ባልሆነች ባለቤቱ ምላሽ እንደተነፈገው አፍቃሪ በመሆኑ የተናቀና የሚያዝን እንደሆነ መመሰሉ እግዚአብሔርን በተለየ መንገድ እንዲያዩት የሚረዳዎ እንዴት ነው? ከአምላክ ጋር ያለዎትን ግንኙነት የሚያዩበትን መንገድ እንዴት ይለውጠዋል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/04.md b/src/am/ss/2025-01/01/04.md new file mode 100644 index 0000000000..3853b28acf --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/04.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: በነጻ የተሰጠ ፍቅር +date: 31/12/2025 +--- + +እግዚአብሔር ፍቅሩን ያለማቋረጥ እንዲሁ የለገሰው በተደጋጋሚ ለሚያምፀው ለእሥራኤል ብቻ ሳይሆን፣ ለእኛም ገና ኃጢአተኞች ሳለን እንዲሁ በነፃ ፍቅሩን መስጠቱን ቀጥሏል። የእግዚአብሔር ፍቅር በጭራሽ አይገባንም፤ በሥራም ልናገኘው አንችልም። እግዚአብሔር ከኛ ምንም አይፈልግም (ሐዋ. 17፡ 25)። እግዚአብሔር ለኛ ያለው ፍቅር በራሱ በጎ ፈቃድ የተመሰረተ ነው። ራእይ 4:11ን ከመዝሙር 33:6 ጋር ያነፃፅሩ። `እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ፍጥረትን እንደፈለገው ስለ መፍጠሩ ምን ይነግሩናል?` + +እግዚአብሔር ይህንን ዓለም በፈቃዱ ፈጠረው። በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ክብር፣ ውዳሴና ኃይል ሁሉ ይገባዋል። እግዚአብሔር የትኛውንም ዓለም መፍጠር አያስፈልገውም ነበር። ዓለም ገና ሳይፈጠር፣ እግዚአብሔር በሥላሴ (በመለኮት) መካከል በነበረው የፍቅር ግንኙነት ይደሰት ነበር። + +`ዮሐንስ 17:24ን ያንብቡ። ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ስለነበረው የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ይነግረናል?` + +እግዚአብሔር ለፍቅሩ መገለጫ ፍጡራን አያስፈልጉትም ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ባሕርይው ፍቅር ስለሆነ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ለመፍጠር እና ከፍጡራን ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዲኖረው መረጠ። + +እግዚአብሔር ይህን ዓለም በፈቃዱ የፈጠረው ፍቅሩን አብዝቶ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በኤደን በኃጢአት ከወደቁ በኋላም ሆነ በግል ኃጢአት ከሠራን በኋላም እግዚአብሔር ሰዎችን እንዲሁ በነፃ መውደዱን ቀጥሏል። + +አዳምና ሔዋን በኤደን ከወደቁ በኋላ፣ በሕይወት መኖር እና የእግዚአብሔርን ፍቅር የመቀበል መብት አልነበራቸውም። ነገር ግን "ሁሉን በስልጣኑ ቃል" የሚደግፈው እግዚአብሔር (ዕብ. 1:3)፣ ከታላቅ ፍቅሩ፣ ምህረቱና ጸጋው የተነሳ በሕይወት እንዲኖሩና የሰው ዘርም ከራሱ ጋር የሚታረቅበትን መንገድ አዘጋጀ። ያ እርቅ እኛንም ያካትታል። + +`አለማችን የወደቀና ክፉ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ፍቅሩን መለገስ መቀጠሉ ስለ ፍቅሩና ባሕርይው ምን ይነግረናል? ይህ እውነት በምላሹ እሱን እንድንወደው ሊያደርገን የሚገባው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/05.md b/src/am/ss/2025-01/01/05.md new file mode 100644 index 0000000000..72dc7bf6f3 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/05.md @@ -0,0 +1,19 @@ +--- +title: የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው +date: 01/01/2026 +--- + +`እግዚአብሔር ሰዎችን በገዛ ፈቃዱ ስለሚወዳቸው፣ በምላሹም እንዲወዱት ይጋብዛቸዋል። እግዚአብሔር ለሰዎች ፍቅሩን ለመቀበል ወይም ላላመቀበል የምርጫ ነፃነት እንደሰጣቸው፣ ክርስቶስ ስለ ሠርግ ግብዣ በተናገረው ምሳሌ ላይ በግልጽ ይታያል። ማቴዎስ 22:1-14ን ያንብቡ። የዚህ ምሳሌ ትርጉም ምንድን ነው?` + + +ክርስቶስ ስለ ሰርጉ ግብዣ በተናገረው ምሳሌ ላይ፣ አንድ ንጉሥ ለልጁ ሰርግ አዘጋጅቶ አገልጋዮቹን “ወደ ሰርጉ የታደሙትን እንዲጠሩ” ይልካቸዋል። + +ነገር ግን የታደሙት "ሊመጡ አልወደዱም" (ማቴ. 22:2, 3)። ንጉሡ ከአንድ ጊዜ በላይ የታደሙትን እንዲጠሩዋቸው ባሮቹን ላከ፣ እነርሱ ግን ጥሪውን ችላ አሉ፣ ይባስ ብለውም ባሪያዎቹን ይዘው ገደሏቸው (ማቴ. 22፡4-6)። + +ንጉሡ አገልጋዮቹን የገደሉትን ከቀጣ በኋላ፣ ሌሎች አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው:- “ሰርጉስ ተዘጋጅቷል፣ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤ እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ” (ማቴ. 22:8, 9)። የሰርግ ልብስ ያልለበሰው ሰው ወደ ውጭ ከተጣለ በኋላ፣ በሰርጉ ግብዣ ለመታደም የሰርግ ልብስ ከንጉሱ መቀበል አስፈላጊ መሆኑን አመልክቶ፣ ምሳሌውን “የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ. 22፡14) የሚለውን ትልቅ ትርጉም ያለውን ሐረግ በመናገር ይቋጨዋል ። + +`ይህ ምን ማለት ነው? በመጨረሻ “የተመረጡት” የጌታን የሰርግ ግብዣ ጥሪ በፈቃዳቸው የተቀበሉ ናቸው ማለት ነው።` + +በርግጥ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ወደ ሰርጉ ድግስ ይጠራል ። ሆኖም ማናችንም ብንሆን የእግዚአብሔርን ፍቅር እምቢ ልንል እንችላለን። የምርጫ ነፃነት ለፍቅር አስፈላጊ ነው። እግዚአብሔር ፍቅሩን እንድንቀበል ማናችንንም በፍጹም አያስገድድም። የሚያሳዝነው ግን ከእግዚአብሔር ጋር የፍቅር ግንኙነት እዳይኖረን መቃወም እንችላለን። + +`“የተመረጡት” ግብዣውን የሚቀበሉ ናቸው። እግዚአብሔርን ለሚወዱት፣ እኛ ልንገምተው ከምንችለው በላይ፣ አስደናቂ ነገሮችን እግዚአብሔር አዘጋጅቷል። ሁሉም የሚንጠለጠለው በፍቅር እና በፍቅር ውስጥ ባለው የምርጫ ነፃነት ላይ ነው። የሰርጉን ግብዣ መቀበልህንና በአግባቡ መልበስህን ሕይወትህ ያሳያል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/06.md b/src/am/ss/2025-01/01/06.md new file mode 100644 index 0000000000..d525327936 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/06.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ስለኛ ተሰቀለ +date: 02/01/2026 +--- + +እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ከእርሱ ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዲኖረው ይጋብዛል፣ ነገር ግን ግብዣውን በፈቃዳቸው የሚቀበሉት ብቻ ዘላለማዊ ደስታን ያገኛሉ። በሠርጉ ግብዣ ምሳሌ እንደታየው፣ ንጉሡ የጠራቸው ብዙዎቹ "ለመምጣት ፈቃደኛ አልነበሩም" (ማቴ. 22: 3)። + +ክርስቶስ ከመስቀሉ ጥቂት ቀደም ብሎ እንዲህ ሲል በሀዘን ተናገረ:- “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፣ ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም” (ማቴ. 23፡37)። + +ክርስቶስ በጉያው ሊሰበስባቸው ፈለገ፣ እነርሱ ግን ፈቃደኛ አልነበሩም። ቴሎ የሚባለው ተመሳሳይ የግሪክ ግስ ክርስቶስ እነርሱን ለማዳን መፈለጉን እና እነሱ ግን ለመዳን ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ቃል በማቴ. 22፡3 ላይም ይገኛል። + +`ሆኖም ክርስቶስ ወደ መስቀል የሄደው ለእነዚህ ሰዎች እና ለእኛ ሲል ነው።` + +`አስደናቂ ፍቅር! በኃጢአት ምክንያት ሰው ሞት የሚገባው ሆኖ ሳለ፣ እግዚአብሔር ራሱ (በክርስቶስ) ዋጋ ከፍሎ በሰማይና በምድር መካከል የተቋረጠውን ግንኙነት ለማደስ መንገድን አዘጋጀ። ምንም እንኳን ከርሱ ነፃ ቁርጠኝነት ውጭ ምንም ግዴታ ባይኖርበትም፣ አሁንም ፍቅሩን በኛ ላይ ማፍሰሱን ቀጥሏል። ዮሐ. 10:17፣ 18ን ያንብቡ። ከገላ. 2:20 ጋር ያስተያዩ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእኛ ያለው መልእክት ምንድን ነው?` + +የእግዚአብሔር ፍቅር በአስደናቂ ሁኔታ በታየበት በመስቀሉ፣ ክርስቶስ በራሱ ፍቃድ ለእኛ ሲል ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ እናያለን። ክርስቶስ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠን “በራሱ ተነሳሽነት” ነው። ማንም ሕይወቱን ከእርሱ አልወሰደበትም፣ አለም ሳይፈጠር በፊት በሰማይ በተዘጋጀው የደህንነት እቅድ መሠረት ራሱን በፈቃዱ አቀረበ። + +“የእኛ የደህንነት እቅድ ከአዳም ውድቀት በኋላ የተነደፈ አልነበረም። + +ይልቅስ ‘ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው‘ ምስጢር ተገለጠ (ሮሜ 16፡25)። ከዘመናት በፊት የእግዚአብሔር ዙፋን መሠረት የሆነው መርህ ተዘረጋ። ገና ከጅምሩ እግዚአብሔር እና ክርስቶስ የሰይጣንን ክህደት እና በአታላዩ አማካኝነት የሰው ዘር እንደሚወድቅ ያውቁ ነበር። ኃጢአት እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፣ ነገር ግን የኃጢአትን መከሰት አስቀድሞ ተመለከተ፣ እናም አስፈሪውን አደጋ ለመቀልበስ ሁኔታዎችን አዘጋጀ። ለዓለማችን የነበረው ፍቅር ታላቅ ስለነበር፣ ‘በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ’ አንድያ ልጁን ለመስጠት ቃል ኪዳን ገባ (ዮሐ. 3፡16)።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 22. \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/07.md b/src/am/ss/2025-01/01/07.md new file mode 100644 index 0000000000..6e3dbf90b0 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/07.md @@ -0,0 +1,25 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 03/01/2026 +--- + +የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች ከሚለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ሙሽራውን ለመገናኘት” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 405–421 ያንብቡ። + +"ዓለምን የሸፈነው እግዚአብሔርን በተሳሳተ መንገድ የመረዳት ጨለማ ነው። ሰዎች ስለ ባሕሪይው ያላቸውን እውቀት እያጡ ነው። ባሕሪይው በተሳሳተ መንገድ ተስተውሏል፣ ተተርጉሟልም። በዚህ ዘመን የሚያበራ እና ተጽእኖና የማዳን ኃይል ያለው የእግዚአብሔር መልእክት ሊታወጅ ይገባል። ባሕሪይውም ሊታወቅ ያስፈልጋል። ወደ ጨለማው ዓለም የክብሩ፣ የመልካምነቱ፣ የምሕረቱ እና የእውነት ብርሃን መብራት ይኖርበታል። + +በነብዩ ኢሳያስ ሊሰራ የታቀደው እንዲህ ተገልጧል፡- “የምሥራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፥ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፤ የምሥራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፤ አንሺ፥ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፡- እነሆ፥ አምላካችሁ! ብለሽ ንገሪ። እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።’ ኢሳ. 40:9, 10 + +“የሙሽራውን መምጣት የሚጠባበቁት ‘እነሆ፥ አምላካችሁ!’ ብለው ለሰዎች መናገር አለባቸው። ለዓለም የሚሰበከው የመጨረሻው የምሕረት ብርሃን፣ የመጨረሻው የምሕረት መልእክት የእርሱን የፍቅር ባሕርይ መግለጥ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ክብሩን ሊገልጡ ይገባል። በሕይወታቸው እና በባሕርያቸው የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረገላቸውን መግለጥ አለባቸው። + +“የጽድቅ ፀሐይ ብርሃን በመልካም ሥራ - በእውነት ቃል እና በቅዱስ ምግባር - ሊያበራ ይገባል።”— ኤለን ጂ. ዋይት፣ የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 415, 416 + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + +`1. አምላክ የለም ከሚለው አስተሳሰብ የባሰው እግዚአብሔር ይጠላናል የሚለው አስተሳሰብ ነው። ይህ እውነት ቢሆን ኖሮ እኛ የምንኖርበት ዓለም ምን ያህል የተለየ ይሆን ነበር?` + +`2. ዛሬ በዓለማችን የእግዚአብሔርን ባሕርይ በተሳሰተ መንገድ የምንረዳው ለምን ይመስልዎታል? ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር በተሻለ መንገድ እንዲመለከቱ ልትረዷቸው የምትችሉባቸውን መንገዶች በማሰብ ተወያዩ።` + +`3. ዛሬ ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ሊታወጅ የሚገባው መልእክት ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ፍቅር እውነታ ላልተረዳ ሰው ይህንን መልእክት እንዴት ይገልጹታል? የፍቅሩንና የድንቅ ባሕርይውን እውነታ የሚያሳይ ምን ማስረጃ ሊጠቁሙ ይችላሉ?` + +`4. ስለ እግዚአብሔር ፍቅር መናገር አንድ ነገር ነው። ያንን ፍቅር በሕይወታችን መግለጥ እና ማንፀባረቅ ደግሞ ሌላ ነገር ነው። በዙሪያችን ላሉ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያሳዩ “የቅድስና ሥራዎች” ምን ሊሆኑ ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/01/info.yml b/src/am/ss/2025-01/01/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..397d82d430 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/01/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "እግዚአብሔር እንዲሁ ይወዳል" + start_date: "28/12/2025" + end_date: "03/01/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/01.md b/src/am/ss/2025-01/02/01.md new file mode 100644 index 0000000000..b5c2aa0ce5 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/01.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ኪዳናዊ ፍቅር +date: 04/01/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +2ጴጥ. 3:9፣ ዘዳ. 7፡6–9፣ ሮሜ. 11:22፣ 1 ዮሐ. 4:7-20፣ ዮሐ. 15:12፣ 1 ዮሐ. 3:16 + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> ኢየሱስም መለሰ አለውም:- የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን”ዮሐ. 14፡23 + +አጋፔ የሚለው የግሪክ ቃል ልዩ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደሚያመለክት፣ እንደ ፊልዮ ያሉት ሌሎች የፍቅር ቃላት ደግሞ ከአጋፔ ያነሱ የተለያዩ የፍቅር ዓይነቶችን እንደሚያመለክቱ ብዙዎች ተምረዋል። አንዳንዶች አጋፔ የአንድ ወገን ፍቅርን፣ የሚሰጥ ብቻ እንጂ የማይቀበል፣ በሰው ምላሽ የማይወሰን ፍቅርን ያመለክታል ይላሉ። + +ሆኖም በቃሉ ያለውን መለኮታዊ ፍቅር በጥንቃቄ ስናጠና፣ እነዚህ አመለካከቶች ምንም እንኳን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ ቢሆኑም የተሳሳቱ መሆናቸውን ያሳያል። በመጀመሪያ፣ አጋፔ የሚለው የግሪክ ቃል የእግዚአብሔርን ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ፍቅርን፣ አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ የሰው ፍቅርን ጭምር ያመለክታል (2ጢሞ. 4፡10)። ሁለተኛ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአጋፔ በተጨማሪ ሌላ ብዙ ቃላት የእግዚአብሔርን ፍቅር ያመለክታሉ። + +ለምሳሌ፣ ኢየሱስ ሲያስተምር “እናንት ስለወደዳችሁኝ [ፊሊዮ]፣ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋል [ፊሊዮ]” ይላል (ዮሐንስ 16፡27)። እዚህ ላይ ፊሌዮ የሚለው የግሪክ ቃል የሰውን ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅርም ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ስለዚህ ፊልዮ ጎደሎ የሆነውን የፍቅር ዓይነት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም ፍቅር ያመለክታል። + +በተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔር ፍቅር የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ግንኙነትን የሚጠይቅ እንደሆነ፣ ፍቅሩንም ለእርሱ እና ለሌሎች መልሰው ማንጸባረቅ ወይም አለማንፀባረቃቸው ለእግዚአብሔር ትልቅ ልዩነት እንዳለው ያስተምራሉ። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/02.md b/src/am/ss/2025-01/02/02.md new file mode 100644 index 0000000000..678dcdc9f6 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/02.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ፍቅር +date: 05/01/2026 +--- + +`ቃሉ ግልጽ ነው፡- እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ይወዳል። በጣም የታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ዮሐንስ 3፡16 ይህንን እውነት ያውጃል፡ - “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” መዝ. 33:5 እና መዝ. 145:9ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ፍቅር፣ ርኅራኄና ምሕረት ስፋት ምን ያስተምራሉ?` + +አንዳንዶች የማይወደዱ እንደሆኑ ሊሰማቸው ይችላል፣ ወይም ከነሱ በቀር እግዚአብሔር ሌላውን ሁሉ ይወዳል ብለው ያስቡ ይሆናል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር የተወደደ እንደሆነ ይናገራል። + +እርሱ የማይወደው ማንም የለም። እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ስለሚወድ፣ ሁሉም እንዲድኑ ይፈልጋል። + +`2 ጴጥ. 3:9ን፣ 1 ጢሞ. 2:4ን እና ሕዝ. 33:11ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ለማዳን ስላለው ፍላጎት ምን ያስተምራሉ?` + + +ከዮሐ. 3፡16 በኋላ ያለው ጥቅስ፡- “ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፣ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና” ይላል (ዮሐ. 3፡ 17)። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ (ፍላጎት) ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሁሉም ሰው ፍቅሩን ተቀብሎ ይድን ነበር። ሆኖም ጌታ ፍቅሩን እንዲቀበሉ ማንንም አያስገድድም። + +ሰዎች ሊቀበሉት ወይም ሊንቁት መብት አላቸው። + +`ምንም እንኳን አንዳንዶች ባይቀበሉትም፣ እግዚአብሔር እነርሱን መውደድ አያቆምም። በኤር. 31፡3 ላይ ለሕዝቡ፡- “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ በሌላ ስፍራ ደጋግሞ እንደሚያስተምረው የእግዚአብሔር ፍቅር ለዘላለም ይኖራል (ለምሳሌ መዝ. 136ን ይመልከቱ)። የእግዚአብሔር ፍቅር በጭራሽ አያልቅም። ዘላለማዊ ነው። ብዙ ጊዜ ሌሎችን አለመውደድ ስለሚቀልለን፣ ይህን እውነት መረዳት ይከብደናል፤ አይደለም እንዴ?` + +ነገር ግን፣ እኛ በግላችን የዚህን ፍቅር እውነታ ብንለማመደው— የእግዚአብሔርን ፍቅር በግላችን ብናውቀው —እንዴት ያለ የተለየ ህይዎት በኖርንና ሌሎችንም በተንከባከብን ነበር ። + +`እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው የሚወድ ከሆነ፣ ይህ ማለት አስጸያፊ ባሕርይ ያላቸውንም ይወዳል ማለት ነው። አምላክ ለእነዚህ ሰዎች ያለው ፍቅር እኛ ከእነርሱ ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት ምን ሊያስተምረን ይገባል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/03.md b/src/am/ss/2025-01/02/03.md new file mode 100644 index 0000000000..e3a3ba7d94 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/03.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: ኪዳናዊ ፍቅር +date: 06/01/2026 +--- + +`መጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ያለውን የተለየ የፍቅር ግንኙነት የሚገልጸው፣ በቤተሰብ ወይም በዝምድና በተለይም በባልና በሚስት ወይም መልካም እናት ለልጇ ያላትን ፍቅር የሚያሳዩ ዘይቤዎችን በመጠቀም ነው። እነዚህ ዘይቤዎች በተለይ በእግዚአብሔር እና በቃል ኪዳኑ ህዝቦች መካከል ያለውን የተለየ ግንኙነት ለማሳየት ያገለግላሉ። ይህ ግንኙነት ኪዳናዊ ፍቅር ነው፡- ይህም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች ይህን ፍቅር ተቀብለው በምላሹ እርሱን እና አንዱ ሌላውን እንዲወድ ይጠብቃል። ዘዳ. 7:6–9ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እና በእግዚአብሔር ፍቅር መካከል ስላለው ግንኙነት ምን ያስተምራሉ?` + +ዘዳ. 7፡9 እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ሕዝብ ያለውን የተለየ ፍቅር ይገልጻል፣ ግንኙነቱ በከፊል ታማኝ በመሆናቸው ወይም ባለመሆናቸው ላይ የተመሰረተ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በሁኔታዎች የተመሰረተ አይደለም፣ ነገር ግን ከሕዝቡ ጋር ያለው የቃል ኪዳን ግንኙነት በሁኔታዎች የተመሰረተ ነው። + +በዘዳ. 7፡9 ላይ “ርኅራኄ” ወይም “ምሕረት” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ኼሴድ ራሱ የመለኮታዊ ፍቅርን ኪዳናዊ ገጽታ ያሳያል። ኼሴድ ብዙ ጊዜ ታላቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምሕረት፣ መልካምነትና ፍቅር ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። በተለይ ኼሴድ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ አንዱ ለሌላው ወገን ያለውን ጽኑ ፍቅር ያመለክታል። ሌላውም ወገን በምላሹ ይህን ፍቅር እንዲያሳይ ግንኙነቱ ያነሳሳዋል። + +የእግዚአብሔር ኼሴድ ፍቅሩ እጅግ አስተማማኝ፣ ጽኑ እና ዘላለማዊ እንደሆነ ያሳያል። ሆኖም የኼሴድን በረከቶች መቀበል በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡- ሕዝቡ ለመታዘዝ እና ቃላቸውን ለመጠበቅ ባላቸው ፈቃደኝነት ማለት ነው (2 ሳሙ. 22:26፣ 1 ነገ. 8:23፣ መዝ. 25:10፣ መዝ. 32:10፣ 2 ዜና 6:14)። + +የእግዚአብሔር ጽኑ ፍቅር የሁሉም የፍቅር ግንኙነቶች መሠረት ነው፣ ያንን ፍቅርም በፍጹም ልንደርስበት አንችልም። እግዚአብሔር በሕይወት እንድንኖር ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ ስለ እኛ ራሱን በፈቃዱ ሰጠ። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" (ዮሐ. 15:13)። ትልቁ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠው ጌታ “ራሱን አዋርዶ፣ ለሞት ይኸውም ለመስቀል ሞት እንኳ በታዘዘ ጊዜ” (ፊልጵ. 2፡8) እንደሆነ ምንም አያጠያይቅም። + +`የእግዚአብሔርን ፍቅር እውነታ በሃሳብህ ውስጥ ያለማቋረጥ ማሰላሰል የምትችልባቸው መንገዶች ምንድን ናቸው? ይህን ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/04.md b/src/am/ss/2025-01/02/04.md new file mode 100644 index 0000000000..a011c21712 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/04.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: በሁኔታዎች የተመሠረተ ግንኙነት +date: 07/01/2026 +--- + +እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ከእርሱ ጋር የጠበቀ የፍቅር ግንኙነት እንዲኖረው ይጋብዛል (ማቴ. 22፡1–14ን ይመልከቱ)። ለዚህ ጥሪ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እግዚአብሔርን እና ሌሎችን እንድንወድ የተሰጠንን ትዕዛዝ መታዘዝን ያካትታል (ማቴ. 22፡37–39ን ይመልከቱ)። አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የቃል ኪዳኑን በረከቶች የሚያገኘው ይህንን ፍቅር ለመቀበል ወይም ላለመቀበል በሚያደርገው ውሳኔ ነው። + +`ሆሴ. 9:15ን፣ ኤር. 16:5ን፣ ሮሜ 11:22ን እና ይሁ. 21ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ከእግዚአብሔር ፍቅር የተነሳ የምናገኛቸውን በረከቶች ልናጣቸው እንደምንችል ምን ያስተምሩናል?` + + +በእነዚህ እና በሌሎች ጥቅሶች ተደጋግሞ እንደተገለፀው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ባለን የፍቅር ግንኙነት በረከቶቹን የምንለማመዳቸው ለፍቅሩ ምላሽ ስንሰጥ ብቻ ነው። ሆኖም አምላክ ሰውን መውደዱን ያቆማል ብለን በማሰብ ልንሳሳት አይገባም። እንዳየነው የእግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊ ነው። ምንም እንኳን ሆሴዕ 9፡15 ላይ እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር፡- “ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም’’ ቢልም፣ በኋላ ላይ በዚያው መጽሐፍ እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ “በፈቃዴ እወድዳቸዋለሁ’’ ብሎ እንደተናገረ ማስታወስ አስፈላጊ ነው (ሆሴ. 14:4)። ሆሴ. 9፡15 እግዚአብሔር ሕዝቡን መውደድ አቁሟል አይልም። + +ይልቁንም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የፍቅር ግንኙነት በረከት በሁኔታዎች ላይ የተመረኮዘ መሆኑን እያመለከተ ነው። ይህም ግንኙነት እንዲቀጥል ለፍቅሩ የምንሰጠው ምላሽ ወሳኝ ነው። + +"ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ” (ዮሐ. 14:21)። በተመሳሳይ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ፡- “እናንተ ስለወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋል” ብሏቸዋል (ዮሐንስ 16፡27)። + +እነዚህ እና ሌሎች ጥቅሶች የሚያስተምሩን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን የሚያድን ግንኙነት ምክንያት የምናገኛቸውን በረከቶች ማስቀጠል የምንችለው የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመቀበል ፈቃደኛ ስንሆን ነው። ይህ ደግሞ ፍቅሩን ለሌሎች ለማድረስ የሚገለገልብን ዕቃዎች መሆንን ይጨምራል። ይህ ማለት ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በምንም ሁኔታ ያቆማል ማለት አይደለም። + +ይልቅስ ፀሐይን እንዳታበራ ማድረግ እንደማንችል፣ ከጨረሮቿ ግን ራሳችንን መሰወር እንደምንችል ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ፍቅር ለማቆም ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፤ ሆኖም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ችላ ብለን የሚሰጠንን በረከት በተለይም የዘላለም ሕይወት ተስፋ ልናጣ እንችላለን። + +`ሰዎች ምላሽ ቢሰጡም ባይሰጡም፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እውነታ የሚያዩባቸው እና የሚለማመዱባቸው መንገዶች ምንድናቸው? ለምሳሌ፣ ከኃጢአት ውድቀት በኋላ እንኳን ተፈጥሮ ፍቅሩን እንዴት ይገልጣል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/05.md b/src/am/ss/2025-01/02/05.md new file mode 100644 index 0000000000..08c1af3bfa --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/05.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ችላ የተባለው ምሕረት +date: 08/01/2026 +--- + +የእግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊ እና ምንጊዜም ሳይገባን የተሰጠን ነው። + +ይሁን እንጂ ሰዎች ላይቀበሉት ይችላሉ። ምንም ሳናደርግ ፍጹምና ዘላለማዊ በሆነው ፍቅሩ አስቀድሞ እንዲሁ ስለወደደን ብቻ (ኤር. 31፡3)፣ ይህን ፍቅር ለመቀበልም ሆነ ችላ ለማለት እድሉ አለን። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር፣ አስቀድሞ ሳንጠይቅ ለተሰጠን ፍቅር ምላሽ ነው። + +`1 ዮሐ. 4:7–20ን በተለይ ቁጥር 7 እና 19 ያንብቡ። ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር ፍቅር ቅድሚያ ስለሚሰጠው ነገር ምን ይነግረናል?` + +ሁልጊዜ የሚቀድመው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ ባይወደን፣ መልሰን ልንወደው አንችልም ነበር። እግዚአብሔር ለመውደድም ሆነ ልንወደድ የምንችል አድርጎ ቢፈጥረንም፣ የፍቅር ሁሉ መሰረቱና ምንጩ ግን እግዚአብሔር ራሱ ነው። ሆኖም ልንቀበለውና በሕይወታችን ልናንጸባርቀው ምርጫ አለን። ይህ እውነት ክርስቶስ በተናገረው ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ባልሆነው አገልጋይ ምሳሌ ተገልጿል (ማቴ. 18፡23–35ን ይመልከቱ)። + +በምሳሌው ላይ አገልጋዩ የጌታውን ዕዳ የሚከፍልበት ምንም አይነት መንገድ እንዳልነበረ እናያለን። እንደ ማቴ. 18 አገልጋዩ ከጌታው የ10,000 መክሊት ዕዳ ነበረበት። አንድ መክሊት 6,000 ዲናር የሚያህል ነበር። አንድ ዲናር ደግሞ ለአንድ ተራ ሠራተኛ ለቀን ሥራ የሚከፈለው ነበር (ከማቴ. 20፡2 ጋር ያነፃፅሩ)። + +ስለዚህ አንድ መክሊት ለማግኘት አንድ ተራ ሰራተኛ ለ6,000 ቀናት የጉልበት ሥራ ይሰራል። የዕረፍት ቀናትን ሳይጨምር አንድ ተራ ሠራተኛ በዓመት 300 ቀናትን በመሥራት በዓመት 300 ዲናር ሊያገኝ ይችላል እንበል። ስለዚህ አንድ መክሊት ዕዳ ለመክፈል አንድ ተራ ሰራተኛ 20 ዓመት ገደማ ይፈጅበታል (6,000 ዲናር ÷ 300 = 20)። 10,000 መክሊት ለማግኘት አንድ ተራ ሠራተኛ በአማካይ 200,000 ዓመታት መሥራት ይኖርበታል። ባጭሩ አገልጋዩ ይህንን ዕዳ ፈጽሞ ሊከፍል አይችልም ነበር። ሆኖም ጌታው ለአገልጋዩ ስለ ራራለት ያለበትን ትልቅ ዕዳ እንዲሁ ተወለት። + +ይህ ምሕረት የተደረገለት አገልጋይ፣ ትንሿን የ100 ዲናር ዕዳ ለባልንጀራው ባለመተው ወደ እስር ቤት ሲያስገባው፣ ጌታው ተቆጥቶ ይቅርታውን አነሳ። + +አገልጋዩ የጌታውን ፍቅርና ይቅርታ አጣ። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ እና ምሕረት የማያልቁ ቢሆንም፣ ሰው በስተመጨረሻ በረከቶቹን ሊገፋቸው፣ እንዲያውም ሊያጣቸው ይችላል። + +`ይቅር የተባልከውን እና በኢየሱስ ይቅር ለመባል ምን ዋጋ እንደከፈልክ አስብ። ሌሎችን ይቅር ስለማለት ይህ ምን ሊነግርህ ይገባል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/06.md b/src/am/ss/2025-01/02/06.md new file mode 100644 index 0000000000..d2b1400724 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: በነጻ የተቀበላችሁትን በነጻ ስጡ +date: 09/01/2026 +--- + +አገልጋዩ የጌታውን ዕዳ በጭራሽ መክፈል እንደማይችል ሁሉ፣ እኛም ለእግዚአብሔር ምንም ልንከፍለው አንችልም። የእግዚአብሔርን ፍቅር በሥራችን ልናገኘው አንችልም። “ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ. 5፡8)። እንዴት ያለ አስደናቂ ፍቅር ነው! 1ኛ ዮሐ. 3፡1 “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ” ይላል። + +ልናደርግ የምንችለው እና ማድረግ ያለብን የአምላክን ፍቅር ለሌሎች ማሳየት ነው። እንዲህ ያለ ታላቅ ርኅራኄ እና ይቅርታ ከተቀበልን፣ እንዴት አብልጠን ለሌሎች ልንራራ እና ይቅርታ ልናደርግ ይገባናል? አገልጋዩ ለባልንጀራው አገልጋይ ምሕረት ስላላደረገለት፣ የጌታውን ርኅራኄና ይቅርታ ማጣቱን አስታውሱ። እግዚአብሔርን በእውነት የምንወደው ከሆነ፣ ፍቅሩን ለሌሎች ከማሳየት ወደ ኋላ አንልም። + +`ዮሐ. 15:12ን፣ 1 ዮሐ. 3:16ን፣ እና 1 ዮሐ. 4:7–12ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በእግዚአብሔር ፍቅር እና እኛ ለርሱ እና ለሌሎች ባለን ፍቅር መካከል ስላለው ግንኙነት ምን ያስተምሩናል?` + +ከዮሐ. 15፡12 በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ "እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ" ብሏቸዋል (ዮሐ 15፡14)። ኢየሱስ ምን አዟቸው ነበር? እርሱ እንደወደዳቸው ሌሎችን እንዲወዱ አዟቸው ነበር። ጌታ እዚህ እና ሌሎች ክፍሎች ላይ፣ እግዚአብሔርን እንድንወድ እና እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ያዘናል። + +ባጭሩ ልንገነዘበው የሚገባን ልንቆጥረው እና ፈጽሞ ልንከፍለው የማንችለው ዕዳ ይቅር ተብሎልናል። ይህም የሆነው በመስቀሉ ብቻ ነው። + +ስለዚህ እግዚአብሔርን ልንወደውና ልናመሰግነው፣ ከሌሎችም ጋር በፍቅር እና በጸጋ ልንኖር ይገባናል። ሉቃ. 7፡47 እንደሚያስተምረን ብዙ ይቅር የተባለለት ብዙ ይወዳል፣ ነገር ግን “ጥቂት የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።” ከመካከላችን ምን ያህል ይቅር እንደተባለ የማያስተውል ማን አለ? + +`እግዚአብሔርን መውደድ ሌሎችን መውደድን የሚያካትት ከሆነ፣ በቃልም ሆነ በድርጊት የእግዚአብሔርን የፍቅር መልእክት በአስቸኳይ ልናካፍል ይገባል። አሁኑኑ ሰዎችን በዕየለት ኑሯቸው መርዳት አለብን፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ቧንቧ በመሆን ሰዎችን በአዲስ ሰማይ እና በአዲስ ምድር የዘላለም ሕይወት ተስፋን ወደሚሰጣቸው ወደ እርሱ ልናመለክታቸው ይገባል - የእግዚአብሔርን ፍቅር እንቢ በማለት ከዚህ በኃጢአትና በሞት ፍሬ ከተበላሸው ዓለም ፍጹም የተለየ አዲስ ፍጥረት። ሌሎችን በመውደድ እግዚአብሔርን ለመውደድ ምን የተለየ እርምጃ መውሰድ ይችላሉ? ዛሬና በሚቀጥሉት ቀናት ለሰዎች የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማሳየትና የዘላለምን ሕይወት ተስፋ እነዲያጣጥሙ ለመጋበዝ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/07.md b/src/am/ss/2025-01/02/07.md new file mode 100644 index 0000000000..4f42dff209 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/07.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 10/01/2026 +--- + +ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ከሚለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “የፀሎት እድል” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 93–104 ያንብቡ። + +“ፍላጎቶቻችሁን፣ ደስታችሁን፣ ሀዘኖቻችሁን፣ ጭንቀታችሁን እና ፍርሃቶቻችሁን በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጡአቸው። እርሱን ሸክም አታበዙበትም፣ አታደክሙትምም። የራሳችሁን ፀጉር የሚቆጥረው ለልጆቹ ፍላጎት ደንታ ቢስ አይደለም። ‘ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና’ (ያዕ 5፡ 11)። የፍቅር ልቡ በሀዘናችን እና ሀዘናችንን በመናገራችን ይነካል። አእምሯችሁን ግራ የሚያጋባውን ነገር ሁሉ ወደ እርሱ ውሰዱት። ዓለማትን በእጁ ለያዘው እና ሁሉንም ጉዳዮች ለሚቆጣጠረው ለእርሱ፣ ሊሸከመው የማይችለው ምንም ነገር የለም። በምንም መልኩ ሰላማችንን የሚያውክ ማንኛውም ነገር፣ እርሱ የማያስተውለው ትንሽ ነገር አይደለም። በእኛ ተሞክሮ ውስጥ እርሱ የማያነበው ድቅድቅ ጨለማ የሆነ ምዕራፍ የለም፤ ሊፈታው የሚከብደው ግራ መጋባት የለም። የሰማዩ አባታችን የማይመለከተው ወይም ወዲያውኑ ፍላጎት የማያድርበት ከታታናሾቹ ባንዱ ላይ የሚመጣ ጥፋት፣ ነፍሳችንን የሚከብ ጭንቀት፣ የሚያበረታን ደስታ፣ ከከናፍራችን የሚወጣ ልባዊ ጸሎት አይኖርም። + +ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቁስላቸውንም ይጠግናል’ (መዝ. 147፡3)። በምድር ላይ የእርሱን ጥንቃቄ የሚጋራ እና የሚወደውን ልጁን የሰጣት ሌላ ነፍስ የሌለች እስኪመስል ድረስ፣ በእግዚአብሔር እና በእያንዳንዱ ነፍስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለየ እና ሙሉ ነው።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ፣ ገጽ 100. + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + +`1. “በምድር ላይ የእርሱን ጥንቃቄ የሚጋራ እና የሚወደውን ልጁን የሰጣት ሌላ ነፍስ የሌለች እስኪመስል ድረስ፣ በእግዚአብሔር እና በእያንዳንዱ ነፍስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለየ እና ሙሉ ነው” የሚለውን ከላይ ያለውን ዓረፍተ ነገር ያሰላስሉ። ይህ ምን አይነት መጽናናትን ይሰጥዎታል? እግዚአብሔር ለርሶ ቅርብ እና የሚጠነቀቅልዎት መሆኑን በማወቅ ሕይወትዎን እንዴት መኖር አለብዎት? በዚህ አስደናቂ ተስፋ መኖርን እንዴት መማር ይችላሉ? በየዕለቱ ይህን በእውነት በማመን ብኖረው ብለው ያስቡ።` + +`2. ከዚህ ሳምንት ትምህርት አንጻር መዝ. 103:17, 18ን እንዴት ይረዱታል? የእግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት የሚያስገኛቸው በረከቶች ፍቅሩን በመቀበላችን ላይ መመርኮዙን እንዴት ያሳያል?` + +`3. ይህን ማወቅዎ ከአምላክ ጋር ባለዎት ግንኙነት ላይ ለውጥ የሚያመጣው እንዴት ነው? የሌሎችን ሀዘን የሚያስቡበትን መንገድ እንዴት ይቀይረዋል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/02/info.yml b/src/am/ss/2025-01/02/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..540e68595c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/02/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "ኪዳናዊ ፍቅር" + start_date: "04/01/2026" + end_date: "10/01/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/01.md b/src/am/ss/2025-01/03/01.md new file mode 100644 index 0000000000..39056d50fd --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/01.md @@ -0,0 +1,19 @@ +--- +title: እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት +date: 11/01/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ሉቃ 15፡11–32፣ ሶፎ. 3፡ 17፣ ኤፌ. 5፡25–28፣ ኢሳ. 43፡4፣ ሮሜ. 8፡1፣ ሮሜ. 5:8፣ ማር. 9:17-29። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> "አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፤ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል” ሶፎ. 3፡17 + + +እስቲ የሚከተለውን ሁኔታ ያስቡ፡- የአምስት ዓመት ልጅ በአባቶች ቀን በደንብ ያልተጠቀለለ ስጦታ ይዞ ወደ አባቱ ይመጣል። በደስታ ስጦታውን ለአባቱ ይሰጠዋል። አባትየው “ልጄ፣ ስለ ስጦታህ ግድ የለኝም። እንዲያውም እኔን የሚያስደስት ምንም ነገር ልትሰጠኝ አትችልም። ልትሰጠኝ የምትችለው ሁሉ፣ ራሴ እገዛዋለሁ፣ የምትሰጠኝ ማንኛውም ነገር በገንዘቤ የተገዛ ወይም ከከፈልኩባቸው ቁሳቁሶች የተሰራ ነው። ስለዚህ ስጦታህ ለራስህ ይሁንልህ። + +አያስልፈልገኝም። ለማንኛውም ግን እወድሃለሁ” እንዳለው ያስቡ። እህ! + +የዚህ አባት ምላሽ ምን ይመስልዎታል? “ጨካኝ”፣ “ቀዝቃዛ” እና “ስሜት- የለሽ” የሚሉት ቃላት ወደ አእምሯችን ይመጣሉ። እግዚአብሔር እንደዚህ ነው ለእኛ ምላሽ የሚሰጠን? በእርግጥ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን? ለመገመት አስቸጋሪ ቢሆንም - የወደቅን፣ በኃጢአት የተጨማለቅን እና ለክፋት የተጋለጥን ብንሆንም እንኳን - አዎን እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን! በሌላ አነጋገር፣ እግዚአብሔር እኛን ወይም የምናመጣቸውን ስጦታዎቻችንን እንደዚያ አባት አይመለከታቸውም። በተቃራኒው፣ በክርስቶስ ብቻ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/02.md b/src/am/ss/2025-01/03/02.md new file mode 100644 index 0000000000..c12885454a --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/02.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ከምትገምተው በላይ ዋጋ ያለው +date: 12/01/2026 +--- + +ቀደም ባለው ትምህርት ላይ እንዳየነው፣ እግዚአብሔር የማይወደው የከፋ ኃጢአተኛ ወይም ክፉ አድራጊ የለም። እግዚአብሔር ለሰዎች ከምንገምተው በላይ ትልቅ ዋጋ ስላለው፣ ስለሚወደንና ኃጢአትም ምን እንደሚያመጣብን ስለሚያውቅ፣ እርሱ የሚያዝነው በኃጢአት ነው። + +`ሉቃ. 15:11-32ን ያንብቡ። የአባካኙ ልጅ ምሳሌ ስለ እግዚአብሔር ርኅራኄና ፍቅር ምን ያሳየናል? ልክ እንደሌላኛው ልጅ በቤት ላሉ ሰዎች ምን ማስጠንቀቂያ ይሰጣል?` + + +ኢየሱስ በተናገረው በዚህ ታሪክ ውስጥ፣ የሰውየው ልጅ አባቱንና የአባቱን ቤተሰብ በመናቅ ርስቱን አስቀድሞ ጠየቀ። አባካኙ ልጅ ድርሻውን ካባከነ በኋላ ደኸየ፤ ተርቦም ከገንዳ በሚመገቡ እርያዎች ቀና። በአባቱ ቤት ያሉ አገልጋዮች ከበቂ በላይ ምግብ እንዳላቸው ሲያስታውስ፣ አገልጋይ ለመሆን ተመኝቶ ወደ ቤቱ ለመመለስ ወሰነ። + +ቀጥሎ የሆነው አስገራሚ ነው። አንዳንድ አባቶች እንዲህ ዓይነቱን ልጅ ሲመለስ አይቀበሉትም። “ርስትህን ወስደሃል፣ ከቤቴ ተለይ። ከእንግዲህ እዚህ ቤት የለህም” ይሉታል። ይህ ምክንያታዊ እና ትክክለኛ አስተሳሰብ አይደለም? በአንዳንድ ወላጆች እይታ፣ ልጁ እንደ ልጅ ወደ ቤት ሊቀበሉት ወደ ማይችሉበት ደረጃ ደርሷል። + +በምሳሌው ላይ እግዚአብሔርን የሚወክለው አባት ግን በእነዚህ አይነት መንገዶች ምላሽ አይሰጥም። ይልቁንም “እርሱም [አባካኙ ልጅ] ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው” (ሉቃ. 15፡20)። + +`በዚያን ዘመን አባወራ አንድን ሰው ለመቀበል መሮጥ ነውር ቢሆንም ፣ አባትየው ከታላቅ ርኅራኄው የተነሳ ልጁን ለመገናኘት ሩጦ በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ ወደ ቤተሰቡ ቀላቀለው፤ ግብዣም አደረገለት። ይህ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ለባዘነ ሰው ያለውን ታላቅ ርኅራኄ እና ወደ ቤት ሲመለስም ደስ እንደሚሰኝ የሚያመለክት ነው። እንዴት ያለ የእግዚአብሔር ምስል ነው! የሌላኛው ልጅ ሁኔታ የሚገርም ነው። ለምንድነው ይህ ምላሽ፣ በከፊል ፍትሃዊና ለመረዳት የማያስቸግር፣ የሰው ምላሽ የሆነው? ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የፍትሃዊነት ፅንሰ-ሀሳቦች የወንጌልን ጥልቀት ወይም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ሊገልጹት እንደማይችሉ የዚህ ታሪክ ክፍል ምን ያስተምረናል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/03.md b/src/am/ss/2025-01/03/03.md new file mode 100644 index 0000000000..8363fefaf8 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/03.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: በደስታ ሐሴት ማድረግ +date: 13/01/2026 +--- + +ሶፎ. 3፡17 አምላክ በተዋጁት ሕዝቡ ላይ ያለውን ደስታ አጉልቶ ያሳያል። + +በዕብራይስጥ ደስታን የሚገልፁባቸው ቃላት ሁሉ በዚህ አንድ ጥቅስ ውስጥ ታጭቀዋል፣ ይህም እግዚአብሔር በተቤዠው ሕዝቡ ደስ እንደሚሰኝ ያሳያል። + +በዚያ ቀን የእግዚአብሔርን ደስታ ለመግለጽ ከቃላቶቹ ውስጥ አንዳቸውም ብቻቸውን ብቁ አይሆኑም። + +በዚህ ጥቅስ መሠረት እግዚአብሔር በሕዝቡ "መካከል" እንዳለ አስተውሉ። ከፍቅር ግንኙነት የሚመነጨው እርቅ የእግዚአብሔርን መገኘት እውን ያደርጋል። ልክ እንደ አባካኙ ልጅ አባት - ልጁን ከሩቅ ሲያየው እንደሮጠ - እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ነው። + +በኢሳ. 62፡4 ላይ ተመሳሳይ መልዕክት ያዘለ የጋብቻ ምሳሌ ይገኛል። + +በኢሳ. 62:4 የእግዚአብሔር ሕዝብ “ደስታዬ የሚኖርባት” ተብሎ ሲጠራ፣ ምድሪቱም “ያገባች” ትባላለች። ለምን? ምክንያቱም ጥቅሱ “እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና” ይላል። አባቱ በአባካኙ ልጅ እንደተደሰተ፣ የእግዚአብሔር የደስታ ጥግ፣ ሕዝቡን በመንግስቱ ተቀብሎ በሚደሰትበት ቀን ይሆናል። + +`ኤፌ 5:25–28ን ያንብቡ። እኛ እንድናሳይ ስለተጠራንለት የፍቅር ዓይነት ምን ይላል?` + + +ይህ ክፍል ባሎች ሚስቶቻቸውን “ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት እና ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ” እንዲወዷቸው እና “እንደ ገዛ ሥጋቸው” እንዲወዷቸው ይመክራል (ኤፌ. 5፡25፣ 28)። እነዚህ ጥቅሶች ባል ለሚስቱ ሊኖረው ስለሚገባው ከራስ ወዳድነት የጸዳና መስዋዕትነት የሚያስከፍል ፍቅር ብቻ ሳይሆን የሚጠቁሙት፣ ክርስቶስም ራሱ ሕዝቡን (ቤተ-ክርስቲያንን) እንደራሱ እንደሚወዳቸው ያሳያሉ። diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/04.md b/src/am/ss/2025-01/03/04.md new file mode 100644 index 0000000000..4aebca8257 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/04.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: እግዚአብሔርን ማስደሰት? +date: 14/01/2026 +--- + +የአለማት ሁሉ አምላክ በዚች ትንሽ ፕላኔት (ዓለም) ውስጥ በሚኖሩ ተራ ሰዎች - ጊዜያዊ የህዋስ ፈሳሽ ነጠብጣቦች - እንዴት ሊደሰት ይችላል? ሁሉን ቻይ ለሆነውና ምንም ለማያስፈልገው ልዑል፣ የሰዎች ጉዳይ ይህን ያህል ግድ የሚለው ለምን ይሆን? እነዚህ ጥያቄዎች በሁለት መልኩ ሊተነተኑ ይችላሉ። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ራሱ እንዴት ሊደሰት ይችላል? ሁለተኛ ኃጢአተኛ የሆንን ሰዎች እንዴት ልናስደስተው እንችላለን? የመጀመሪያው ጥያቄ የዛሬው ርዕስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የነገ ይሆናል። + +`ኢሳ. 43:4ን፣ መዝ. 149:4ን እና ምሳ. 15:8, 9ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በሕዝቡ እንዴት ደስ ይለዋል?` + +ትላንት በከፊል እንዳየነው አምላክ በሰዎች ሊደሰት ይችላል ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰዎችን የሚወዳቸው እንዲሰምርላቸው ነው - ሌሎችን የሚወድና የሚጠነቀቅላቸው እንደሚያደርገው ሁሉ ማለት ነው። + +በአንጻሩ ሕዝቡ ክፉ ሲሠሩ እግዚአብሔር ያዝናል። ምሳ. 15:8, 9 የክፉዎች “መሥዋዕት” እና “መንገድ” “በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ” ሲሆን፣ “የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው”፣ ደግሞም “እርሱ ጽድቅን ይወድዳል” በማለት ያስተምራል። ይህ ክፍል እግዚአብሔር በክፋት ማዘኑን፣ በበጎ ነገር ደግሞ መደሰቱን ያሳያል። በተጨማሪም መለኮታዊ ደስታን እና ፍቅርን ጎን ለጎን ያስቀምጣቸዋል፣ ይህም በቃሉ ውስጥ በእግዚአብሔር ፍቅር እና ደስታ መካከል ያለውን ጥልቅ ቁርኝት ያሳያል። + +እንደ መዝ. 146፡8 “እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል”። ደግሞም 2 ቆሮ. 9፡7 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል” ይላል። በመጀመሪያ እነዚህ ጥቅሶች የማያስተምሩትን አስተውሉ። እግዚአብሔር ጻድቃንን ወይም በደስታ የሚሰጠውን ብቻ ይወዳል አይሉም። እግዚአብሔር ሁሉንም ይወዳል። + +ሆኖም እነዚህ ጥቅሶች የሚያስተላልፉት መልዕክት፣ እግዚአብሔር “ጻድቃንን” እና “በደስታ የሚሰጠውን” በተለየ መንገድ ይወዳቸዋል የሚል ነው። በምሳ. 15: 8, 9 ላይ የተመለከትነው ነገር ፍንጭ ይሰጠናል፦ አምላክ ሁሉንም የሚወዳቸው በእነርሱ ደስ በመሰኘት ነው። + +የአለማት ፈጣሪ የሆነው አምላክ በስሜት እንኳን ሳይቀር ከእኛ ጋር በመቆራኘቱ፣ ሰማይና ምድር ምን ያህል የተሳሰሩ እንደሆነ ያስቡ። + +`ይህ አስደናቂ ሐሳብ ምን ተስፋ ሊሰጥዎ ይገባል - በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆኑ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/05.md b/src/am/ss/2025-01/03/05.md new file mode 100644 index 0000000000..5d22cde71c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/05.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ሕያዋን ድንጋዮች +date: 15/01/2026 +--- + +`የወደቅንና ኃጢአተኛ ፍጡራን ቅዱሱን አምላክ እንዴት ደስ ማሰኘት እንችላለን? ሮሜ 8፡1ን እና ሮሜ 5፡8ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሔር ፊት ስላለን ተቀባይነት ምን ያስተምራሉ?` + + +ሰዎች ገና ምላሽ ሳይሰጡ፣ እግዚአብሔር ለሰዎች ጸጋውን ይሰጣቸዋል። + +ምንም ሳናደርግ በፊት፣ እግዚአብሔር ወደ እኛ መጥቶ ፍቅሩን እንድንቀበል ወይም እምቢ እንድንል እድሉን ይሰጠናል። ሮሜ 5፡8 “ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” በማለት ይገልጸዋል (ከኤር. 31፡3 ጋር ያስተያዩ)። እናም አዳኛችን ለኛ በሠራው ሥራ በማመን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ልንታረቅና በፊቱም ደስ ልናሰኘው እንችላለን። + +`1 ጴጥ. 2:4–6ን አንብበው ከዕብ. 11:6 ጋር ያስተያዩ። እግዚአብሔርን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደምንችል ይህ ምን ይነግረናል?` + +ያለ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት፣ በኃጢአት የወደቁ ሰዎች ምንም ዋጋ ያለው ነገር ለእግዚአብሔር ሊያመጡ አይችሉም። ነገር ግን እግዚአብሔር በጸጋው እና በምህረቱ፣ በክርስቶስ ሥራ መንገድን አዘጋጀ። በተለይም “በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ማቅረብ” እንችላለን (1ጴጥ. 2፡5)። ምንም እንኳን “ያለ እምነት እርሱን ደስ ማሰኘት ባይቻልም” (ዕብ. 11፡6)፣ በክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ፣ እግዚአብሔር “በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን” ይላል (ዕብ. 13:21)። የርሱ ጽድቅ ብቻ ተቀባይነት ስላለው፣ በክርስቶስ ምልጃ ለእግዚአብሔር በእምነት ምላሽ የሚሰጡ፣ በእርሱ ፊት ጻድቃን ሆነው ይቆጠራሉ። ለእግዚአብሔር ፍቅር ምላሽ የሚሰጡ በክርስቶስ ምልጃ ምክንያት ብቁ ሆነው ይቆጠራሉ (ሉቃ. 20፡35)፤ እርሱም እርሱን እንዲመስሉ ይለውጣቸዋል (1ቆሮ. 15፡51-57፣ 1ዮሐ. 3፡2)። የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ለእኛ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን፣ በእኛ ውስጥም የሚፈፀም ነው። + +`ክርስቶስ በሰማይ ስለ እናንተ የሚማልድ መሆኑ የሚያበረታታ የሆነው ለምንድን ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/06.md b/src/am/ss/2025-01/03/06.md new file mode 100644 index 0000000000..2b21bbc8c6 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: የከበረ አላማ +date: 16/01/2026 +--- + +በእግዚአብሔር ምሕረትና ምልጃ ጥላ ስር፣ ለፍቅሩ ትንሽዬ አዎንታዊ ምላሽ እንኳን ስንሰጥ እግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ብቻውን ሊወደድ በሚገባው እና ፍጹም ጻድቅ በሆነው በርሱ በኩል፣ እያንዳንዳችን ጻድቃን ተብለን፣ በእግዚአብሔር ተወደው ለዘላለምም ከርሱ ጋር ፍጹም በሆነ ፍቅር ከሚኖሩት ጋር ልንቆጠር እንችላለን። ይህ ታላቅ የመቤዠት ተስፋ ነው፣ እሱም ክርስቶስ በሰማይ ለእኛ የሚሰራውን ሥራ ያካትታል። + +`ግን ይህ እኔንም ሊያካትት ይችላል? ብለው ሊደነቁ ይችላሉ። ብቁ ባልሆንስ? በቂ እምነት የለኝም ብዬ ብፈራስ? ማር. 9:17-29ን ያንብቡ። ክርስቶስ በታሪኩ ውስጥ ላለው ሰው ምን ምላሽ ሰጠው? ምን ያህል እምነት ነው በቂ እምነት ሊሆን የሚችለው?` + +ደቀ መዛሙርቱ ጋኔኑን ማውጣት አልቻሉም፤ ተስፋው ሁሉ የተሟጠጠ መሰለ። ኢየሱስ ግን ቀርቦ ለአባቱ ‘‘ብታምን፣ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል’’ አለው (ማር. 9፡23)። አባትየውም በእንባ፡- "ጌታ ሆይ፥ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው አለ” (ማር. 9፡24)። + +ኢየሱስ ሰውየውን፣ “እምነት ሲኖርህ ወደ እኔ ተመለስ” እንዳላለው አስተውሉ። ይልቁንም “አለማመኔን እርዳው” የሚለው ጩኸቱ በቂ ነበር። + +ያለ እምነት አይቻልም (ዕብ. 11፡6)፤ ሆኖም ኢየሱስ ትንሿን እምነት እንኳን ይቀበላል። እናም በእምነት (በክርስቶስ የምልጃ ሥራ) እርሱን ደስ ማሰኘት እንችላለን። በእምነት እና ክርስቶስ በእኛ ፈንታ ባደረገው ሥራ፣ አምላክን በሚያስደስት መንገድ ምላሽ መስጠት እንችላለን - ምድራዊ አባት ልጁ ብዙም ዋጋ የሌለው ስጦታ ሲያመጣለት እንደሚደሰት ሁሉ ማለት ነው። + +ስለዚህ የጳውሎስን ምክር በመከተል እግዚአብሔርን ‘ማስደሰት’ አላማችን ሊሆን ይገባል (2 ቆሮ. 5:9, 10፤ ከቆላ. 1:10፣ 1 ተሰ. 4:1፣ ዕብ. 11፡5 ጋር ያስተያዩ)። እናም የምንወዳቸውን ሰዎች ፍላጎት ለመሙላት የኛን ምኞት እንዲለውጥልን እና ፍቅራችን ለሌሎች እንዲደርስ እንዲያሰፋው እግዚአብሔርን ልንጠይቀው ይገባል። “በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጸኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ” (ሮሜ. 12፡10–13፣)። + +`እግዚአብሔር በክርስቶስ የሚቀበለን ከሆነ፣ እኛስ ሌሎችን እንዴት አብልጠን መቀበል አለብን? ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚለው ትእዛዝ (ዘሌ. 19፡18፣ ማቴ. 22፡39) እና ሰዎች ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን አንተም እንዲሁ አድርግላቸው የሚለው ወርቃማው ሕግ ይህን ሃሳብ እንዴት ይገልጹታል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/07.md b/src/am/ss/2025-01/03/07.md new file mode 100644 index 0000000000..9f7cc6ffef --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/07.md @@ -0,0 +1,28 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 17/01/2026 +--- + +የዘመናት ምኞት ከሚለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ልባችሁ አይታወክ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 662–680 ያንብቡ። + +“ጌታ ሕዝቡ ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት ሲሰጡ ያዝናል። የመረጠው ርስቱ የሆነ ሕዝብ፣ እርሱ በሰጣቸው ዋጋ ልክ ራሳቸውን እንዲተምኑ ይሻል። + +እግዚአብሔር ይፈልጋቸዋል፣ ያማ ባይሆን ኖሮ ልጁን እንዲቤዣቸው እንዲህ ያለ ውድ ዋጋ የሚያስከፍል መልዕክት አስይዞ ባልላከው ነበር። ለእነርሱ ሥራ አለው፤ ስሙንም ያከብሩ ዘንድ ታላላቅ ልመናዎችን ሲያቀርቡለት በጣም ይደሰታል። + +በተስፋዎቹ ካመኑ ታላላቅ ነገሮችን ሊጠብቁ ይችላሉ። + +"በክርስቶስ ስም መጸለይ ግን ትርጉም አለው። ባሕርይውን መቀበል፣ መንፈሱን መግለጥ እና ሥራውን መሥራት አለብን ማለት ነው። የአዳኛችን ተስፋ የተሰጠው በቅድመ ሁኔታ ነው። ‘ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ’ ይላልና። ሰዎችን የሚያድናቸው ከነኃጢአታቸው ሳይሆን ከኃጢአታቸው ነው። የሚወዱትም በመታዘዝ ፍቅራቸውን ያሳያሉ። + +"እውነተኛ ታዛዥነት ሁሉ ከልብ ይመነጫል። ክርስቶስ ጉዳዩ ልብን መለወጥ ነው። ፍቃደኛ ብንሆን፣ ራሱን ከሀሳባችን እና አላማችን ጋር ያጣምራል፣ ልባችንን እና ሀሳባችንን ከፈቃዱ ጋር እንዲስማማ ያዋህደዋል፣ እርሱን ስንታዘዝ ታዲያ የራሳችንን ስሜት እንደመፈጸም ይሆንልናል። የታደሰና የተቀደሰ ፈቃዳችን፣ ሥራውን በመፈጸም ከፍ ያለ ደስታን ያገኛል። በተሰጠን እድል ልክ እግዚአብሔርን ስናውቀው፣ ሕይወታችን ቀጣይነት ያለው የታዛዥነት ሕይወት ይሆናል። የክርስቶስን ባሕርይ ስናደንቅ፣ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ስንቆይ፣ ኃጢአትን እንጠላዋለን።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት ፣ ገጽ. 668. + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. “ሳንሳሳ መቀበል” ምን ማለት ሊሆን ይችላል? የመስጠትና የመቀበል ግንኙነት በሰማይና በአዲሲቱ ምድር ምን ሊመስል ይችላል?` + +`2. ምናልባትም የጄምስ ዌብ የጠፈር ቴሌስኮፕ ዓይኖች ሊደርሱባቸው ከማይችሉት ከሩቅ የኮስሞስ ክፍል የመጡ ሰማያዊ መልእክተኞች ነቢዩ ዳንኤልን ሃሙድ “የተወደድክ፣ ተፈላጊ፣ ውድ” በማለት ጠርተውታል። ያውም ሦስት ጊዜ። በዳን. 9፡23 ገብርኤል ኪ ሃሙድ አታ “አንተ እጅግ የተወደድክ ነህና” ይላል። በዳን. 10፡11 ላይ ሰማያዊው ፍጡር (ምናልባትም ገብርኤል) ኢሽ ሃሙድ “እጅግ የተወደድህ ሰው” ብሎ ይጠራዋል፤ ይህም ሀረግ ለዳንኤል ተደግሞለታል (ዳን. 10፡19)። ይህ ስለ እግዚአብሔር ምን እንደሚል እና ምን ያህል ቅርባችን እንደሆነ ያስቡ። ከዚህ አስደናቂ እውነት ምን ተስፋ ሊሰንቁ ይችላሉ?` + +`3. በዕብ. 11 ላይ የተገለጹት የእምነት ጀግኖች ምሳሌዎች ከዚህ ሳምንት ትምህርት ይዘት ጋር እንዴት ይዛመዳሉ? በተለይም አንድ ሰው በእምነት 'እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት' የሚችለው እንዴት እንደሆነ እነዚህ ምሳሌዎች ምን ያሳያሉ? ከእነዚህ የእምነት እና የታማኝነት ምሳሌዎች ምን መማር እና በየዕለት ህይወታችሁ መተግበር ትችላላችሁ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/03/info.yml b/src/am/ss/2025-01/03/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..53da20905b --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/03/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት" + start_date: "11/01/2026" + end_date: "17/01/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/01.md b/src/am/ss/2025-01/04/01.md new file mode 100644 index 0000000000..87a5b78666 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/01.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው +date: 18/01/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +መዝ. 103:13፣ ኢሳ. 49:15፣ ሆስ. 11:1–9፣ ማቴ. 23:37፣ 2 ቆሮ. 11:2፣ 1 ቆሮ. 13:4–8 + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም::” ኢሳ. 49፡15 + + + +ስሜቶች ብዙውን ጊዜ የማይፈለጉ እና ሊወገዱ እንደሚገቡ ይቆጠራሉ። ለአንዳንድ ሰዎች ስሜቶች ምክንያታዊነት የጎደላቸው ስለሆኑ፣ ጥሩ ወንድ ወይም ሴት “ስሜታዊ” ናቸው ተብለው አይገለጹም። በአንዳንድ ጥንታዊ የግሪክ ፍልስፍናዎች፣ “ምክንያታዊ” ሰው የሚባለው ለስሜታዊነት የማይዳረግ ወይም ስሜቱን ስሜት-አልባ በሆነ አመክንዩ የሚገዛ ተመራጭ ነው ተብሎ ይሸለማል። + +በእርግጥ ያልተገሩ ስሜቶች ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠራቸው ስሜት እንዲኖራችው አድርጎ ነው፤ እግዚአብሔር ራሱ በቃሉ የተገለፀው ጥልቅ ስሜቶች እንዳሉት ተደርጎ ነው። + +እግዚአብሔር በጥልቅ ስሜቶች ውስጥ የሚያልፍ ከሆነ፣ ስሜቶች በተፈጥሯቸው መጥፎ ወይም ምክንያት አልባ ሊሆኑ አይችሉም - ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ፍጹም መልካም እና ፍጹም ጥበብ ያለው ነውና። + +በርግጥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ጥልቅ ስሜታዊ ፍቅር መሆኑን በመገንዘብ ውብ እውነታዎችን ልናገኝ እንችላለን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር (ስሜታዊም ሆነ ሌላ) ሁልጊዜ ፍጹም ስለሆነ፣ ከሰው ስሜቶች ጋር ተመሳሳይ ነው ተብሎ ሊታሰብ አይገባም። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/02.md b/src/am/ss/2025-01/04/02.md new file mode 100644 index 0000000000..5a13097bde --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/02.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ከእናት ፍቅር በላይ +date: 19/01/2026 +--- + +ምናልባትም ሰዎች ሁሉ የሚቀምሱት ትልቁ ፍቅር ወላጅ ለልጁ ያለው ፍቅር ነው። እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን አስደናቂ ርኅራኄ ለማሳየት መጽሐፍ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ የወላጅ እና የልጅን ግንኙነት እንደ ምሳሌ ይጠቀማል፡- ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ጥልቅ እና በጣም ውብ ከሆነው የሰው ርኅራኄ ስሜት እጅግ የላቀ መሆኑን አጽንዖት ቢሰጥም። + +`መዝ. 103:13ን፣ ኢሳ. 49:15ን እና ኤር. 31:20ን ያንብቡ። እነዚህ ምስሎች ስለ እግዚአብሔር ርኅራኄ ሁኔታ እና ጥልቀት ምን ያስተላልፋሉ?` + +በእነዚህ ጥቅሶች፣ እግዚአብሔር እኛን እንደ ተወደዱ ልጆቹ ያየናል፣ መልካም አባት እና እናት ልጆቻቸውን እንደሚወዱ ይወደናል። ሆኖም ኢሳ. 49: 15 እንደሚገልጸው፣ እናት እንኳን “የምታጠባውን ልጇን ትረሳ ይሆናል” ወይም “ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ ላትራራ ትችላለች”፣ ነገር ግን አምላክ ልጆቹን ፈጽሞ አይረሳም፣ ርኅራኄውም ፈጽሞ አያልቅም (ሰቆ. ኤር. 3፡22)። + +በተለይም፣ በዚህና በሌሎች ጥቅሶች ርኅራኄ ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ረኸም የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ሩኅሩኅ ፍቅር የሚገልፅ ሲሆን፣ ማሕፀን ከተባለው የዕብራይስጥ ቃል ሬኼም እንደተወሰደ ይታመናል። + +ስለዚህም ሊቃውንት እንዳስተዋሉት፣ የእግዚአብሔር ርኅራኄ “በማኅፀን የተመሰለ የእናት ፍቅር” ነው። በእርግጥም፣ እናት ለአራስ ልጇ ካላት ርኅራኄ እጅግ የላቀ ነው። + +ምንም እንኳን በተደጋጋሚ በእርሱ ላይ በማመፅ ቢያሳዝኑትም፣ በኤር. 31:20 እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝቡን እንደ “ውድ ልጅ” እና “ደስ የሚያሰኝ ልጅ” አድርጎ ይመለከታቸዋል። እግዚአብሔር “ልቤ ይናፍቀዋል”፣ “በእርግጥም እምረዋለሁ” ይላል። እዚህ ላይ ምሕረት ተብሎ የተተረጎመው ቃል ከላይ መለኮታዊ ርኅራኄ (ረሃም) የተባለው ቃል ነው። በተጨማሪም “ልቤ ይናፍቃል” የሚለው ሐረግ “ውስጤ ታወከ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። + +ይህ ገለጻ ከአንጀት ጋር የተቆራኘ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የሚያሳይ፣ የመለኮታዊ ስሜት ቋንቋ ነው። ምንም እንኳን ታማኝ ባይሆኑም፣ እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ርኅራኄውን እና ምህረቱን በሕዝቡ ላይ ያፈሰዋል - ያውም ከምንጠብቀው በላይ። + +`ለአንዳንዶቻችን፣ አምላክ ለእኛ ያለው ርኅራኄ ከአፍቃሪ አባት ወይም እናት ጋር መመሳሰሉን ማወቃችን እጅግ የሚያጽናና ነው። ሆኖም፣ አንዳንድ ሰዎች ወላጆቻቸው አፍቃሪ ስላልነበሩ ለማስተዋል ሊቸገሩ ይችላሉ። ለእነዚህ የአምላክ ርኅራኄ በምን ሌሎች መንገዶች ሊገለፅ ይችላል?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/03.md b/src/am/ss/2025-01/04/03.md new file mode 100644 index 0000000000..189c247e93 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/03.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: አንጀት የሚያላውስ ፍቅር +date: 20/01/2026 +--- + +እግዚአብሔር ለሰው ያለው የማይለካው ጥልቅ ፍቅር በሆሴዕ ተገልጿል። + +እግዚአብሔር ነብዩን ሆሴዕን እንዲህ ሲል አዞት ነበር፡- “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና፣ ሂድ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች ለአንተ ውሰድ አለው” (ሆሴ. 1፡2)። ኋላ ላይ በሆሴ. 11 እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት በአፍቃሪ አባት ይመስለዋል። + +`ሆሴ. 11:1-9ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለው ምስል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅርና ጥንቃቄ እንዴት ሕይወት ይዘራበታል?` + +እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ፍቅር፣ ወላጅ ለልጁ ባለው ርኅራኄ የተሞላ ፍቅር ተመስሏል። ቃሉ ፍቅሩን ለመግለጽ ሌሎች ምሳሌዎችን ተጠቅሟል፡ - ሕጻን ልጅን እንዲራመድ ማስተማር፤ የሚወደውን ልጅ በክንዶቹ ማቀፍ፤ መፈወስ እና በሕይወት ማኖር፤ ለሕዝቡ መጠንቀቅ። “ሰው ልጁን እንደሚሸከም” እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ “ተሸከመ” ይናገራል (ዘዳ. 1፡31)። “በፍቅሩና በረህራሄውም ተቤዣቸው”፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንስቶ ተሸከማቸው” (ኢሳ. 63፡9)። + +ከእግዚአብሔር የማይናወጥ ታማኝነት ጋር ሲነጻጸር፣ ሕዝቡ ግን በተደጋጋሚ ታማኝ አልነበሩም፤ እንዲያውም እግዚአብሔርን በመጋፋትና በራሳቸው ላይ ፍርድ በማምጣት እጅግ አሳዘኑት። እግዚአብሔር ሩኅሩኅ ነው፣ ነገር ግን ፍትሃዊም ነው። (በቀጣዩ ትምህርት እንደምንመለከተው ፍቅርና ፍትሕ አይነጣጠሉም)። + +በሆነ ነገር ተበሳጭተው አንጀትዎ ተላውሶ ያውቃል? ይህ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ጥልቅ ስሜት ያሳያል። የልብ መቃተት እና በርኅራኄ መንሰፍሰፍ የእግዚአብሔርንም ሆነ የሰዎችን ጥልቅ ስሜት የሚያሳዩ ምሳሌዎች ናቸው። + +በርኅራኄ መንሰፍሰፍን (ካማር) የሚያሳው ምሳሌ፣ ወደ ሰሎሞን በመጡትና ሕጻኑ የራሳቸው እንደሆነ በተናገሩት ሁለት ሴቶች ጥቅም ላይ ውሏል። ሰሎሞን ሕፃኑን ለሁለት እንዲከፍሉት ባዘዘ ጊዜ፣ ይህ ሥዕላዊ መግለጫ የእውነተኛዋን እናት ስሜት ይገልጻል (1 ነገ. 3፡26፤ ከዘፍ. 43፡30 ጋር ያስተያዩ)። + +`ወላጅ የሆነ ሁሉ ትምህርቱ ስለ ምን እየተናገረ እንደሆነ ያውቃል። ሌላ ምድራዊ ፍቅርም ከዚህ ጋር አይወዳደርም። ይህ አምላክ ለእኛ ያለውን ፍቅር እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ከዚህ መረዳትስ ምን የሚያፅናና ነገር ልናገኝ ይገባል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/04.md b/src/am/ss/2025-01/04/04.md new file mode 100644 index 0000000000..2207e64e63 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/04.md @@ -0,0 +1,15 @@ +--- +title: የኢየሱስ ርኅራኄ +date: 21/01/2026 +--- + +እንደ ብሉይ ኪዳን ሁሉ፣ አዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔርን ርኅራኄ ለማሳየት ተመሳሳይ ምስል ይጠቀማል። ጳውሎስ አብን “የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ” ይለዋል (2ቆሮ. 1፡3)። በተጨማሪም ጳውሎስ በኤፌ. 2፡4 ላይ እግዚአብሔር “በምሕረቱ ባለ ጠጋ” እንደሆነ እና “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ” እንደዋጀን ይገልፃል። + +`ክርስቶስ ራሱ በተለያዩ ምሳሌዎች፣ የአብን ርኅራኄ ለማሳየት ውስጣዊና አንጀትን የሚያላውስ ስሜትን የሚገልጹ ቃላትን ደጋግሞ ይጠቀማል (ማቴ. 18፡ 27፣ ሉቃ. 10፡33፣ ሉቃ. 15፡20)። በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መለኮታዊ ርኅራኄን ለመግለጽ የተጠቀማቸውን ተመሳሳይ ቃላት፣ ወንጌልም ኢየሱስ ለተጨነቁ ሰዎች የሰጠውን በርኅራኄ የተሞላ ምላሽ ለማሳየትም ተጠቅሞበታል። ማቴ. 9:36ን፣ ማቴ. 14:14ን፣ ማር. 1:41ን፣ ማር. 6:34ን እና ሉቃ. 7:13 ያንብቡ። በተጨማሪ ማቴ. 23፡37ን ይመልከቱ። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ በሰዎች ሥቃይ የተነካበትን መንገድ የሚገልጹት እንዴት ነው?` + + +ወንጌል ደጋግሞ፣ ክርስቶስ በጭንቀት ወይም በችግር ላሉ ሰዎች እንደራራላቸው ይናገራል። መራራትም ብቻ ሳይሆን፣ ችግራቸውንም ፈቶላቸዋል። + +በተጨማሪም ኢየሱስ ለሕዝቡ አንብቷል። ክርስቶስ ከተማዋን ሲመለከት፣ አይኖቹ እንባ እንዳቀረሩ መገመት አይከብድም፡- “ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም” (ማቴ. 23: 37)። እዚህ ላይ የታየው የክርስቶስ ሀዘን፣ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተገለጸው የእግዚአብሔር ኀዘን ጋር እንደሚመሳሰል እንመለከታለን። እንዲያውም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት፣ ወፍ ለጫጩቶቿ ያላት እንክብካቤ በጥንታዊ ቅርብ ምሥራቅ አገሮች ለመለኮት ብቻ ጥቅም ላይ መዋሉን አስተውለዋል። ይህን ብዙዎች በዘዳ. 32፡11 ላይ ስለ እግዚአብሔር ከተገለጸው ጋር ያመሳስሉታል — ወፍ ከጫጩቶቿ በላይ እንደምትሰፍፍ፣ እንደምትጠብቅ እና እንደምትንከባከብ። + +`እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር የሚያሳይ ከኢየሱስ የሚበልጥ ምሳሌ የለም - ፍቅሩን ለመግለፅ ራሱን ለእኛ አሳልፎ ሰጥቷልና። ሆኖም ክርስቶስ ፍጹም የእግዚአብሔር አምሳል ብቻ አይደለም። በተጨማሪም እርሱ ፍጹም የሰዎች ምሳሌ ነው። ሕይወታችንን በክርስቶስ አምሳል የምንቀርፀው አንዴት ነው? በሌሎች ሰዎች ፍላጎት ላይ በማተኮር፣ በመስበክ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ መንገድ የአምላክን ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/05.md b/src/am/ss/2025-01/04/05.md new file mode 100644 index 0000000000..b62cd9ba60 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/05.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ቀናተኛ አምላክ? +date: 22/01/2026 +--- + +የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ “ሩኅሩኅ አምላክ” ነው። በዕብራይስጥ እግዚአብሔር ኤል ራሁም ይባላል (ዘዳ. 4፡31)። “ኤል” የሚለው ቃል “እግዚአብሔር” ማለት ሲሆን፣ ራሁም ደግሞ ሌላው የርኅራኄ (ራሃም) ሥርወ-ቃል ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ሩኅሩኅ አምላክ ብቻ ሳይሆን ቀናተኛ አምላክ ኤል ካና ተብሎም ተጠርቷል። ዘዳ. 4፡24 እንደሚናገረው “አምላካህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፣ ቀናተኛም (ኤል ካና) አምላክ” ነው (ዘዳ. 6:15ን፣ ኢያ. 24:19ን፣ ናሆ. 1፡2ን ይመልከቱ)። + +1ኛ ቆሮ. 13፡4 “ፍቅር አይቀናም” በማለት ያውጃል። ታዲያ እግዚአብሔር “ቀናተኛ አምላክ” እንዴት ሊሆን ይችላል? 2ኛ ቆሮ. 11፡2 አንብበው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለእርሱ ታማኝ ያልሆኑበትን መንገድ ያሰላስሉ (ለምሳሌ መዝ. 78፡58 ይመልከቱ)። + +`እነዚህ ጥቅሶች መለኮታዊውን “ቅናት” ለመረዳት እንዴት ይረዱናል?` + +የእግዚአብሔር "ቅናት" ብዙውን ጊዜ በትክክል አልተስተዋለም። አንድን ሰው ቀናተኛ ባል ወይም ሚስት ነው ካሉ ይህ ሙገሳ አይደለም። ብዙውን ጊዜ ቅናት የሚለው ቃል በብዙ ቋንቋዎች አሉታዊ ፍቺዎች አሉት። ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መለኮታዊ ቅናት ምንም ዓይነት አሉታዊ ትርጉም የለውም። ይህም ንጹህ ፍቅር ሲሆን፣ አፍቃሪ ባል ከሚስቱ ጋር ያለው ብቸኛ ግንኙነት ነው። + +ፍቅርን የሚጻረር ዓይነት ቅናት ቢኖርም (1ቆሮ. 13፡4)፣ እንደ 2ኛ ቆሮ. 11፡ 2 መልካም እና ንጹህ “ቅናት” አለ። ጳውሎስ “አምላካዊ ቅንዓት” ብሎ ይጠራዋል (2ቆሮ. 11፡2)። የእግዚአብሔር ቅናት ሁልጊዜ ንጹህ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ጥልቅ ፍቅር ሊባል ይችላል። + +የእግዚአብሔር ፍቅር (ካና) ለሕዝቡ ካለው ጥልቅ ፍቅር የመነጨ ነው። + +እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ብቸኛ የሆነ (ያልተከፋፈለ) ግንኙነት ይፈልጋል፤ እርሱ ብቻ አምላካቸው ሊሆን ይገባል። ሆኖም እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ምላሽ የተነፈገው፣ የተናቀ ፍቅረኛ ሆኖ ይገለጻል (ሆሴ. 1-3ን፣ ኤር. 2፡2ን፣ ኤር. 3፡ 1-12ን ይመልከቱ)። ስለዚህ የእግዚአብሔር "ቅናት" ወይም "ጥልቅ ስሜት" ያለ ምክንያት የሚመጣ አይደለም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ለከዳተኞችና ለክፉ ሰዎች ምላሽ ነው። የእግዚአብሔር ቅናት (ወይም "ጥልቅ ፍቅር") እንደ ሰው ቅናት አሉታዊ ትርጉም የለውም። ምቀኛም አይደለም፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ለጥቅማቸው ብቻ፣ ከሕዝቡ ጋር ሊኖረው የሚፈልገው ብቸኛ የሆነ፣ ትክክለኛና ንጹህ ፍቅር ነው ። + +`አምላክ ለእኛ ያለውን ዓይነት መልካም “ቅናት” ለሌሎች ማንጸባረቅ የምንችለው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/06.md b/src/am/ss/2025-01/04/06.md new file mode 100644 index 0000000000..2ff5111d8f --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ርህሩህ እና አፍቃሪ +date: 23/01/2026 +--- + +የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ሩኅሩኅ እና አፍቃሪ ነው፣ እነዚህ መለኮታዊ ስሜቶች በጥልቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ተገጸዋል። እግዚአብሔር አዛኝ ነው (ከኢሳ. 63፡9፣ ዕብ. 4፡15 ጋር ያስተያዩ)፤ በሕዝቡ ሰቆቃ ውስጡ ይነካል (መሳ. 10፡16፣ ሉቃ. 19፡41)፤ ለመስማት፣ ለመመለስ እና ለማጽናናትም ፈቃደኛ ነው (ኢሳ 49:10, 15፣ ማቴ. 9፡36፣ ማቴ. 14፡14)። + +`1 ቆሮ. 13:4–8ን ያንብቡ። ይህ ክፍል ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት የእግዚአብሔርን ርኅራኄ እና አስደናቂ ፍቅር እንድንገልጽ የሚጠራን በምን መንገዶች ነው?` + +በ1ኛ ቆሮ. 13፡4–8 ላይ የተገለጸውን ፍቅር ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ወዳጅነት እንዲኖረን እንናፍቃለን። ለሌሎች እንዲህ አይነት ሰው ለመሆን ግን ምን ያህል እንፈልጋለን? ራሳችንን ታጋሽ እና ደግ ማድረግ አንችልም፤ ራሳችንን የማይቀና፣ የማይመካ፣ የማይገባውን የማያደርግ፣ ወይም የራሱን የማይፈልግ ማድረግ አንችልም። “ሁሉን የሚታገስ፥ ሁሉን የሚያምን፥ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ፥ በሁሉ የሚጸና፣ ለዘወትር የማይወድቅ ፍቅር” በራሳችን ሊኖረን አይችልም (1ኛ ቆሮ. 13፡7፣ 8)። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር በሕይወታችን ሊታይ የሚችለው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ሆኖ ነው። መንፈስ ቅዱስም በእምነት የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት በልባቸው ውስጥ ያፈስላቸዋል፤ እግዚአብሔር ይመስገን (ሮሜ. 5፡5)። + +በእግዚአብሔር ጸጋ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ ለእግዚአብሔር ጥልቅና ስሜታዊ፣ ግን ሁልጊዜ ፍጹም ንጹህ እና ምክንያታዊ ፍቅር፣ እንዴት ባለ ተግባራዊ መንገድ ምላሽ ልንሰጥ እና ለሌሎች ልናሳይ እንችላለን? በመጀመሪያ፣ ብቸኛው ተገቢ ምላሽ ፍቅር የሆነውን አምላክ ማምለክ ነው። ሁለተኛ፣ ለሌሎች ርኅራኄ እና ደግነት የተሞላበት ፍቅር በማሳየት ለእግዚአብሔር ፍቅር ምላሽ መስጠት አለብን። በክርስትና እምነታችን ረክተን መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለማጽናናት መነሳሳት አለብን። በመጨረሻም፣ እግዚአብሔር ብቻ እንጂ እኛ ልባችንን መለወጥ እንደማንችል መገንዘብ አለብን። + +ስለዚህ እግዚአብሔርን አዲስ ልብ እንዲሰጠን እንለምነው - መልካሙን የሚወድ እና ከውስጥ እንክርዳዱን የሚያስወግድ ንጹህ እና የሚያነጻ ፍቅር እንዲኖረን። + +ጸሎታችን "ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ … ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም” ይሁን (1 ተሰ. 3:12, 13)። + +`ለምንድነው ለራስ እና ራስ ወዳድነትና ክፋት ለሞላበት ለተፈጥሮአዊ ልባችን መሞት ይህን አይነት ፍቅርን ለመግለፅ ብቸኛው መንገድ የሆነው? ለእኔነት እንሞት ዘንድ ምን ምርጫዎች ማድረግ እንችላለን?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/07.md b/src/am/ss/2025-01/04/07.md new file mode 100644 index 0000000000..43fc13d44c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/07.md @@ -0,0 +1,24 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 24/01/2026 +--- + + + +የበረከት ተራራ ትምህርቶች ከሚላው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ብፁዓን” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 6–44 ያንብቡ። + +“ጥልቅ የሆነ የጎዶሎነት ስሜት የሚሰማቸውና በራሳቸው ምንም መልካም ነገር እንደሌላቸው የሚሰማቸው ሁሉ ወደ ኢየሱስ በመመልከት ጽድቅን እና ኃይልን ሊያገኙ ይችላሉ። ‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ’ ይላል (ማቴ 11፡28)። ድህነትህን በጸጋው ባለጠግነት እንድትለውጥ ይጋብዝሃል። + +እኛ የእግዚአብሔር ፍቅር አይገባንም፣ ነገር ግን ዋሳችን የሆነው ክርስቶስ ብቁ እና ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ አብልጦ ሊያድናቸው ይችላል። ያለፈው ልምምድህ ምንም ይሁን፣ አሁን ያለህበት ሁኔታም ተስፋ የሚያስቆርጥህ ቢሆን፣ ከነማንነትህ ማለትም ከነድካምህ፣ አቅመ ቢስነትህና፣ ተስፋ መቁረጥህ ወደ ኢየሱስ ና። ሩህሩሁ አዳኛችን ከሩቅ ይገናኝሃል፣ በፍቅር እጆቹ ይጠመጠምብሃል፣ የጽድቅ መጎናጸፊያውን ያለብስሃል። የራሱን ባሕርይ የሚያሳየውን ነጭ ልብስ አልብሶ ወደ አብ ያቀርበናል። የኃጢአተኛውን ቦታ ወስጃለሁ ብሎ ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ይማልዳል። ይህን የሚባዝን ልጅ አትመልከት፣ እኔን እንጂ ይላል። ምናልባት ሰይጣን ድምፁን ከፍ አድርጎ በኃጢአታችን እየከሰስ የእኔ ምርኮ ናቸው ቢልም፣ የክርስቶስ ደም በታላቅ ኃይል ይማልድልናል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የበረከት ተራራ ትምህርቶች፣ ገጽ 8, 9 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. ለኢየሱስ ምስጋና ይሁንና እንዴት ወደ አብ እንደምንቀርብ ከላይ የትንቢት መንፈስ የሚናገረውን ይመልከቱ። "የራሱን ባሕርይ የሚያሳየውን ነጭ ልብስ አልብሶ ወደ አብ ያቀርበናል።" አንዳንድ ጊዜ ከስህተቶቻችንና ከድክመቶቻችን የተነሳ የቱንም ያህል ተስፋ ብንቆርጥ ወይም ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚያፈሰውን ፍቅር ለሌሎች ማንጸባረቅ ባንችልም፣ ሁልጊዜ በአብ ዘንድ ተቀባይነት ወደ አገኘንበት ወደ አስደናቂው የምሥራች ያውም የሱስ "የራሱን ባሕርይ የሚያሳየውን ነጭ ልብስ አልብሶ ወደ አብ ያቀርበናል" ወደሚለው መመልከት ያለብን ለምንድን ነው?` + +`2. ሁለቱ ሴቶች በሕይወት ያለው ሕፃን ልጃቸው እነደሆነ በመናገር በሰሎሞን ፊት በቀረቡ ጊዜ፣ እናትየው ምን እንደተሰማት ያስቡ። በ1 ነገ. 3፡26 ላይ የተገለጸውን ስሜት እንደገና ይመልከቱ። ይህ በሆሴ. 11፡8 ላይ አምላክ ለሕዝቡ ያለውን ስሜት ለመግለጽ የተጠቀመበትን ተመሳሳይ ቃል ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል?` + +`3. በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ በሰዎች ፍላጎት ልቡ ይነካ እንደነበረ አይተናል። እና ምን አደረገ? የሕዝቡን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ ችግራቸውን ፈቶላቸዋል። እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ቡድን፣ መፅናናት የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ፍላጎት ማሟላት የምትችሉባቸው ተጨባጭ መንገዶች ምንድን ናቸው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/04/info.yml b/src/am/ss/2025-01/04/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..32d223a1d5 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/04/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው" + start_date: "18/01/2026" + end_date: "24/01/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/01.md b/src/am/ss/2025-01/05/01.md new file mode 100644 index 0000000000..2bbe903852 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/01.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: የመለኮታዊው ፍቅር ቁጣ +date: 25/01/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +መዝ. 78፣ ዮና. 4:1–4፣ ማቴ. 10:8፣ ማቴ. 21:12, 13፣ ኤር. 51:24, 25፣ ሮሜ. 12፡17–21። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “እርሱ ግን መሓሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም” መዝ. 78፡38 + + + + +ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ርኅራኄ ቢወደስም፣ የቁጣው ነገር ብዙዎችን ይረብሻቸዋል። እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ ቁጣውን ፈጽሞ መግለጽ የለበትም ብለው ያስባሉ። ይህ አመለካከት ግን የተሳሳተ ነው። + +ቁጣው በቀጥታ የሚመነጨው ከፍቅሩ ነው። አንዳንዶች የብሉይ ኪዳኑ አምላክ የቁጣ አምላክ እንደሆነ እና የአዲስ ኪዳኑ አምላክ ደግሞ የፍቅር አምላክ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው፤ በሁለቱም ኪዳናት ተመሳሳይ እንደሆነ ተገልጿል። ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር በክፋት ላይ ይቆጣል—ምክንያቱ ደግሞ እሱ ፍቅር ስለሆነ ነው። ኢየሱስ ራሱ በክፋት ላይ ጥልቅ ቁጣውን ገልጿል፤ አዲስ ኪዳንም ጻድቅና ተገቢ ስለሆነው የእግዚአብሔር ቁጣ ብዙ ጊዜ ያስተምራል። + +የእግዚአብሔር ቁጣ ሁልጊዜ በክፋትና በኢ-ፍትሐዊነት ላይ የሚገለጽ የጽድቅና የፍቅር ምላሽ ነው። መለኮታዊው ቁጣ ከፍፁም መልካምነቱና ፍቅሩ የተነሳ የሚመጣ የጽድቅ ቁጣ ነው፤ እናም የፍጥረትን ሁሉ ደህንነት ይሻል። + +ባጭሩ የእግዚአብሔር ቁጣ የምንለው ለክፋትና ለኢ-ፍትሐዊነት የሚሰጥ ተገቢ የሆነ የፍቅር ምላሽ ነው። ስለዚህ ክፋት እግዚአብሔርን የተገፉትን ለማዳን እና በአጥፊዎቹም ለመፍረድ እንዲነሳ ያደርገዋል። እንግዲህ መለኮታዊው ቁጣ የመለኮታዊ ፍቅር ሌላው ገጽታ ነው ማለት ነው። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/02.md b/src/am/ss/2025-01/05/02.md new file mode 100644 index 0000000000..d12a4ae78a --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/02.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: በክፋት የሚያዝን +date: 26/01/2026 +--- + +የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ፍትሕን ይወዳል፣ ክፋትንም ይጠላል። ስለዚህ ኃጢአትና ክፋት እርሱን ለተጨቆኑና ለተበደሉ በስሜት እንዲነሳ ያደርገዋል - የአንድ ሰው ክፋት በዋነኝነት ራሱን በሚጎዳበት ጊዜም ማለት ነው። እግዚአብሔር ክፋትን የሚጠላው ክፋት ሁልጊዜ ፍጡራኑን ስለሚጎዳ ነው - ምንም እንኳን ጉዳቱን ሰው በራሱ ላይ ቢያመጣውም። በቃሉ እንደተገለጸው፣ በተደጋጋሚ የተነሳው የአመፅ ዑደት እግዚአብሔርን በቁጣ እንዲነሳ አድርጎታል። ዑደቱም እንደሚከተለው ነው፡- + +ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ ክፉ ይሰራሉ፣ አንዳንዴ ልጆቻቸውን በመሰዋት እና ሌሎች አጸያፊ ድርጊቶችን በፊቱ በማድረግ አሰቃቂ ግፍ ይፈጽማሉ። + +እግዚአብሔር በእነርሱ ውሳኔ ምክንያት ከእነርሱ ይለያል። ሕዝቡ በባእድ አገራት ይጨቆናል። ሕዝቡ እግዚአብሔር እንዲያድናቸው ይጮሃሉ። እግዚአብሔር በቸርነቱ ሕዝቡን ያድናቸዋል:: ሕዝቡ እንደገና ከፊት ይልቅ በከፋ ሁኔታ በእግዚአብሔር ላይ ያምጻሉ። በዚህ አስከፊ የክፋት እና የክህደት አዙሪት ውስጥ እንኳን፣ የሰውን አለመታመን እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ታማኝነት፣ በትዕግስት፣ በሚያስደንቅ ጸጋ እና ጥልቅ ርኅራኄ ደጋግሞ ይገናኘዋል። + +`መዝ. 78ን ያንብቡ። ለሕዝቡ ተደጋጋሚ አመጽ የእግዚአብሔር ምላሽ ምን እንደሆነ ይህ ክፍል ምን ይነግረናል?` + + +በመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅርና ፍትሕ እንዳይነጣጠሉ ሆነው የተጋመዱ ናቸው። መለኮታዊው ቁጣ በክፉ ላይ የሚመጣ ትክክለኛ የፍቅር ምላሽ ነው፣ ምክንያቱም ክፋት ሁልጊዜ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው ይጎዳል። + +በቃሉ ውስጥ እግዚአብሔር በዘፈቀደ ወይም ያለ አግባብ የተቆጣበት ወይም የተናደደበት ሁኔታ የለም። + +ሕዝቡ ደጋግመው እግዚአብሔርን ቢተውትና ቢክዱትም፣ ከምንጠብቀው በላይ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ በትዕግሥት ራርቶላቸዋል (ነህ. 9፡7–33)። በዚህም የማይመረመረውን ጥልቅ ትዕግሥት የተሞላውን ርኅራኄ እና መሐሪ የሆነውን ፍቅሩን አሳይቷል። በእርግጥም እንደ መዝ. 78: 38 እግዚአብሔር “መሓሪ (ሩኅሩኅ) ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም”። + +`በእርግጠኝነት በሌሎች ላይ በተፈፀመው ክፋት ተቆጥተው ያውቃሉ። ታዲያ ይህ ስሜት በክፋት ላይ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ቁጣ በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱት የሚረዳዎት እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/03.md b/src/am/ss/2025-01/05/03.md new file mode 100644 index 0000000000..42ef93f02a --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/03.md @@ -0,0 +1,24 @@ +--- +title: እግዚአብሔር ለቁጣ የዘገየ ነው +date: 27/01/2026 +--- + + + +`እግዚአብሔር በክፋት ላይ የሚቆጣው ፍቅር ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር እጅግ ርህሩህና ቸር ስለለሆነ፣ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢይ ከምሕረቱ ብዛት የተነሳ በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረመ! የዮናስን ታሪክ ይመልከቱ። በዮና. 4፡1–4 ውስጥ እግዚአብሔር ለነነዌ ሰዎች ላደረገው ርኅራኄ የተሞላ ይቅርታ የዮናስን ምላሽ ያሰላስሉ። ይህ ስለ ዮናስ እና ስለ እግዚአብሔር ምን ይነግረናል? (ማቴ. 10:8ንም ይመልከቱ)` + +ዮናስ ለእግዚአብሔር ምሕረት የሰጠው ምላሽ በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይታያል። በመጀመሪያ የዮናስን ልበ ደንዳናነት ያሳያል። አሦራውያን በእሥራኤላውያን ላይ ስላደረጉት ነገር እጅግ ስለጠላቸው፣ እግዚአብሔር እንዲምራቸው አልፈለገም። + +ለእኛ እንዴት ያለ ትምህርት ነው! ምንም እንኳን ሁኔታው ምክንያታዊ ቢሆንም፣ ከእንደዚህ አይነት ተመሳሳይ አመለካከት መጠበቅ ይኖርብናል። + +ከሌሎች ሁሉ ይልቅ የእግዚአብሔርን ጸጋ የተቀበሉ፣ ጸጋ ምን ያህል የማይገባን ስጦታ እንደሆነ ተገንዝበው፣ ጸጋን ለሌሎች ለመለገስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው። + +በሁለተኛ ደረጃ የዮናስ ምላሽ የእግዚአብሔር ርኅራኄና ጸጋ የባሕርይው እምብርት መሆናቸውን ያጠናክራል። ዮናስ የእግዚአብሔርን ምሕረት በሚገባ ስለሚያውቅ፣ እግዚአብሔር “ቸርና ይቅር ባይ” እንዲሁም “ለቁጣ የዘገየ ምሕረቱም የበዛ“ ስለሆነ፣ ጌታ በነነዌ ላይ ከመፍረድ እንደሚፀፀት ያውቅ ነበር (ዮና. 4፡2)። + +እግዚአብሔር ሁሉንም ህዝቦች በፍትሃዊነትና በምሕረት ይዳኛቸዋል። + +“ለቁጣ የዘገየ” ወይም “ታጋሽ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ሐረግ “አፍንጫ ረጅም” ተብሎ ቃል በቃል ሊተረጎም ይችላል። በዕብራይስጥ ፈሊጥ፣ ቁጣ በምሳሌያዊ አነጋገር ከአፍንጫ ጋር ይዛመድ ነበር፣ እናም የአፍንጫ ርዝማኔ አንድ ሰው ለመናደድ የሚወስድበትን ጊዜ ያሳያል። + +አምላክ “አፍንጫ ረጅም” ተብሎ መጠራቱ ለቁጣ የዘገየና ታጋሽ መሆኑን ያሳያል። ሰዎች ለመናደድ ብዙ ጊዜ ባይወስድባቸውም፣ እግዚአብሔር ግን እጅግ ታጋሽ እና ጸጋውን በነፃ አብዝቶ የሚሰጥ ነው፤ ነገር ግን ኃጢአትን አያጸድቅም ወይም ከኢ-ፍትሃዊነት ፊቱን አያዞርም። ይልቁንም እግዚአብሔር ጻድቅ እና በእርሱ የሚያምኑትን የሚያጸድቅ ስለሆነ ራሱ በመስቀሉ በኩል ኃጢአትንና ክፋትን ያስተሰርያል (ሮሜ 3፡25፣26)። + +`ለበደላችሁ ሰው ምሕረትን ወይም ጸጋን ማሳየት አቅቷችሁ ያውቃል? እግዚአብሔር ላሳየህ የተትረፈረፈ ጸጋ ምላሽ በመስጠት፣ ለሌሎች የበለጠ ቸር እንድትሆን፣ እግዚአብሔር ያደረገልህን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ልታስታውስ ትችላለህ? ኃጢአትን ሳንፈቅድ ወይም በደልንና ጭቆናን ሳናበረታታ፣ ለሌሎች ምሕረትን እና ጸጋን እንዴት እናሳያቸዋለን?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/04.md b/src/am/ss/2025-01/05/04.md new file mode 100644 index 0000000000..a91768852f --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/04.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: የጽድቅ ቁጣ +date: 28/01/2026 +--- + + + +ብዙ ተገቢ ያልሆኑ ቁጣዎች ቢኖሩም መጽሐፍ ቅዱስ “የጽድቅ ቁጣ” እንዳለ ያስተምራል። አንዲት እናት የሦስት ዓመት ሴት ልጇን በመጫወቻ ስፍራ ስትጫወት እየተመለከተች ሳለ፣ በድንገት አንድ ሰው በልጇ ላይ ጥቃት እንዳደረሰባት ያስቡ። + +ታዲያ መቆጣት የለባትምን? በደንብ አንጂ። እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ፣ ቁጣ የፍቅር ተገቢው ምላሽ ነው። ይህ ምሳሌ የአምላክን “የጽድቅ ቁጣ” እንድንገነዘብ ይረዳናል። + +`ማቴ. 21:12, 13ን እና ዮሐ. 2:14, 15ን ያንብቡ። ኢየሱስ ቤተ- መቅደሱን ይገለገሉበት ለነበረው ሁኔታ የሰጠው ምላሽ፣ እግዚአብሔር በክፉ ላይ እንደሚቆጣ ምን ይነግረናል?` + +`በእነዚህ ሁኔታዎች የአምላክን ቤተ-መቅደስ አርክሰውና “የወንበዴዎች ዋሻ” አድርገው መበለቶችን፣ ወላጅ አልባ ልጆችን እና ድሆችን በሚበዘብዙት ላይ ኢየሱስ "አምላካዊ ቅንዓት" የሆነውን የጽድቅ ቁጣ አሳይቷል (ማቴ. 21:13ን ከዮሐ. 2:16 ጋር ያስተያዩ)። የእግዚአብሔርን ይቅርታና ኃጢአተኞችን ማንጻቱን የሚያመለክቱት ቤተ-መቅደሱና አገልግሎቶቹ፣ በምትካቸው ምስኪኖችን ለማጭበርበር እና ለመጨቆን ይውሉ ነበር። ኢየሱስ በዚህ ርኩሰት መቆጣት አልነበረበትምን?` + +ማር. 10:13, 14 እና ማር. 3:4, 5 የጽድቅ ቁጣውን የሚያሳዩ ተጨማሪ ምሳሌዎችን ይሰጡናል። ሰዎች ሕፃናትን ወደ ኢየሱስ ሲያመጡና “ደቀ መዛሙርቱ ያመጡአቸውን ሲገሥጿቸው”፣ ኢየሱስ “በጭራሽ አልተደሰተም” - “ተቈጣ” እንጂ። እርሱም፡- “ሕፃናትን ወደ እኔ ይምጡ ዘንድ ተው አትከልክሉአቸው” አላቸው (ማር. 10:13, 14)። + +በሌላ ቦታ፣ ፈሪሳውያን ኢየሱስን በሰንበት በመፈወሱ ሕግን እንደ ጣሰ ለመክሰስ ሲጠባበቁ፣ ኢየሱስ “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” ሲል ጠየቃቸው (ማር. 3፡4)። “ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸውና” ሰውየውን ፈወሰው (ማር. 3፡5)። የክርስቶስ ቁጣ እዚህ ላይ በደንዳናነታቸው ማዘኑን ያሳያል። + +`በብሉይ ኪዳን እንደተገለጸው፣ ይህ ከፍቅር የሚመነጭ የጽድቅ ቁጣ ነው። በተለይ ክፋት የፍቅሩን ኢላማዎች ሲጎዳ፣ ፍቅር በክፋት ላይ እንዴት አይቆጣም?` + +`ራስ ወዳድ የሆነን ቁጣ “የጽድቅ ቁጣ” ነው ብለን እንዳናስብ መጠንቀቅ ያለብን እንዴት ነው? ይህን ማድረግ ቀላል የሚሆነው ለምንድን ነው? ራሳችንንስ ከዚህ ስውር ግን ተጨባጭ ወጥመድ እንዴት መጠበቅ እንችላለን?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/05.md b/src/am/ss/2025-01/05/05.md new file mode 100644 index 0000000000..88d241125e --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/05.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: እግዚአብሔር ሆን ብሎ አያስጨንቅም +date: 29/01/2026 +--- + +በመላው መጽሐፍ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ለተገፉና ለተጨቆኑ እንደሚያዝንላቸው እና የጽድቅ ቁጣውን ደግሞ በአስጨናቂዎቻቸውና በጨቋኞቻቸው ላይ እንደሚያመጣ እየደጋገመ ያሳያል። ክፋት ባይኖር እግዚአብሔር አይቆጣም ነበር። ቁጣው ሁልጊዜ ፍጥረቱን በሚጎዳው ነገር ላይ ብቻ ነው። + +እንደ ሰቆ. ኤር. 3:32, 33 እግዚአብሔር ሆን ብሎ “ከልቡ” አያስጨንቅም። + +በክፉ አድራጊዎች ላይ መፍርድ አይፈልግም፣ ነገር ግን ፍቅር በመጨረሻ ፍትሕን ይሻል። + +ይህ እውነት እግዚአብሔር ሕዝቡን ለረጅም ጊዜ ይቅር በማለቱ እና ንስሐ እንዲገቡና ከእሱ ጋር እንዲታረቁ እድሎችን ደጋግሞ በመስጠቱ ታይቷል። + +በተደጋጋሚ እግዚአብሔር ሕዝቡን በነቢያቱ አማካኝነት ጠርቷቸዋል፣ ነገር ግን እነርሱ ለማድመጥ ፈቃደኛ አልነበሩም (ኤር. 35፡14–17ን፣ መዝ. 81፡11–14ን ይመልከቱ)። + +`ዕዝ. 5:12ን አንብበው ከኤር. 51:24, 25, 44 ጋር ያስተያዩ። ይህ በባቢሎናውያን በኩል በኢየሩሳሌም ላይ ስለመጣው ፍርድ ምን ይገልጻል? ( 2 ዜና 36:16ንም ይመልከቱ)` + +ዕዝ. 5 እንደሚለው ሕዝቡ በእምቢተኝነትና ያለማቋረጥ እግዚአብሔርን ካስቆጡ በኋላ፣ እርሱ በመጨረሻ ተዋቸውና ሕዝቡን “በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው” (ዕዝ. 5፡12)። ይሁን እንጂ አምላክ ይህን ያደረገው “መድኃኒት ስላላገኘላቸው” ብቻ ነው (2 ዜና. 36:16)። የኋላ ኋላ ግን አምላክ ባቢሎንን በይሁዳ ላይ ባደረሰችው ከመጠን ያለፈ ውድመት ፈርዶባታል (ኤር. 51:24, 25, 44 ፤ ከዘካ. 1:15 ጋር ያስተያዩ)። + +ቃሉ እግዚአብሔር እንዳመጣባቸው የሚገልጻቸው ሌሎች በርካታ ፍርዶች፣ ሕዝቡ ጌታን በመተው የአሕዛብን “አማልክት” ለማገልገል ስለወሰኑ (መሳ. 10፡6–16፣ ዘዳ. 29፡24–26)፣ አምላክ ሕዝቡን ለጠላቶቻቸው አሳልፎ መስጠቱን የሚያሳይ ነው (መሳ. 2:13, 14፣ መዝ. 106:41, 42)። እግዚአብሔር በክፋት ላይ ያለው ቁጣ የሚመነጨው ለሁሉ ካለው ፍቅርና ለዓለማት ካለው የደህንነት ፍላጎት ነው። ዓለማት ስለ ኃጢአት፣ አመፅና ክፋት ጥያቄ ውስጥ ናቸው። በመጨረሻም ክፋትን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያጠፋዋል። + +`አምላክ በማንም ላይ ፍርድ ለማምጣት የማይፈልግ የመሆኑ እውነታ፣ ስለ መለኮታዊው ቁጣ ያለህን ግንዛቤ የሚቀይረው እንዴት ነው? አምላክ ለቁጣ የዘገየ ከሆነ፣ በዙሪያችን ላሉ ሰዎች የበለጠ ታጋሽ መሆን አይገባንምን? በደል የደረሰባቸውን ሰዎች በመከላከልና በመንከባከብ ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/06.md b/src/am/ss/2025-01/05/06.md new file mode 100644 index 0000000000..3b502e6b1c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/06.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: ርህሩህ ሁን +date: 30/01/2026 +--- + +መለኮታዊው ቁጣ “አስፈሪ” ቢሆንም፣ በምንም መንገድ አግባብ ያልሆነ ወይም ፍቅር የለሽ አይደለም። በተቃራኒው፣ በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን፣ እግዚአብሔር ከፍቅሩ የተነሳ በክፋት ላይ ቁጣውን ይገልፃል። መለኮታዊውን ቁጣ አስፈሪ የሚያደርገው፣ ከእግዚአብሔር ፍጹም መልካምነትና ግርማ ጋር ሲነጻጸር የክፋት ተንኮለኛ መሆን ነው። + +በዚህ ረገድ ፍቅር ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ሲሆን ቁጣ ግን አይደለም። + +`ክፋት ወይም ግፍ በሌለበት ቁጣ የለም። በመጨረሻም፣ የአምላክ ክፋትን ከዓለም የማጥፋት የፍቅር እርምጃ፣ ቁጣን ያስወግዳል። ይህም የሚሆነው ዳግመኛ ግፍ ወይም ክፋት ስለማይኖር ነው። ፍጹም በሆነ የፍቅር ግንኙነት፣ ደስታ እና ፍትሕ ብቻ ለዘላለም ይሰፍናሉ። ዳግመኛ መለኮታዊ ቁጣ የሚያስፈልግበት ምክንያት በጭራሽ አይኖርም። እንዴት ያለ ድንቅ ነገር ነው! አንዳንዶች መለኮታዊው ቁጣ ሳይታሰብ ለሰዎች በቀል ፈቃድ እንደሚሰጥ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብለው ይጨነቃሉ። ዘዳ. 32:35ን፣ ምሳ. 20:22ን፣ ምሳ. 24:29ን፣ ሮሜ 12:17–21ን፣ እና ዕብ. 10:30ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የሰው በቀል አላስፈላጊ መሆኑን የሚገልጹት እንዴት ነው?` + +ቃሉ እንደሚናገረው፣ እግዚአብሔር ፍርድን የማምጣት መብት አለው፣ ሲፈርድም ሁልጊዜ ፍጹም በሆነ ፍትሕ ነው። ብሉይ እና አዲስ ኪዳን በቀል የእግዚአብሔር እንደሆነ በግልፅ ይናገራሉ። ጳውሎስ በሮሜ 12፡19 “ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና” ይላል (ከዘዳ. 32፡35 በመጥቀስ)። + +እግዚአብሔር በመጨረሻ በኢ-ፍትሐዊነትና በክፋት ላይ ፍርድን ሲያመጣ፣ ክርስቶስ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ መንገድን አዘጋጅቷል። በእርግጥም “ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን ኢየሱስ” ነው (1 ተሰ. 1:10፤ ከሮሜ 5:8, 9 ጋር ያስተያዩ)። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር እቅድ ነው፡- " እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ" (1ኛ ተሰ. 5፡9)። መለኮታዊው ቁጣ አይሻርም፣ ነገር ግን በኢየሱስ የሚያምኑ በክርስቶስ ምክንያት ከዚህ ቁጣ ይድናሉ። + +`የክርስቶስ የስርየት አገልግሎት ፍትሕን አስከብሮ እኛን ግን ከቁጣ የሚያድነን በምን መንገድ ነው? ደካማም ብትሆን የመዳን መንገድ ለአንተ እንደተዘጋጀልህ መገንዘብህ፣ ለሌሎች አብልጠህ ምን ያህል ይቅር ባይ መሆን አለብህ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/07.md b/src/am/ss/2025-01/05/07.md new file mode 100644 index 0000000000..03eb2891f9 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/07.md @@ -0,0 +1,32 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 31/01/2026 +--- + +አበው እና ነቢያት ከሚለው የኤለን ጂ. ዋይት መጽሐፍ “በሲና የጣዖት አምልኮ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 315–330 ያንብቡ። + +ከወርቅ ጥጃው ኃጢአት አንጻር ኤለን ጂ. ዋይት እንዲህ በማለት ጽፋለች:- “እሥራኤላውያን አምላክን በመካድ በደለኞች ነበሩ፣ ይህንም ያደረጉት በበረከት በሞላቸውና ለስልጣኑም በፈቃዳቸው ለመታዘዝ ቃል በገቡለት ንጉሥ ላይ ነበር። + +መለኮታዊው መንግሥት እንዲጸና፣ ከሃዲዎቹ ሊፈረድባቸው ይገባ ነበር። ግን እዚህም ላይ የእግዚአብሔር ምሕረት ታይቷል። ሕጉን ቢያፀናም፣ የምርጫ ነፃነትንና ንስሐ የመግባት እድልን ለሁሉም ሰጣቸው። በዓመፅ የጸኑት ብቻ ተቀሰፉ። + +“እግዚአብሔር በጣዖት አምልኮ ደስ እንደማይሰኝ በዙሪያው ላሉት አሕዛብ ምስክር እንዲሆን በዚህ ኃጢአት ላይ እርምጃ መወሰድ ነበረበት። በበደለኞቹ ላይ በመፍረድ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ሙሴ፣ በወንጀላቸው ላይ የከበረ ሕዝባዊ ተቃውሞን በመዝገብ ላይ ማስቀመጥ ነበረበት። እሥራኤላውያን ከዚህ በኋላ በዙሪያቸው የነበሩትን ነገዶች የጣዖት አምልኮ ሲያወግዙ፣ ያህዌ አምላካችን ነው ያለው ሕዝብ በኮሬብ የወርቅ ጥጃ ሠርቶ እንዳመለከው ይከሷቸዋል። + +ምንም እንኳን አሳፋሪ የሆነውን እውነት ለመቀበል ቢገደዱም፣ እሥራኤላውያን በተላላፊዎች ላይ የደረሰውን አስፈሪ ቅጣት በማመልከት፣ ኃጢአታቸው እንዳልተፈቀደ ወይም እንዳልታለፈ ያስረዳሉ። + +“ከፍትሕ ባልተናነሰ ሁኔታ ፍቅር ለዚህ ኃጢአት ፍርድ እንዲሰጥ አድርጓል። + +. . . በሚሊዮኖች ላይ ሊመጣ ያለውን ፍርድ ለማስቀረት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መሰቃየታቸው የእግዚአብሔርን ምሕረት ያሳይ ነበር። ብዙዎችን ለማዳን፣ ጥቂቶቹን መቅጣት ነበረበት።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ አበው እና ነቢያት፣ ገጽ 324, 325 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1`. ብዙ ሰዎች መለኮታዊ ቁጣ የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ መቀበል የሚከብዳቸው ለምን ይመስላችኋል? እንድታስተውለው የሚረዳህ ምንድን ነው?` + +`2. ሰዎች በቀል ሲፈልጉ የሚመጡ፣ እግዚአብሔር ሲሻ ግን የማይከሰቱ ቁጣዎች ምን ችግሮች ያስከትላሉ?` + +`3. ከወርቅ ጥጃው አመፅ በኋላ አምላክ በእሥራኤል ላይ ያመጣው ፍርድ የመለኮታዊ ምሕረት ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ፍርድ ራሱ የፍቅር ድርጊት መሆኑን የሚያሳዩ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች የትኞቹ ናቸው?` + +`4. ምንም እንኳን እግዚአብሔር በክፋት ላይ በጽድቅ እንደሚቆጣና ፍርድን ፍጹም በሆነ ፍትሕ እንደሚያመጣ ብንገነዘብም፣ ሌሎችን ከመኮነን መቆጠብ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ይህንን በተለይ ከ1ኛ ቆሮ. 4፡5 አንፃር ተወያዩበት።` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/05/info.yml b/src/am/ss/2025-01/05/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..6d4cf82fca --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/05/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "የመለኮታዊው ፍቅር ቁጣ" + start_date: "25/01/2026" + end_date: "31/01/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/01.md b/src/am/ss/2025-01/06/01.md new file mode 100644 index 0000000000..b038af3a61 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/01.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል +date: 01/02/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +መዝ. 33:5፣ መዝ. 85:10፣ ዘዳ. 32፡4፣ ያዕ 1፡17፣ ቲቶ 1፡2፣ ዘጸ. 32፡14፣ ማቴ. 5፡43–48። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “ነገር ግን የሚመካው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር" ኤር. 9፡24 + + +በጥንታዊው የቅርብ ምሥራቅ አገሮች፣ የአሕዛብ “አማልክት”ተለዋዋጭ፣ ሥነ-ምግባር የጎደላቸው እና ባሕርያቸው የማይገመት ብቻ ሳይሆኑ፣ እንደ ሕፃን መስዋዕት ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶችንም ይጠይቁ ነበር። ያም ቢሆን፣ አረማውያኑ በእነርሱ መልካምነት ስለማይተማመኑ፣ የጎሳቸውን “አማልክት” ማስቀየም አይደፍሩም ነበር። + +እንደ ዘዳ. 32፡17 ከእነዚህ “አማልክት” ጀርባ የነበሩት አጋንንት ናቸው (በተጨማሪ 1 ቆሮ. 10፡20, 21ን ይመልከቱ)። የአምልኮ ሥርዓታቸውም ለብዝበዛ የተመቻቸ ስለነበር፣ ሕዝቡን በታላቅ መንፈሳዊና ሥነ-ምግባራዊ ጨለማ ውስጥ ከትቷቸዋል። + +የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ከእነዚህ የአጋንንት ኃይሎች እጅግ የተለየ ነው። ያህዌ ፍፁም መልካምና ባሕርይውም የማይለዋወጥ ነው። እናም አሁንም ሆነ ለዘለአለም ተስፋ ሊኖረን የሚችለው፣ በእግዚአብሔር የማያቋርጥ መልካምነት ብቻ ነው። + +በጥንቱ ዓለም ከነበሩት እና ዛሬም ካሉት የሐሰት “አማልክት” ፍጹም ተጻራሪ በሆነ መልኩ፣ ያህዌ ክፋት፣ መከራ፣ ኢ-ፍትሐዊነት እና ጭቆና በጥልቅ ያሳስበዋል—እነዚህንም ሁሉ ያለማቋረጥ በማያሻማ ሁኔታ ያወግዛል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አንድ ቀን እነዚህን ግፎች ሁሉ ያጠፋቸዋል። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/02.md b/src/am/ss/2025-01/06/02.md new file mode 100644 index 0000000000..13e52542ed --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/02.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ፍቅር እና ፍትሕ +date: 02/02/2026 +--- + +በቃሉ ውስጥ ፍቅር እና ፍትሕ የተጋመዱ ናቸው። እውነተኛ ፍቅር ፍትሕን ይሻል፣ እውነተኛ ፍትሕም የሚኖረውና የሚሰጠው በፍቅር ብቻ ነው። + +እነዚህን ሁለት ፅንሰ-ሀሳቦች የማይነጣጠሉ እንደሆኑ ለማሰብ አልታደልንም፣ ምክንያቱም ፍቅር እና ፍትሕ በሰዎች እጅጉን ተዛብተዋል። + +`መዝ. 33:5ን፣ ኢሳ. 61:8ን፣ ኤር. 9:24ን፣ መዝ. 85:10ን እና መዝ. 89:14ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች አምላክ ለፍትሕ ያለውን ትኩረት የሚያሳዩት እንዴት ነው?` + +እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር ፍትሕን እንደሚወድ በግልጽ ይናገራሉ (መዝ. 33፡5፣ ኢሳ. 61፡8)። በቃሉ ውስጥ የፍቅር እና የፍትሕ ሀሳቦች በማይነጣጠሉ መልኩ የተቆራኙ ናቸው። የእግዚአብሔር ፍቅር እና ጽድቅ አብረው ስለሚሄዱ፣ ጽድቅ እና ፍትሕ በዚህ አለም እንዲከወኑ እጅግ ይገደዋል። + +ስለሆነም ነቢያት ፍትሐዊ ያልሆኑ ሕጎችን፣ የሐሰት ሚዛንን፣ የድሆችንና መበለቶችን ወይም የተጠቁትን ጭቆና ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ኢ-ፍትሐዊነት ያወግዛሉ። ሰዎች ብዙ ክፋትና ግፍ ቢፈጽሙም፣ እግዚአብሔር ግን ያለማቋረጥ “ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ ያደርጋል” (ኤር. 9፡24)። በዚህም መሠረት በቃሉ ውስጥ፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑት በክፉ አድራጊዎች እና ጨቋኞች ላይ ቅጣትን፣ የግፍና ጭቆና ሰለባ ለሆኑት ደግሞ ፍትሕ እና ነፃነትን ስለሚያመጣ መልካም የሆነውን መለኮታዊ ፍርድ በጉጉት ይጠብቃሉ። + +እንዲያውም ጽድቅና ፍትሕ የአምላክ መንግሥት መሠረት ናቸው። + +የእግዚአብሔር የፍቅር መንግሥት ፍትሐዊና ጽድቅን የተሞላ ነው፤ ምግባረ ብልሹ ከሆኑት ከዚህ ዓለም መንግሥታት ፈጽሞ የተለየ ነው። እነርሱ ብዙውን ጊዜ ለግል ጥቅማቸውና ሥልጣናቸው ሲሉ ኢፍትሐዊ ድርጊቶችን እንዲቀጥሉ ያደርጋሉ። በእግዚአብሔር "ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ” (መዝ. 85:10)። + +እግዚአብሔርም ከእኛ የሚጠብቀውን ግልጽ አድርጓል። “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን? (ሚክ. 6:8)። ከእግዚአብሔር ባሕርይ ውስጥ ልናንጸባርቀው የሚገባን ዋንኛው ነገር ፍቅር ሲሆን ይህም ከፍቅር የሚመነጨውን ፍትሕና ምሕረት ያካትታል። + +`አሁንም ቢሆን የተዛባ የሰው ፍትሕ ምሳሌዎች ምንድናቸው? ታዲያ አንድ ቀን የእግዚአብሔር ፍጹም ፍትሕ እንዲመጣ እንዴት መጮህ የለብንም?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/03.md b/src/am/ss/2025-01/06/03.md new file mode 100644 index 0000000000..4b850e4b74 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/03.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: እግዚአብሔር ፍጹም መልካምና ጻድቅ ነው +date: 03/02/2026 +--- + +እግዚአብሔር እንዲሁ ፍትሕን እወዳለሁ የሚል እና ሰዎችንም ፍትሕን እንዲወዱና እንዲያደርጉ የሚጎተጉት ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱ እነዚህን ባሕርያት ፍጹም በሆነና በማያወላውል መልኩ በተምሳሌትነት ያሳየናል። እግዚአብሔር ፍጹም ቅዱስ፣ ታማኝ፣ ጻድቅ እና አፍቃሪ እንደሆነ ቃሉ ያስተምረናል። ሁልጊዜም የሚያደርገው የሚወደድ፣ ጽድቅ የተሞላና ፍትሃዊ ነገር ብቻ ነው። እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም። + +`ዘዳ 32:4ንና መዝ. 92:15ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት እና ጽድቅ ምን ያስተምሩናል?` + +እነዚህ እና ሌሎች ብዙ ጥቅሶች እግዚአብሔር ጻድቅና አፍቃሪ መሆኑን ይናገራሉ—“በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም” (መዝ. 92፡15፣ ከመዝ. 25፡8ና መዝ. 129፡4 ጋር ያስተያዩ)። እግዚአብሔር “ክፋትን አያደርግም። ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፣ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም” (ሶፎ. 3፡5)። የእግዚአብሔር ባሕርይ የፍትሕ መጓደልን ከሚወዱ ሰዎች በቀጥታ ተቃራኒ መሆኑን ያስተውሉ። + +እግዚአብሔር ለሁሉም የሚበጀውን ያውቃል፣ ለሁሉም የተሻለው ነገር እንዲሆን ይፈልጋል፣ ለሁሉም ውጤቱ ያማረ እንዲሆን ዘወትር ይሰራል። + +`መዝ. 9:7, 8ን እና መዝ.145:9–17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?` + +የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ “ጻድቅ ዳኛ” ነው (መዝ. 7፡11)፣ ክፉም ከእርሱ ጋር አይኖርም (መዝ. 5፡4)። 1ኛ ዮሐ. 1፡5 እንደሚያስተምረው፡- “እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም”። እግዚአብሔር ፍፁም መልካም ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን እንደ ያዕ. 1፡13 “እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንም” (ከዕን. 1፡13 ጋር ያስተያዩ)። + +በዚህ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር መልካምነትና ክብር ይታያል። ብዙዎች ስልጣንን ጣዖት ቢያደርጉትም፣ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ስልጣኑን የሚጠቀመው በጽድቅ እና በፍቅር መንገድ ብቻ ነው። ሙሴ እግዚአብሔርን “ክብርህን አሳየኝ” ብሎ ሲጠይቀው፣ እግዚአብሔርም “ቸርነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ” ያለው በአጋጣሚ አይደለም (ዘጸ. 33፡18, 19)። + +`ለምንድነው እንደዚህ አይነቱ መልካም አምላክ በዚህ አለም ላይ ክፋት እንዲበዛ የፈቀደው? በክፍላችሁ መልሳችሁን አብራሩ።` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/04.md b/src/am/ss/2025-01/06/04.md new file mode 100644 index 0000000000..9c31a8bf51 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/04.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: የማይለወጠው የእግዚአብሔር ባሕሪ +date: 04/02/2026 +--- + +`ሚል. 3:6ን እና ያዕ፣ 1:17ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር ባሕሪ ምን ያስተምራሉ?` + +በሚል. 3፡6 ላይ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ አልለወጥም” ይላል። አንዳንዶች ይህንን ጥቅስ አንብበው፣ እግዚአብሔር በምንም መንገድ አይለወጥም ብለው ቢወስዱትም ፣ የቀረው የጥቅሱ ክፍልና አውዱ የሚያረጋግጠው የእግዚአብሔርን የሞራል ባሕርይ አለመለዋወጥ ነው። የቀረው የጥቅሱ ክፍል እንደሚያመለክተው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት ሊለወጥ እንደሚችል ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ‘‘እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፣ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም"ይላልና። ቀጥሎ ባለው ጥቅስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ "ወደ እኔ ተመለሱ፣ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ " ይላል (ሚል. 3:7)። + +ስለዚህ እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር በሁኔታዎች የተመሰረተ ግንኙነቶች ውስጥ ቢገባም፣ ባሕርይው ግን አይለወጥም - ሁልጊዜ ያው ነው። ይህም በያዕ. 1፡17 ላይ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በጎና ፍጹም ስጦታዎች ሁሉ ከማይለዋወጠው ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚመጡ ያውጃል። ስለዚህ እግዚአብሔር የክፋት ምንጭ አይደለም። + +እዚህ እና በሌሎችም ቦታዎች፣ ቃሉ በተደጋጋሚ የእግዚአብሔር ባሕርይ የማይለዋወጥ መሆኑን ያስተምራል። በሌላ አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስ ወጥ በሆነ መልኩ የእግዚአብሔርን የሞራል አለመለዋወጥ ያስተምራል። ሆኖም እግዚአብሔር ከፍጥረታት ጋር እውነተኛ ግንኙነት ውስጥ በመግባት፣ ሁልጊዜ ፍቅር የተሞላና ፍትሃዊ ምላሽ ይሰጣቸዋል። + +`2 ጢሞ. 2:13ን፣ ቲቶ 1:2ን እና ዕብ. 6:17, 18ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?` + +እግዚአብሔር ራሱን ሊክድ አይችልም፤ ፈጽሞ አይዋሽም፤ ተስፋዎቹም የፀኑ ናቸው። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ስለ እኛ ራሱን በመስቀል ላይ (በክርስቶስ) በፈቃዱ የሰጠ ያው አምላክ እንደሆነ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እርሱ ያለምንም ጥርጥር የሚታመን አምላክ ነው፣ ለወደፊቱም አስተማማኝ ተስፋ ሊኖረን ይችላል ምክንያቱም ዕብ. 13: 8 "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው" ይላል። + +`በሕይወታችሁ ነገሮች የተበላሹ ቢሆኑም እንኳን በእግዚአብሔር መልካምነት መታመንን እንዴት መማር ትችላላችሁ? በመልካምነቱ ለመታመን በመስቀል ላይ ያለው የእግዚአብሔር ምስል ምን ያስተምረናል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/05.md b/src/am/ss/2025-01/06/05.md new file mode 100644 index 0000000000..23b2db2a49 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/05.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: የሚፀፀት አምላክ? +date: 05/02/2026 +--- + +እግዚአብሔር “ሊፀፀት” ይችላል? ከሆነ ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔር ባሕርይ ፈጽሞ እንደማይለወጥ አይተናል። ሆኖም አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እግዚአብሔር “ተጸጸተ”ወይም “ሐሳቡን ለወጠ” ብለው ይናገራሉ። + +`ለሰዎች መጸጸት መሳሳትን ማወቅን ያካትታል። ታዲያ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አምላክን “ተጸጸተ” ብለው የሚገልጹት እንዴት ነው? ዘጸ. 32:14ን አንብበው ከኤር. 18:4–10 ጋር ያስተያዩ። ስለ እግዚአብሔር “መጸጸት” የተሰጡትን እነዚህን ገለፃዎች እንዴት ይረዷቸዋል?` + +በእነዚህ እና በሌሎች በርካታ ክፍሎች ውስጥ፣ እግዚአብሔር ሰዎች ሲጸጸቱ ወይም ሲማልዱ በምላሹ ከፍርዱ እንደሚመለስ ተገልጿል። + +እግዚአብሔር ሰዎች ከክፋታቸው ቢመለሱ፣ ሊያደርገው ካቀደው ፍርድ እንደሚፀፀት ቃል ገብቷል። + +`ዘኍ. 23:19ን እና 1 ሳሙ. 15:29ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር “መጸጸት” ምን ያስተምራሉ?` + +እነዚህ ክፍሎች እግዚአብሔር “ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም” (1ሳሙ. 15፡ 29)፤ "ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?” ይላሉ (ዘኍ. 23:19)። ከሌሎቹ ክፍሎች አንፃር ስናነባቸው፣ እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔር በጭራሽ “አይጸጸትም” ይላሉ ብለን ልንወስድ አንችልም፣ ይልቅስ እንደ ሰው “አይጸጸትም” የሚለውን እውነት ነው የሚያስተላልፉት። + +እግዚአብሔር ሁልጊዜ የገባውን ቃል ይጠብቃል። ምንም እንኳን በሰዎች ንስሐ ምክንያት የሚወስደውን እርምጃ ቢለውጥም፣ ያን የሚያደርገው ሁልጊዜም እንደ መልካምነቱና እና እንደ ቃሉ ነው። ሰዎች ንስሐ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር በምላሹ ሊፈጽመው ከነበረው ፍርድ ይመለሳል፣ ምክንያቱም ባሕርይው መልካም፣ ጻድቅ፣ አፍቃሪ እና መሐሪ ስለሆነ ነው። + +`ስለ መለኮታዊው “ጸጸት” የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች አስፈላጊነት ምንድነው? ይህ ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ ወጥነት ምን ያስተላልፋል - ጎን ለጎን እግዚአብሔር ወደ እውነተኛ ሰጥቶ የመቀበል ግንኙነት የሚገባና ያም ለእርሱ ለውጥ የሚያመጣ ቢሆንም?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/06.md b/src/am/ss/2025-01/06/06.md new file mode 100644 index 0000000000..d0470a6c88 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ፍቅርን እና ፍትሕን አጥብቀህ ያዝ +date: 06/02/2026 +--- + +ቃሉ እየደጋገመ እንዲህ ብሎ ያስተምራል፡- "አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ " (ዘዳ. 7:9)። የመልካምነቱና የፍቅር ባሕርይው ከምንም በላይ በመስቀል ላይ በኢየሱስ ተገልጧል (ሮሜ 3፡25, 26ን፣ ሮሜ. 5፡8ን ይመልከቱ)። መዝ. 100:5 "እግዚአብሔር መልካም ነው፣ ፅኑ ፍቅሩም ለዘላለም፣ ታማኝነቱም ለትውልድ ሁሉ ነው” ይላል (ከመዝ. 89፡2 ጋር ያስተያዩ)። ስለዚህ እግዚአብሔር ሊታመን ይችላል፤ ለልጆቹም የሚሰጣቸው በጎ ስጦታዎችን ብቻ ነው (ያዕ. 1፡17፤ ከሉቃ. 11፡11–13 ጋር ያስተያዩ)። + +`እንዲያውም ጠላቶቹ ለሆኑት እንኳን ሳይቀር መልካም ነገሮችን ይሰጣቸዋል። ማቴ. 5:43–48ን ያንብቡ። ይህ ስለ እግዚአብሔር አስደናቂ ፍቅር ምን ያስተምረናል? ከዚህ የኢየሱስ አስተምህሮ አንጻር ለሌሎች ምን ማድረግ አለብን?` + +ማቴ. 5 የእግዚአብሔርን ፍቅር ፍጹም ፍቅር እንደሆነ አድርጎ ይገልጸዋል። ፍጽምና የጎደለው ፍቅር የሚወዱትን ብቻ የሚወድ ፍቅር ነው። + +ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጠሉትን፣ ጠላቶቹም የሆኑትን እንኳን ይወዳቸዋል። ፍቅሩ ሙሉ፣ ፍጹምም ነው። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ፍቅር እና ምሕረት ልናስበው ከምንችለው በላይ የላቀ ቢሆንም፣ ፍትሕን ፈጽሞ አይሽረውም ወይም አይጻረረውም። + +በተቃራኒው ፍርድንና ምሕረትን በአንድ ያጣምራቸዋል (መዝ. 85፡10)። በተመሳሳይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይመክረናል፡- “ምሕረትንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን” (ሆሴ. 12፡6)። ሌላ እትም “ፍቅርንና ፍትሕን አጥብቀህ ያዝ”ይላል (ሆሴ. 12፡6፤ ከሉቃ. 11፡42 ጋር ያስተያዩ)። + +በመጨረሻ እግዚአብሔር ራሱ ፍጹም ፍትሕን ያመጣል። ሮሜ 2፡5 “ቅን ፍርዱ ይገለጣል” ብሎ ያስተምራል። በመጨረሻም የተዋጁት እንዲህ ይዘምራሉ፡ - “ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥ የጽድቅም ሥራህ (ፍርድህ) ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ።” (ራዕ. 15:3, 4፤ ከራዕ. 19:1, 2 ጋር ያስተያዩ)። + +`ኢሳ. 25፡1 “አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ” ብሎ ይናገራል። በመጥፎ ጊዜም ቢሆን አምላክን ማመስገንን እንዴት መማር እንችላለን? በጎ ተጽዕኖ ልታደርግ በምትችልበት ሁሉ ፍትሕን በሚያጎለብት መልኩ ሕይወትህ ራሱ ለአምላክ የምስጋና መስዋዕት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/07.md b/src/am/ss/2025-01/06/07.md new file mode 100644 index 0000000000..af3e1a5046 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/07.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 07/02/2026 +--- + +ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 9-15 ያንብቡ። + +"የእግዚአብሔር ቃል ባሕርይውን ይገልጻል። እርሱ ራሱ ወሰን የሌለውን ፍቅሩንና ርኅራኄውን ገልጿል። ሙሴ ‘ክብርህን አሳየኝ’ ብሎ በጸለየ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ‘መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ’ ሲል መለሰ (ዘጸ. 33:18, 19)። ክብሩም ይህ ነው። ጌታም በሙሴ ፊት አለፈና፡- 'እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል’ ሲል አወጀ (ዘጸ. 34:6, 7)። እርሱ 'ለቍጣ የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ ነው'፣ 'ምሕረትን ይወድዳልና' '' (ዮና. 4፡2፣ ሚክ 7፡18)። + +"በሰማይና በምድር ሊቆጠሩ በማይችሉ መልካምነቶቹ እግዚአብሔር ልባችንን ከእርሱ ጋር አቆራኝቷል። በተፈጥሮ እና የሰው ልብ ሊረዳው በሚችለው ጥልቅና ፍቅር የተሞላበት ምድራዊ ግንኙነት ራሱን ሊገልጥልን ፈለገ። ሆኖም እነዚህ ፍቅሩን በሙላት አይገልጹትም። ምንም እንኳን እነዚህ ማስረጃዎች ሁሉ የተሰጡ ቢሆንም፣ የመልካም ጠላት የሆነው ሰይጣን የሰውን አእምሮ አሳወረ፣ እግዚአብሔርንም በፍርሃት እንዲመለከቱት አደረገ፤ ጨካኝና ይቅር የማይል አድርገው ተረዱት። ሰይጣን ሰዎችን የእግዚአብሔር ዋናው ባሕርይ ፅኑ ፍርድ መፍረድ፣ ደግሞም ጨካኝ ዳኛ፣ ክፉና የማይምር አበዳሪ እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡት መራቸው። ፈጣሪን በሰዎች ላይ ፍርዱን ያፈስባቸው ዘንድ በቅናት ጥፋታቸውንና ስህተታቸውን የሚመለከት አድርጎ ሳለው። ኢየሱስ በሰዎች መካከል ሊኖር የመጣው፣ የአምላክን ወሰን የሌለው ፍቅር ለዓለም በመግለጥ፣ ይህንን ድቅድቅ ጨለማ ለማስወገድ ነበር።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ፣ ገጽ 10, 11 + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + +`1. የእግዚአብሔር ክብር ከመልካምነቱ ጋር የተጣመረ መሆኑን መገንዘብ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ባሕርይ ሳያጎላ፣ ታላቅ ኃይሉ ላይ የሚያተኩረውን የክብር ሥነ-መለኮት አስተምህሮ እንዴት ያርማል?` + +`2. የእግዚአብሔርን መልካምነት ተጠራጥረህ ታውቃለህ? እግዚአብሔርን እንከተላለን የሚሉ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ወይም በዓለም ላይ ካለው ክፋት የተነሳ የእግዚአብሔርን መልካምነት የተጠራጠረ የምታውቀው ሰው አለ? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እንዴት አገኘህለት? እናም በእግዚአብሔር መልካምነት ጥያቄ ያደረበትን ሰው እንዴት መርዳት ትችላለህ? የሚቀጥለውን ሳምንት ትምህርት ይመልከቱ።` + +`3. በክፍል ውስጥ ለሰኞው ጥያቄ መልስ ይፈልጉ። የታላቁ ተጋድሎ እውነታ አሁን ያለውን ክፋት ሁሉ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/06/info.yml b/src/am/ss/2025-01/06/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..aa8cedb60f --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/06/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል" + start_date: "01/02/2026" + end_date: "07/02/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/01.md b/src/am/ss/2025-01/07/01.md new file mode 100644 index 0000000000..60cf6f0634 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/01.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: የክፋት መከሰትና መዘዙ +date: 08/02/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ኢዮ. 30፡26፣ ማቴ.27:46፣ ኢዮ. 38:1-12፣ መዝ. 73፣ ዘፍ. 2:16, 17፣ ራዕ. 21:3, 4። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ::” ራዕ. 21:4 + +ምናልባት ክርስትናን የገጠመው ትልቁ ችግር የኃጢአት መከሰት ሲሆን፣ እግዚአብሔር ፍጹም መልካምና አፍቃሪ ከሆነ፣ በዚህ ዓለም ክፋት እንዴት ሊኖር ቻለ የሚለውን ማስታረቅ ነው። ባጭሩ እግዚአብሔር መልካምና ሁሉን ቻይ ከሆነ፣ እንዴት እጅግ ብዙ ክፋት ሊኖር ቻለ? + +ይህ ተግባራዊ አንድምታ የሌለው የጽንሰ ሐሳብ ችግር ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ ሰዎችን የሚያስጨንቅ እና አንዳንዶችን እግዚአብሔርን እንዳያውቁትና እንዳይወዱት የሚያደርግ ነው። + +“ለብዙዎች የኃጢአት መነሻውና የመከሰቱም ምክንያት እጅግ ግራ ያጋባቸዋል። የክፋትን ሥራ ከአሰቃቂ ስቃይና ጥፋት ውጤቱ ጋር ሲያዩት፣ ይህ ሁሉ በጥበቡ፣ በኃይሉና በፍቅሩ ወሰን በሌለው አምላክ ግዛት ውስጥ እንዴት ሊኖር ይችላል ብለው ይጠይቃሉ። ይህ ምንም ማብራሪያ የማያገኙለት ምስጢር ነው።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 492 + +አምላክ የለም የሚሉ ብዙ ሰዎች በፈጣሪ የማያምኑበት ምክንያት የክፋት መኖር ነው ይላሉ። ነገር ግን በዚህና በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደምንመለከተው፣ የወደቀውን ዓለማችንን የሚጎዳ ክፋት ቢኖርም፣ የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ሙሉ በሙሉ መልካምና ልንተማመንበት የምንችል ነው። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/02.md b/src/am/ss/2025-01/07/02.md new file mode 100644 index 0000000000..79d76b33cf --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/02.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: "እስከ መቼ ጌታ ሆይ?" +date: 09/02/2026 +--- + +የክፋት መዘዝ በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜም ይነሳ ነበር። + +`ኢዮ. 30፡26ን፣ ኤር. 12፡1ን፣ ኤር. 13፡22ን፣ ሚል. 2፡17ን እና መዝ. 10፡1ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ክፋት በሰዎች ልምምድ ውስጥ ዋንኛው ችግር እንደሆነ እንዴት ያሳያሉ?` + +እነዚህ ጥቅሶች ዛሬም የእኛ ጥያቄ የሆኑ ብዙ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። + +ሁልጊዜም ባይሆን በአብዛኛው፣ ክፉዎች የሚበለፅጉና ክፉ የሚሰሩ በክፋታቸው የሚጠቀሙ የሚመስሉት ለምንድነው? ጻድቃን ሲበዛ የሚሰቃዩት ለምንድን ነው? ክፋት ሲፈፀም እግዚአብሔር የት ነው ያለው? አንዳንዴ እግዚአብሔር ከእኛ የራቀ፣ እንዲያውም የተሰወረ፣ የሚመስለው ለምንድነው? + +ስለ እነዚህ ጥያቄዎችና ስለ ክፋት መዘዝ ምንም ብንናገር፣ ክፋትን አለማቃለላችንን እርግጠኛ መሆን አለብን። በዓለም ላይ ያለውን የክፋት ዓይነት ወይም መጠን በማቅለል ችግሩን ለመፍታት መሞከር የለብንም። ክፋት በጣም መጥፎ ነው፣ እግዚአብሔርም ከእኛ ይልቅ ይጠላዋል። ስለዚህ በዓለም ላይ ካለው ብዙ ክፋትና ኢ-ፍትሃዊነት የተነሳ፣ በቃሉ ውስጥ ከሚገኘው “እስከ መቼ ጌታ ሆይ?” ከሚለው ጩኸት ጋር ልንቀላቀል እንችላለን። + +`ማቴ. 27:46ን ያንብቡ። እነዚህን የኢየሱስን ቃላት እንዴት ይረዷቸዋል? ክፋት እግዚአብሔርን በሚገርም መልኩ እንዴት እንደጎዳው ምን ያስተላልፋሉ?` + +በመስቀል ላይ ኢየሱስ ራሱ “አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውከኝ?” (ማቴ. 27፡46) በማለት ይጠይቃል። እዚህ ላይ በተለየ ሁኔታ እግዚአብሔር ራሱ በክፋት እንደተጎዳ እናያለን። ይህም አስደናቂ እውነት፣ የአለም ሁሉ ክፋት በእርሱ ላይ ተጭኖ፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሰቃየቱና በመሞቱ ጎልቶ ይታያል። + +እንዲህም ቢሆን ግን ተስፋ አለ። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገው ነገር፣ የክፋት ምንጭ የሆነውን ሰይጣንን አሸንፏል፤ በመጨረሻም ክፋትን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። ኢየሱስ እነዚህን ቃላት ከመዝ. 22:1 የጠቀሰ ሲሆን፣ የቀረው የመዝሙሩ ክፍል ደግሞ በድል አድራጊነት ይጠናቀቃል። + +`ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ፣ በዚያን ጊዜ ማየት የማይችለውን ተስፋ ወደፊት ተመለከተ። እኛም ከፊታችን ተስፋ አልታየን ሲል፣ ከእርሱ ተሞክሮ መፅናናትን ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/03.md b/src/am/ss/2025-01/07/03.md new file mode 100644 index 0000000000..ec7d2780fa --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/03.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: "የማናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ" +date: 10/02/2026 +--- + +ፍቅር በክፋት ላይ ድል የሚያደርግበት የታሪክ ፍጻሜ ይመጣል። + +`እስከዚያው ድረስ ግን ብዙ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ስለ ክፋት አስቸጋሪነት ጠቃሚ ሊሆን በሚችል መልኩ ማሰብና መነጋገር እንዴት እንችላለን? ኢዮብ 38:1–12ን ያንብቡ። አምላክ ለኢዮብ የሰጠው መልስ የክፋትን ምስጢር እንድናስተውል እንዴት ይረዳናል? ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚሆነውን ምን ያህል እናውቃለን? ምን ያህልስ አናውቅም?` + +በታሪኩ ውስጥ፣ ኢዮብ ብዙ ስቃይ ደርሶበት ስለነበር፣ እጅግ ክፋትና መከራ ለምን እንደደረሰበት ብዙ ጥያቄዎችን አንስቷል። ከመጋረጃው በስተጀርባ በሰማያዊው ዙፋን የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ሳያውቅ፣ ለጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት እግዚአብሔርን ለማነጋገር ጠይቋል (ኢዮብ 1–2ን ይመልከቱ)። + +እግዚአብሔር ለኢዮብ የሰጠው ምላሽ አስደናቂ ነው። በተለይ “እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፡- ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?” (ኢዮ. 38:1, 2)። + +አንድ ትርጉም “ትንሽ የምታውቅ ሆኖ ሳለ ብዙ የምታወራው ለምንድን ነው?” ሲል ገልጾታል (ኢዮ. 38:2)። እግዚአብሔር በኢዮ. 38፡4 ላይ “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር” ሲል ያክላል። + +`ኢዮ. 42:3ን ያንብቡ። የኢዮብ ምላሽ ለራሳችን ስላለን ግምት ምን እንድናስተውል ይረዳናል?` + +እግዚአብሔር ለኢዮብ በሰጠው ምላሽ፣ ኢዮብ ያላወቃቸውና ያልተረዳቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ግልጽ አድርጎለታል። ልክ እንደ ኢዮብ፣ ከመጋረጃው ጀርባ ምንም የማናውቃቸው በዓለም ውስጥ እየሆኑ ያሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ በትሕትና ልንገነዘብ ይገባናል። ለጥያቄዎቻችን መልሱ ምን እንደሆነ አለማወቃችን፣ ጥሩ መልስ የለም ማለት አይደለም አንድ ቀን ሁሉም ነገር መፍትሄ ያገኛልና። እስከዚያው ድረስ በብዙ መንገድ የተገለጠልንን የእግዚአብሔርን መልካምነት ልንታመን ይገባናል። + +ስለማንኛውም ነገር የምናውቀው ምን ያህል ትንሽ እንደሆነ ያስቡ። ታዲያ ለምንድነው በጣም ከባድ ስለሆኑት የክፋትና ስቃይ ጉዳዮች ካልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ጋር መኖርን መለማመድ ያለብን? \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/04.md b/src/am/ss/2025-01/07/04.md new file mode 100644 index 0000000000..78fd184126 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/04.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ብልሁ አማኝ +date: 11/02/2026 +--- + +በኢሳ. 55:8, 9 ላይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- “አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።” + +`የእግዚአብሔር ሃሳብ ከኛ ሃሳብ ይልቅ እጅግ ከፍ ያለ ነው። በታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን እቅድ ረቂቅነት መገመት እንኳን አንችልም። ከዚህ አንጻር፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አምላክ ለሚሠራው ወይም ለማይሠራው ነገር ምክንያቶቹ ምን እንደሆኑ ለማወቅ እንድንችል የምንጠብቀው ለምንድን ነው?` + +እኛ የምናውቀው ትንሽ መሆኑን በመገንዘብ ላይ የተመሰረተ የክፋትን አስቸጋሪነት የምንፈታበት አንዱ መንገድ “ብልሁ (ጠርጣራው) አማኝ” በመባል ይታወቃል። ብልሁ አማኝ እግዚአብሔር ለሚያደርገው ነገር በቂ ምክንያቶች እንዳሉት የሚያምን ነው። ነገርግን ካለን ውስን እውቀት አንጻር፣ እነዚህ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለማወቅ መጠበቅ የለብንም። ብልሁ አማኝ በዚህ ዓለም ውስጥ ካለው ክፋት የተነሳ፣ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክንያቶች ለማወቅ ወይም ለመረዳት አቅም የላቸውም ብሎ ያምናል። ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በዙሪያችን በአየር ላይ ያሉትን ጀርሞች ማየት ስለማይችል፣ ጀርሞቹ የሉም ማለት አይደለም። አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ካላወቀ፣ በርግጥም እግዚአብሔር በቂ ምክንያቶች የሉትም ማለት አይደለም። + +`መዝ. 73ን ያንብቡ። ዘማሪው በዙሪያው ያለውን ክፋትና ኢ-ፍትሃዊነት የሚያስተውለው እንዴት ነው? ግንዛቤውን እንዲቀይር ያደረገውን ምንን አየ?` + +ዘማሪው በዓለም ላይ በነበረው ክፋት ይተክዝ ነበር። ዙሪያውን ሲመለከት ክፉዎች ሲበለጽጉ አየ። ሁሉም ነገር ኢ-ፍትሃዊና ሚዛናዊ ያልሆነ መሰለው። + +የሚሰጠው መልስም አልነበረውም። አምላክን ማመንና ማገልገል ተገቢ ነው ወይ ብሎ ጠየቀ። ይህም የሆነው ወደ መቅደሱ እስኪመለከት ድረስ ነው። + +መቅደሱ የክፋትን ችግር ለመፍታት የቁልፉ አንድ ክፍል ነው—ይህም በራሱ ጊዜ ፍትሕንና ፍርድን የሚያመጣ ጻድቅ ዳኛ እንዳለ መገንዘብ ነው። + +`ስለ ፍርዱና ስለ መቅደሱ አስተምህሮዎች አድቬንቲስቶች ያላቸው መረዳት የክፋትን ምስጢር ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል? ምንም እንኳን አሁን ብዙ ጥያቄዎች ያሉን ቢሆንም፣ የታሪክም ሆነ የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርዶች ዝርዝር በመጨረሻ እንደሚገለጡ ማወቁ ለርሶ ጠቃሚ ነውን?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/05.md b/src/am/ss/2025-01/07/05.md new file mode 100644 index 0000000000..905068dd2c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/05.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: የምርጫ ነፃነት አመክንዮ +date: 12/02/2026 +--- + +የእግዚአብሔርን መንገድና ሐሳብ ባንረዳውም፣ ቃሉ የክፋትን አስቸጋሪነት ለመፍታት የሚረዱ አንዳንድ ነገሮችን ይገልጻል። የክፋትን ምስጢር ለመፍታት አንዱ መንገድ የምርጫ ነፃነት አመክንዮ በመባል ይታወቃል። + +የምርጫ ነፃነት አመክንዮ፣ ክፋት የምርጫ ነፃነትን ያላግባብ የመጠቀም ውጤት ነው የሚል አመለካከት ነው። እንግዲያውስ ለክፋት ተጠያቂው እግዚአብሔር አይደለም፣ ምክንያቱም ክፋት ፍጡራን እግዚአብሔር ለበጎ የሰጣቸውን የምርጫ ነፃነት ያላግባብ መጠቀማቸው ነውና። ይሁን እንጂ አምላክ እንዲህ ዓይነቱን የምርጫ ነፃነት ለምን ይሰጣል? ይህን በተመለከተ ሲ.ኤስ. ሉዊስ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “የምርጫ ነፃነት፣ ምንም እንኳን ክፋትን ለመሥራት የሚያስችል ቢሆንም፣ ሊኖረን የሚገባውን ማንኛውንም ፍቅር ወይም መልካምነት ወይም ደስታ እንዲኖር የሚያደርገው ብቸኛው ነገር ነው። + +`እንደ ማሽን የሚሠሩ ፍጥረታት ያሉበትን ዓለም- መፍጠር ዋጋ የለውም። ከፍ ላሉ ፍጡራኑ እግዚአብሔር የነደፈው ደስታ፣ ከእርሱና ከእርስ በርሳቸው ጋር በነጻነትና በፈቃዳቸው የመስማማት ደስታ ነው። . . . ለዚህም ደግሞ ነፃ መሆን አለባቸው።”—ተራ ክርስትና (ኒው ዮርክ÷ ማክሚላን፣ 1960)፣ ገጽ. 52. ዘፍ. 2:16, 17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ለአዳምና ለሔዋን የተሰጣቸውን የምርጫ ነፃነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?` + +መጀመሪያውኑ የምርጫ ነፃነት ካልነበራቸው በስተቀር ለምን ያዛቸዋል? አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ በሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምድራችን በክፋት ተሞልታለች። ከውድቀት ታሪክ ቀጥሎ ባለው በዘፍ. ምዕራፍ 4 ውስጥ የኃጢአት አስከፊ ውጤት አቤል በወንድሙ በመገደሉ ይታያል። የውድቀት ታሪክ አዳምና ሔዋን የምርጫ ነፃነታቸውን ያላግባብ በመጠቀማቸው ኃጢአትና ክፋት ወደ ምድራችን እንዴት እንደመጣ ያሳያል። + +በቃሉ ውስጥ የምርጫ ነፃነትን እውነታ እናያለን (ዘዳ. 7:12, 13ን፤ ኢያ. 24:14, 15ን፤ መዝ. 81:11–14ን፤ እና ኢሳ. 66:4ን ይመልከቱ)። ይብዛም ይነስም በሕይወታችን በእያንዳንዷ ቀን ፈጣሪ የሰጠንን የምርጫ ነፃነት እንጠቀማለን። + +`የምርጫ ነፃነት ከሌለን ሰው አንሆንም ነበር። እኛ ማሽን ወይም ደግሞ አእምሮ የሌለው ሮቦት እንመስል ነበር። የሶኒ ኮርፖሬሽን አይቦ የሚባል የሮቦት ውሻ ፈጥሯል። እውነተኛ ውሻ ይመስላል ነገር ግን አይታመምም፣ በቁንጫዎች አይጠቃም፣ አይናከስም፣ መርፌ አይወጋም፣ ፀጉርም አያረግፍም። ታዲያ ትክክለኛ ውሻህን በአይቦ ትለውጠዋለህ? ካልሆነ፣ የአንተ ምርጫ፣ ምንም እንኳን አደጋ ቢኖረውም እግዚአብሔር ለምን የምርጫ ነፃነት እንዲኖረን አድርጎ እንደፈጠረን የተሻለ እንድትገነዘብ የሚረዳህ እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/06.md b/src/am/ss/2025-01/07/06.md new file mode 100644 index 0000000000..dfcc68b8a7 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ፍቅር እና ክፋት? +date: 13/02/2026 +--- + +እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ስለሆነ፣ ለፍጡራኑ የምርጫ ነፃነትን ሰጥቷል። ይህንን የምርጫ ነፃነት ያላግባብ መጠቀም ደግሞ የክፋት መንስኤ ነው። አሁንም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። እግዚአብሔር ክፋትን አምርሮ ቢጠላውም፣ ለጊዜውም ቢሆን እንዲኖር ይፈቅዳል ምክንያቱም የመከሰት ዕድሉን መከልከል የፍቅር ባሕርይ ስላልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋትም ደግሞ ለፍቅር አስፈላጊ የሆነውን መተማመንን ስለሚጎዳ ነው። + +“እግዚአብሔርን ባለማወቅ ምድር ጨልማ ነበር። የጨለማው ግርዶሽ እንዲበራ፣ ዓለምም ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ፣ የሰይጣን የማታለል ኃይል መክሸፍ ነበረበት። ይህም በጉልበት ሊሆን አይችልም። ኃይልን መጠቀም ከእግዚአብሔር መንግሥት መርሆዎች ጋር ተጻራሪ ነው። እርሱ የሚፈልገው የፍቅርን አገልግሎት ብቻ ነው፤ ፍቅርም ሊገደድ አይችልም፤ በጉልበትም ሆነ በሥልጣን ሊገኝ አይችልም። ፍቅር የሚቀጣጠለው በፍቅር ብቻ ነው። + +እግዚአብሔርን ማወቅ እርሱን መውደድ ነው፤ የእርሱ ባሕርይ ከሰይጣን ባሕርይ አንፃር መገለፅ አለበት።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 22. + +ያለምርጫ ነፃነት ፍቅር ሊኖር አይችልም። እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ ፍቅር እንዲኖር አስፈላጊ የሆነውን ነፃነት መከልከል ለእግዚአብሔር አማራጭ እንዳልሆነ ግልጽ ይመስላል። እንደ እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው የምናውቅ ብንሆን ብለን ብናስብ፣ ነፃነታችንን እንዲነሳን አንፈልግም ነበር። + +ደግሞስ ፍቅር በሌለበት ዓለም ውስጥ መኖር የሚፈልግ ማን ነው? ሮሜ 8:18ን እና ራዕ. 21:3, 4ን ያንብቡ። በዓለማችን ውስጥ ብዙ ክፋት ቢኖርም፣ እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሔር መልካምነት እንድንተማመን የሚያደርጉን እንዴት ነው? + +`በጨለማው ውስጥ ማየት ባንችልም፣ እግዚአብሔር መጨረሻውን ከመጀመሪያው ይመለከታል። ደግሞም በኢየሱስ ለሚያምኑ ሁሉ ተስፋ የተሰጣቸውን ዘላለማዊ ደስታ ማየት ይችላል። በሮሜ 8፡18 ላይ፡- “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ” ይላል። ይህን አስደናቂ ተስፋ ለማመን እምነት አለን?` + +`በተጨማሪም ፍቅርና ከፍቅር ጋር የተቆራኘው የምርጫ ነፃነት በጣም የተቀደሰና መሰረታዊ ስለሆነ፣ እኛን ከሚከለክለን ይልቅ፣ ኢየሱስን ብዙ ስቃይ ወደሚቀበልበት ወደ መስቀል እንደሚያመራው ያውቅ ነበር። የሚያስከፍለውን ዋጋ እያወቀም ቢሆን ይህንን ነፃነት ሰጠን። ለምንድነው ይህ ሁልጊዜ ልናስላስለው የሚገባ ወሳኝ ሐሳብ የሆነው? እግዚአብሔር የምርጫ ነፃነት የሰጠን መሆኑን ማሰላሰላችን፣ የሚሆነው ነገር ሁሉ የአምላክ ፈቃድ ነው ብለን እንዳናስብ የሚጠብቀን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/07.md b/src/am/ss/2025-01/07/07.md new file mode 100644 index 0000000000..9dc402c79b --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/07.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 14/02/2026 +--- + +አበውና ነቢያት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ኃጢአት ለምን ተፈቀደ?” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 33-43 ያንብቡ። + +“ከሰማይ ቢጣልም እንኳን፣ አምላክ በጥበቡ ሰይጣንን አላጠፋውም። + +በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው የፍቅር አገልግሎት ብቻ ስለሆነ፣ የፍጡራኑ ታማኝነት በርሱ ፍትሕና ደግነት ላይ በማመን መመስረት አለበት። የሰማይና የዓለማት ነዋሪዎች፣ የኃጢአትን ምንነት ወይም መዘዝ ሊረዱ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ስለነበሩ፣ ያኔ ሰይጣንን ቢያጠፋው ኖሮ የእግዚአብሔርን ፍትሓዊነት ማየት ባልቻሉም ነበር። እርሱን ወዲያውኑ ቢደመስሰው ኖሮ፣ አንዳንዶች በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት እግዚአብሔርን ያገለግሉ ነበር። የአሳቹ ተጽእኖ ወይም የዓመፅ መንፈስ ሙሉ በሙሉ ባልጠፋ ነበር። ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ጥቅም ሲባል፣ በመለኮታዊው መንግሥት ላይ የሰነዘራቸው ክሶች በሁሉም ፍጥረታት ዘንድ በእውነተኛው ብርሃን እንዲታዩ፣ የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ምሕረትና የማይለወጠው ሕጉ ለዘላለም ጥያቄ እንዳይነሳባቸው፣ የሰይጣን መርሆዎች ፍሬ ማፍራት ነበረባቸው። + +“ስለ ኃጢአት ምንነትና ስለ አስፈሪ ውጤቶቹ ዘላለማዊ ምስክር ይሆን ዘንድ፣ የሰይጣን አመጽ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ትምህርት መሆን ነበረበት። የሰይጣን አሰራርና በሰዎችም ሆነ በመላእክት ላይ ያለው ውጤት መገለጡ፣ መለኮታዊውን ሥልጣን ወደ ጎን የመተው ፍሬ ምን እንደሚሆን ያሳያል። + +የፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ ደህንነት የተንጠለጠለው በእግዚአብሔር መንግሥት መኖር መሆኑን ይመሰክራል። ስለዚህ ይህ የዓመፅ አስከፊው ታሪክ ቅዱሳንን ሁሉ በመተላለፍ እንዳይታለሉ፣ ኃጢአት እንዳይሰሩና በቅጣቱ እንዳይሰቃዩ ለዘላለም ይጠብቃቸዋል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ አበውና ነቢያት፣ ገጽ 42, 43 + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. “ቲዮደሲ (Theodicy)” ማለት ክፋትም ቢኖር እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው ማለት ነው። ነገር ግን ለክፋት መኖር ምክንያት አያቀርብም። በሰማይ አንድ ሰው እንዲህ አለ ብለህ አስብ፣ “ኦ! አዎ ኢየሱስ፣ አሁን ቤተሰቦቼ በፊቴ ለምን እንደተሰቃዩና እንደተገደሉ ገብቶኛል። አዎ አሁን ሁሉም ነገር ትርጉም ይሰጣል። አመሰግናለሁ ኢየሱስ!” ይህ ልክ አይደለም። በታላቁ ተጋድሎ በስተመጨረሻ ነጻ የሚሆነው እግዚአብሔር እንጂ ክፋት እንዳልሆነ እንዴት ልንረዳ እንችላለን? (ትምህርት ዘጠኝን ይመልከቱ)` + +`2. እንደ ኢዮብ ያለ ስሜት ተሰምቶህ ያውቃል? አንተ ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ለደረሰባቸው ሥቃይ አሳማኝ ማብራሪያ ሊኖር አይችልም ብለህ ለማሰብ ተፈትነህ ታውቃለህ? ኢዮብ በመጨረሻ “የማያስተውለውን ነገር እንደተናገረ” መገንዘቡ (ኢዮ. 42: 3)፣ ጥያቄዎቻችንን ለማስተዋል የሚረዳን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/07/info.yml b/src/am/ss/2025-01/07/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..7ab92f5c70 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/07/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "የክፋት መከሰትና መዘዙ" + start_date: "08/02/2026" + end_date: "14/02/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/01.md b/src/am/ss/2025-01/08/01.md new file mode 100644 index 0000000000..f0f035da16 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/01.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: የምርጫ ነጻነት ፍቅር እና መለኮታዊው ችሮታ +date: 15/02/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ሉቃ. 13፡34፣ ኤር. 32:17– 20፣ ዕብ. 1:3፣ ዘዳ. 6:4, 5፣ ኤፌ. 1:9–11፣ ዮሐንስ 16፡33። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ::” ዮሐንስ 16፡33 + + +የአምላክ ችሮታ (ፍቃድ) በአለም ውስጥ የእግዚአብሔርን ምግባር ለመግለጽ የሚያገለግል ቃል ነው። ስለ እግዚአብሔር ችሮታ ያለን አስተሳሰብ፣ ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት እና ስለ ክፋት መከሰትና መዘዝ ባለን እይታ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። + +ክርስቲያኖች ስለ መለኮታዊው ችሮታ የተለያዩ ግንዛቤዎች አሏቸው። አንዳንዶች እግዚአብሔር ኃይሉን ሁሉም ክስተቶች ባሉበት እንዲፈጸሙ በሚወስን መልኩ እንደሚጠቀም ያምናሉ። ማን እንደሚድን እና ማን እንደሚጠፋ ሳይቀር ይመርጣል! በዚህ አመለካከት ሰዎች እግዚአብሔር ከወሰነው ውጭ የመምረጥ ነፃነት የላቸውም። እንዲያውም ይህንን የሚያምኑ ሰዎች የሰው ፍላጎት እንኳን በእግዚአብሔር ይወሰናል ብለው ይከራከራሉ። + +በአንጻሩ አሳማኝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት እግዚአብሔር የሚሆነውን ነገር ሁሉ አስቀድሞ አይወስንም። ይልቁንም ከእርሱ ፈቃድ ውጭ ለመኖር እንኳን እስኪመርጡ ድረስ ለሰዎች (ለመላዕክትም ጭምር) የመምረጥ ነፃነትን ይሰጣል። የውድቀት፣ የኃጢያትና የክፋት ታሪክ ይህንን የምርጫ ነፃነት ያላግባብ የመጠቀም ውጤት አስደናቂና አሳዛኝ ማሳያ ነው። + +የምርጫ ነጻነት፣ ፍቅር እና መለኮታዊው ችሮታ የደህንነት እቅድ የተዘጋጀው የምርጫ ነፃነትን ያላግባብ መጠቀም ያስከተለውን አሳዛኝ ሁኔታ ለማስተካከል ነው። +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/02.md b/src/am/ss/2025-01/08/02.md new file mode 100644 index 0000000000..32a7f2f3c2 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/02.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ሉዓላዊው አምላካችን +date: 16/02/2026 +--- + +`አንድ የልጆች ቄስ "እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው" ሲል የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎቹን ቡድን ያስተምራል። "ይህ ማለት የሚሆነውን ሁሉ እርሱ ይቆጣጠራል ማለት ነው።" ግራ የተጋባ አንድ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ፡- “ታዲያ ውሻዬ ሲሞት እግዚአብሔር ይቆጣጠር ነበር? እግዚአብሔር ውሻዬን ለምን ይገድለዋል?` + +ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የልጆቹ ቄስ እንዲህ አለ፡- “ይህ ከባድ ነው። + +ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች እንድናልፍ አድርጎ ለወደፊት ይበልጥ አስቸጋሪ ለሆኑ ነገሮች ዝግጁ እንድንሆን ያደርገናል። ውሻዬ ሲሞት ምን ያህል ከባድ እንደነበር አስታውሳለሁ። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ማለፌ በኋላ አያቴ በሞተችበት ወቅት የገጠመኝን የባሰ አስቸጋሪ ጊዜ እንድቋቋም ረድቶኛል። ይህ ትርጉም ይሰጥሃል?” + +ከረዥም ፀጥታ በኋላ፣ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪው እንዲህ ሲል መለሰ፡- “ስለዚህ አያቴን ሲገድላት ዝግጁ እንድሆን ነው እግዚአብሔር ውሻዬን የገደለው?”— ማርክ ኮርቴዝ፣ በጆን ሲ. ፔካም የተጠቀሰ፣ መለኮታዊ ባሕርያት፡- የመጽሐፍ ቅዱሱን የኪዳን አምላክ ማወቅ (ሚቺጋን፡- ቤከር አካዳሚክ፣ 2021)፣ ገጽ. 141. + +`ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የሚሆነው ነገር ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር እንዲሆን በሚፈልገው መልኩ ነው ብለው ያስባሉ። በዓለም ላይ የሚሆነው ማንኛውም ነገር እግዚአብሔር እንዲሆን ስለፈለገ ነው ይላሉ። ደግሞም እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። ታዲያ እግዚአብሔር እንዳይሆን የሚፈልገው ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል? ስለዚህ ምንም ያህል መጥፎ ቢሆን፣ የሚሆነው ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ቢያንስ የዚህ ሥነ-መለኮት አስተምሮ የሚያስተምረው ይህንን ነው። መዝ. 81:11–14ን፣ ኢሳ. 30:15, 18ን፣ ኢሳ. 66:4ንና ሉቃ. 13:34ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የሚሆነው ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ወይ ለሚለው ጥያቄ ምን ይላሉ?` + +ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚፈልገውን ያደርጋል ብለው ቢያምኑም፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ግን የተለየ ታሪክ ነው። ቃሉ በተደጋጋሚ እግዚአብሔር ያልተፈጸሙ ምኞቶች እንዳሉት ይገልፃል። ይህ ማለት ብዙ ጊዜ የሚሆነው ነገር፣ እግዚአብሔር እንዲሆን ከሚፈልገው ነገር ተቃራኒ ነው። በብዙ አጋጣሚዎች እግዚአብሔር እየሆነ ያለው ነገር እሱ ከሚፈልገው ተቃራኒ መሆኑን በግልፅ ይናገራል። እርሱ ለሕዝቡ አንድ ነገር እንዲሆንላቸው ፈለገ፣ እነርሱ ግን በምትኩ ሌላ መረጡ። እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ሲል አዘነ:- “ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም…። ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፣ እሥራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆ፣ ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር” (መዝ. 81፡11, 13, 14)። + +`የሚሆነው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው የሚለውን ማንኛውንም የሥነ-መለኮት ትምህርት አንድምታ ያሰላስሉ። እንዲህ ዓይነቱ አስተምህሮ፣ በተለይም ከክፋት አውድ አንጻር፣ምን አይነት የተወሳሰቡ ችግሮችን ይፈጥራል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/03.md b/src/am/ss/2025-01/08/03.md new file mode 100644 index 0000000000..67c75f01c8 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/03.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ሁሉን ቻይ +date: 17/02/2026 +--- + +በቃሉ ውስጥ የእግዚአብሔር አስደናቂ ኃይል ተገልጧል። መጽሐፍ ቅዱስ ኃይሉን ተጠቅሞ ስለ ሰራቸው እጅግ ብዙ ተአምራቶች ይተርካል። ይህም ቢሆን እግዚአብሔር እንዲሆኑ የማይፈልጋቸው ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። + +`ራዕ. 11:17ን፣ ኤር. 32:17–20ን፣ ሉቃ. 1:37ን እና ማቴ. 19:26 የንብቡ። በተጨማሪም ዕብ. 1:3ን ይመልከቱ። እነዚህ ክፍሎች ስለ እግዚአብሔር ኃይል ምን ያስተምራሉ?` + +እነዚህና ሌሎች ጥቅሶች እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነና ዓለምን በኃይሉ እንደሚደግፍ ያስተምራሉ። በእርግጥም ራዕይ ደጋግሞ እግዚአብሔርን “ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ” ሲል ይጠቅሰዋል (ለምሳሌ፡- ራዕ. 11:17፤ ከ2ቆሮ. 6:18፣ ራዕ. 1:8፣ ራዕ. 16:14፣ ራዕ. 19:15፣ ራዕ. 21:22 ጋር ያስተያዩ)። “ሁሉን ቻይ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል ፓንቶክርተር ፍቺው “በሁሉም ላይ ሥልጣን ያለው” ማለት ነው። የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት በቃላት ብቻ የተረጋገጠ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት ወይም በአለም ላይ በተአምር ጣልቃ ለመግባት ኃይሉን በሚጠቀምበት ብዙ አስደናቂ አጋጣሚዎች ውስጥ ተገልጧል። + +ይሁን እንጂ እግዚአብሔር “ሁሉን ቻይ ነው” ማለት ማንኛውንም ነገር ያደርጋል ማለት አይደለም። ቃሉ እግዚአብሔር የማያደርጋቸው አንዳንድ ነገሮች እንዳሉ ያስተምራል፤ ለምሳሌ፡- 2 ጢሞ. 2፡13 እግዚአብሔር “ራሱን ሊክድ አይችልምና” ይላል። + +በዚህ መሠረት፣ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እንደሆነ ይስማማሉ፣ ይህ ማለት እግዚአብሔር ተቃርኖ የሌለበትን ማንኛውንም ነገር የማድረግ ኃይል አለው ማለት ነው — ማለትም ምክንያታዊ የሆነና ከእግዚአብሔር ማንነት ጋር የሚስማማ ማንኛውንም ነገር ያደርጋል። አንዳንድ ነገሮች ለእግዚአብሔር የማይቻሉት ተቃርኖ የሚያመጡ ሲሆኑ እንደሆነ በክርስቶስ የጌቴሴማኒ ጸሎት ላይ በግልጽ ይታያል። ክርስቶስ “በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል” (ማቴ. 19፡26) ብሎ ቢያረጋግጥም፣ ስቅለቱ ሲቃረብ ደግሞ ወደ አባቱ እንዲህ ሲል ጸለየ፡- “አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ” (ማቴ. 26፡39)። + +እርግጥ ነው፣ አብ ክርስቶስን በመስቀል ላይ እንዳይሰቃይ ለማዳን ከፍተኛ ኃይል ነበረው፣ ነገር ግን ኃጢአተኞችን ለማዳን ሲል ይህንን ማድረግ አይችልም ነበር። ሁለቱም ሳይሆኑ፣ አንዱ ወይም ሌላኛው መሆን ነበረበት። + +`ደግሞም እግዚአብሔር ሁሉን ማዳን እንደሚፈልግ ቃሉ ያስተምራል (ለምሳሌ፡- 1ጢሞ. 2፡4–6፣ ቲቶ 2፡11፣ 2 ጴጥ. 3፡9፣ ሕዝ. 33፡ 11)፤ ነገር ግን ሁሉም አይድኑም። ይህ እውነታ ስለ ምርጫ ነፃነትና የምርጫ ነፃነት ለተሰጣቸው ፍጡራን የእግዚአብሔር ኃይል ውስንነት ምን ያስተምራል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/04.md b/src/am/ss/2025-01/08/04.md new file mode 100644 index 0000000000..18a2e4c21f --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/04.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: እግዚአብሔርን ውደድ +date: 18/02/2026 +--- + +እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ምክንያታዊ ያልሆነውን ያደርጋል ማለት አይደለም። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር አንድን ሰው በዘፈቀደ በራሱ ምርጫ እንዲወደው ሊወስን አይችልም። ባጭሩ፣ አስቀድመን እንዳየነውና በድጋሚ አፅንዖት መስጠት የሚገባን—እግዚአብሔር ማንንም ሰው እንዲወደው አያስገድድም፤ ግዳጅ ከተጨመረበት፣ ፍቅር ፍቅር ሊሆን አይችልም። + +`ማቴ. 22:37ንና ዘዳ. 6:4, 5ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለምርጫ ነፃነት እውነታ ምን ያስተምራሉ?` + +እግዚአብሔርን ውደድ የሚለው ታላቁ ትእዛዝ፣ እግዚአብሔር በእርግጥም ሁሉም ሰው እንዲወደው እንደሚፈልግ ያስረዳል። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰው እግዚአብሔርን አይወደውም። ታዲያ ለምንድነው አምላክ ሁሉም ሰው እንዲወደው የማያደርገው? ምክንያቱም ፍቅር፣ ፍቅር እንዲሆን፣ እንዲሁ በነፃ መሰጠት ስላለበት ነው። + +`ዕብ. 6:17, 18ንና ቲቶ 1:2 ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ምን ያስተምራሉ?` + +በዘኍ. 23፡19 መሠረት፡- “ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም” ይላል። እግዚአብሔር ፈጽሞ አይዋሽም (ቲቶ 1: 2)፤ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ቃሉን ይጠብቃል፣ የገባውንም ተስፋ አያጥፍም (ዕብ. 6:17, 18)። ስለዚህ እግዚአብሔር ተስፋ ከሰጠ ወይም አንድ ነገር ለማድረግ ቃል ከገባ፣ የወደፊት ድርጊቱ በተስፋው ላይ የተወሰነ ነው። + +ይህ ማለት እግዚአብሔር ከሚፈልገውም ውጭ እንዲመርጡ ለፍጡራኑ የምርጫ ነፃነትን እስከ ሰጠ ድረስ፣ ሰዎች የሚመርጡት የእግዚአብሔር ኃላፊነት (ጉዳይ) ሊሆን አይችልም። + +የምርጫ ነጻነት፣ ፍቅር እና መለኮታዊው ችሮታ ቃል ከገባ፣ ሰዎች ከአምላክ ምኞት ጋር በሚፃረር መንገድ ነፃነታቸውን የመጠቀም ችሎታ አላቸው። የሚያሳዝነው፣ ብዙ ሰዎች ነፃነታቸውን በዚህ መንገድ ያላግባብ ይጠቀማሉ፤ በዚህም መሠረት እግዚአብሔር እንዲሆኑ የማይፈልጋቸው ብዙ ነገሮች ይፈፀማሉ፣ ነገር ግን ለእነዚህ እግዚአብሔር ተጠያቂ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም አይመለከተውምና። + +`እግዚአብሔር እንዲያደርጉ የማይፈልገውን ምን ነገር አድርገዋል? ይህ ስለ ምርጫ ነፃነት እውነታና ስለ አስፈሪ ውጤቶቹ ምን ያስተምረናል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/05.md b/src/am/ss/2025-01/08/05.md new file mode 100644 index 0000000000..dced277062 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/05.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ እና የመፍትሄ ፈቃድ +date: 19/02/2026 +--- + +`ኤፌ. 1:9–11ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ አስቀድሞ ስለ መወሰን ምን እያለ ነው? አንዳንድ ሰዎች ለመዳን፣ ሌሎች ደግሞ ለመጥፋት አስቀድመው ተወስነዋል?` + +በዚህ ጥቅስና በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች “አስቀድሞ መወሰን” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል (ፕሮኦሪዞ) አምላክ ታሪክን በምክንያት ይወስናል ብሎ አያስተምርም። ከዚህ ይልቅ የግሪኩ ቃል “ሳይሆን በፊት መወሰን” ማለት ነው። + +እርግጥ ነው፣ አንድ ሰው በራሱ አንድን ነገር አስቀድሞ ሊወስን ይችላል፣ ወይም የሌሎችን ነፃ ውሳኔ ግምት ውስጥ በማስገባት አንድን ነገር አስቀድሞ ሊወስን ይችላል። እግዚአብሔር የኋለኛውን አማራጭ ተጠቅሞ እንደሚሰራ ቃሉ ያስተምራል። + +በኤፌ. 1:9–11ና በሌሎች ቦታዎች (ለምሳሌ ሮሜ 8:29, 30) “አስቀድሞ ወሰነ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል እግዚአብሔር አስቀድሞ የሚያውቀውን የፍጡራኑን ነፃ ውሳኔ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደፊት ያቀደውን ያመለክታል። + +ስለዚህ ለእውነተኛ የፍቅር ግንኙነት የሚያስፈልገውን የፍጡራንን ነፃነት እያከበረ፣ እግዚአብሔር በፈቃዱ ታሪክን ለሁሉም ወደሚመኘው በጎ ዓላማ መምራት ይችላል። + +`ኤፌ. 1፡11 እግዚአብሔር “እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን እንደሚሰራ” ይናገራል። ይህ ማለት እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደፈለገው እንዲሆን ይወስናል ማለት ነው? ኤፌ. 1፡9–11 ለብቻው ተነጥሎ ሲነበብ፣ ይህን አመለካከት የሚደግፍ ሊመስል ይችላል። ሆኖም ይህ አተረጓጎም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ” እንደማይቀበሉ የሚያሳዩትን ቀደም ሲል ያየናቸውን ብዙ ጥቅሶች ይቃረናል (ሉቃ. 7፡30፤ ከሉቃ. 13፡34ና መዝ. 81፡11-14 ጋር ያስተያዩ)። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን ካልተቃረነ በስተቀር፣ እነዚህን ክፍሎች እርስ በርሳቸው እንዲስማሙ ሆነው እንዴት ሊስተዋሉ ይችላሉ?` + +አንድ ሰው በእግዚአብሔር “በጎ ፈቃድ” (ideal will) እና በእግዚአብሔር “የመፍትሔ ፈቃድ” (remedial will) መካከል ያለውን ልዩነት ከተገነዘበ ይህ ክፍል ትርጉም ይሰጠዋል። የእግዚአብሔር “በጎ ፈቃድ” እግዚአብሔር እንዲሆን የሚፈልገው ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው እያንዳንዱ ሰው ሁልጊዜ እግዚአብሔር የሚሻውን በትክክል ካደረገ ነው። በሌላ በኩል የእግዚአብሔር “የመፍትሔ ፈቃድ” አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ከሚመርጠው ውጭ የሚሆነውን የፍጡራንን ነፃ ውሳኔ ጭምር ያገናዘበ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ኤፌ. 1:11 የሚናገረው የአምላክን “የመፍትሔ ፈቃድ” ነው። + +እግዚአብሔር ስለ ወደፊቱ ያለው እውቀት አስደናቂ ከመሆኑ የተነሳ፣ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ምርጫዎች ሁሉ እያወቀ - መጥፎ ምርጫዎችን ጨምሮ - "ነገር ሁሉ ለበጎ" እንዲሆን ማድረግ ይችላል (ሮሜ 8:28)። + +`ከዚህ እውነት ምን ማጽናኛ ማግኘት ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/06.md b/src/am/ss/2025-01/08/06.md new file mode 100644 index 0000000000..87ac7b7f74 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/06.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ክርስቶስ ዓለምን አሸንፏል +date: 20/02/2026 +--- + +ሁሉም ነገር እንደ እግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖ ቢሆን ኖሮ፣ ፍጹም የሆነ የፍቅርና የስምምነት ደስታ ብቻ እንጂ ክፋት በፍፁም አይኖርም ነበር። + +በመጨረሻ አለማት ወደዚህ ፍጹምና በጎ የሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይመለሳሉ። እስከዚያው ድረስ ግን እግዚአብሔር የፍጡራኑን ነፃ ውሳኔ ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ፈቃዱን እየፈፀመ ነው። + +ሁሉም ተሳታፊዎች የተወሰኑ ንጥረ ነገሮችን እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ የኬክ መጋገር ውድድርን ያስቡ፣ ነገር ግን የሚፈልጉትን ኬክ ለመጋገር የፈለጉትን ሌላ ማንኛውንም ንጥረ ነገር መጨመር ይችላሉ ። ዞሮ ዞሮ ጋጋሪው የሚሠራው የትኛውም ዓይነት ኬክ፣ በከፊል ጋጋሪው ባልመረጠው አንዳንድ ንጥረ ነገሮች ይወሰናል። + +በተመሳሳይ እግዚአብሔር ለፍቅር አስፈላጊ የሆነውን የፍጡራንን ነፃነት ስለሚያከብር፣ የዓለምን ታሪክ የሚወስኑት ብዙዎቹ “ንጥረ ነገሮች” በእግዚአብሔር የተመረጡ ሳይሆኑ፣ እንዲያውም እግዚአብሔር ከሚፈልገው ተቃራኒዎች ናቸው። + +በዚህ አመለካከት፣ እግዚአብሔር የሚሆነውን ሁሉ ብቻውን የሚቆጣጠር ይመስል፣ መለኮታዊው ችሮታ ዝም ብሎ በአንድ ገፅታ የሚታይ አይደለም። + +ይልቁንስ ይህ የእግዚአብሔር ችሮታ ቢያንስ ባለ ሁለት ገፅታ እይታን ይፈልጋል። በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉ አንዳንድ ነገሮች በእግዚአብሔር የሆኑ ናቸው፣ ሌሎች ክስተቶች ግን የፍጡራን ነፃ ውሳኔ ውጤቶች ናቸው (ሁሉንም ክፋት ጨምሮ)። + +`እግዚአብሔር እንዲሆኑ የማይፈልጋቸው ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። ዮሐ. 16:33ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ በመከራም ውስጥ ቢሆን ምን ተስፋ ይሰጠናል?` + +ሰዎች በምድር ሲኖሩ እግዚአብሔር ከመከራና ከፈተና ሊያድነን ይገባል የሚል የተሳሳተ እምነት ስላላቸው፣ በተለይ በመከራ ወይም በፈተና ጊዜ እምነታቸው ሊናወጥ ይችላል። ነገር ግን ኢየሱስ ለተከታዮቹ በዚህ ዓለም ፈተናና መከራ እንደሚደርስባቸው አስጠንቅቋቸዋል፤ ሆኖም ተስፋ አለን፣ ክርስቶስ ዓለምን አሸንፏልና (ዮሐ. 16፡33)። + +መከራና ፈተና ገጠመን ማለት ግን አምላክ ለእኛ እንዲሆንልን የሚመኘው ይህ ነው ማለት አይደለም። ሁልጊዜም የታላቁን ተጋድሎ እውነታ ማስታወስ አለብን። ሆኖም ግን እርግጠኛ መሆን የምንችለው ነገር፣ ምንም እንኳን ክፋት እንደ ቅድመ ሁኔታ ለበጎ ነገር አስፈላጊ ባይሆንም፣ እግዚአብሔር ከክፉ ክስተቶች ውስጥ እንኳን መልካምን ሊያመጣ ይችላል። በእግዚአብሔር ብንታመን፣ መከራችንንም እንኳን ወደ እርሱ እንድንቀርብና ለሌሎችም እንድንራራላቸውና እንድንጠነቀቅላቸው ለማድረግ ሊጠቀምበት ይችላል። \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/07.md b/src/am/ss/2025-01/08/07.md new file mode 100644 index 0000000000..8c1b0ed564 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/07.md @@ -0,0 +1,26 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 21/02/2026 +--- + +የዘመናት ምኞት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ + +“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 19–26 ያንብቡ። + +“የእኛ የደህንነት እቅድ ከአዳም ውድቀት በኋላ የተነደፈ አልነበረም። + +ይልቅስ ‘ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው‘ ምስጢር ተገለጠ (ሮሜ 16፡25)። ከዘመናት በፊት የእግዚአብሔር ዙፋን መሠረት የሆነው መርህ ተዘረጋ። ገና ከጅምሩ እግዚአብሔር እና ክርስቶስ የሰይጣንን ክህደት እና በአታላዩ አማካኝነት የሰው ዘር እንደሚወድቅ ያውቁ ነበር። ኃጢአት እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፣ ነገር ግን የኃጢአትን መከሰት አስቀድሞ ተመለከተ፣ እናም አስፈሪውን አደጋ ለመቀልበስ ሁኔታዎችን አዘጋጀ። ለዓለማችን የነበረው ፍቅር ታላቅ ስለነበር፣ ‘በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ’ አንድያ ልጁን ለመስጠት ቃል ኪዳን ገባ (ዮሐ. 3፡16)።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 22. + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚፈልገውን የማያገኝ ከሆነ፣ ይህ እውነታ በዓለም ውስጥ ስለሚሆነው ነገር ያለህን አመለካከት እንዴት ይቀይረዋል? እግዚአብሔር ያልተሟሉ ምኞቶች እንዳሉት መረዳት አንድምታው ምንድን ነው?` + +`2. የሐሙሱን የኬክ ምሳሌ ጥናት ከተመለከትን፣ ምንም እንኳን "እግዚአብሔርና ክርስቶስ የሰይጣንን ክህደት ያውቁ የነበረ ቢሆንም"፣ እኛን ለምን እንደፈጠሩን እንረዳለን። ፍቅር ከሚቀላቀሉት ንጥረ ነገርች ውስጥ መሆን ነበረበት፣ ፍቅርም ነፃነትን ይሰጣል። እግዚአብሔር እኛን መውደድ እንድንችል አድርጎ ነው የፈጠረን፣ ነገር ግን ይህ ኢየሱስን ወደ መስቀል እንደሚመራው እያወቀ ነበር ያደረገው። የፍቅር አካል የሆነውን ነፃነት ከሚነፍገን ይልቅ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መከራን መቀበሉ፣ ፍቅር ለእግዚአብሔር መንግሥት ምን ያህል የተቀደሰና መሠረታዊ መሆኑን ይህ ምን ይነግረናል?` + +`3. ብዙ ጊዜ በዚህ አለም ውስጥ ስላለው ክፋትና ስቃይ እናዝናለን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱ በመከራና በክፋት እንደሚያዝን ለማሰላሰል ምን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ? እግዚአብሔር ራሱ በክፋት ምክንያት እንደሚሠቃይ ማወቁ፣ ስለ ክፋትና መከራ ባለዎት መረዳት ላይ ምን ልዩነት ያመጣል?` + +`4. እግዚአብሔር የማይፈልጋቸው ብዙ ነገሮች በዚህ ዓለም ውስጥ የመሆናቸው እውነታ፣ በተለይ ትርጉም የማይሰጥና ምንም ዓይነት መልካም ነገር የማያመጣ የሚመስል ሥቃይ ሲደርስብህ ለመቋቋም የሚረዳህ እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/08/info.yml b/src/am/ss/2025-01/08/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..4a1d0dbd52 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/08/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "የምርጫ ነጻነት ፍቅር እና መለኮታዊው ችሮታ" + start_date: "15/02/2026" + end_date: "21/02/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/01.md b/src/am/ss/2025-01/09/01.md new file mode 100644 index 0000000000..a3a5e58c8f --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/01.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: አለማትን ያካተተው ተጋድሎ +date: 22/02/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ማቴ. 13:24–27፣ ዘፍ. 1:31፣ ሕዝ. 28:12–19፣ ኢሳ. 14:12–15፣ ማቴ. 4:1–11፣ ዮሐ. 8:44, 45። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ::” ዘፍ 3፡15 + + +ክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እምብርት ነው። ምንም እንኳን በእግዚአብሔር እና በወደቁትና በአምላካቸው ላይ ባመፁት ሰማያዊ ፍጥረታት መካከል ያለው አለማቀፋዊው ተጋድሎ ዋነኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ቢሆንም (ማቴ. 13፡24– 30፣ 37–39፤ ራእይ 12፡7–10)፣ እንዲሁም በብዙ የክርስትና ወጎች ውስጥ ቢገኝም፣ ብዙ ክርስቲያኖች ይህንን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል ወይም ችላ ብለውታል። + +ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር ግን፣ የአለማቀፋዊው ተጋድሎ ጭብጥ የሆነው የእግዚአብሔር መንግሥት በዲያብሎስና በመላእክቱ የሚደርስበት ተቃውሞ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉ ታሪኮችን ባለመረዳት ካልሆነ በስተቀር ችላ ልንለው የምንችለው ጉዳይ አይደለም። ወንጌል ብቻ እንኳን እግዚአብሔርን በሚቃወሙት በዲያቢሎስና በአጋንንት ታሪኮች የተሞላ ነው። + +በዚህ ሳምንት በአንዳንድ ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መሠረት የሚከተሉት ሁለት ጥያቄዎች እንዴት መልስ ሊያገኙ እንደሚችሉ እናያለን፡- + +በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል አለማቀፋዊ ተጋድሎ እንዳለ የሚያስተምረው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው? + +`በቃሉ መሠረት የተጋድሎው ሁኔታ ምን ይመስላል?` + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/02.md b/src/am/ss/2025-01/09/02.md new file mode 100644 index 0000000000..427b859986 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/02.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: ጠላት ይህን አደረገ +date: 23/02/2026 +--- + +`ማቴ. 13:24–27ን ያንብቡ። ምሳሌው በዓለማችን ውስጥ ያለውን ክፋት እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?` + +`ኢየሱስ በእርሻው ላይ መልካም ዘር ብቻ ስለዘራ አንድ የመሬት ባለቤት ታሪክ ይናገራል። ይሁን እንጂ እንክርዳድ በስንዴው መካከል በቀለ። ይህን ሲያዩ አገልጋዮቹ ባለቤቱን ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት” (ማቴ. 13:27)። ይህ ዛሬም ስለ ክፋት ሚስጥር በተደጋጋሚ ከሚጠየቀው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ነው፡- እግዚአብሔር ዓለምን ሙሉ በሙሉ መልካም አድርጎ ከፈጠረ፣ ለምን በውስጡ ክፋት ሊኖር ቻለ? ማቴ. 13፡28–30ን በማቴ. 13፡37–40 ላይ ክርስቶስ ከሰጠው ማብራሪያ አንጻር ያንብቡ። ይህ ደግሞ ስለ አለማቀፋዊው ተጋድሎ ምንነት የሚያስረዳን እንዴት ነው?` + +ጌታው ለአገልጋዮቹ ጥያቄ ሲመልስ፡- “ጠላት ይህን አደረገ” አላቸው (ማቴ. 13፡28)። ኢየሱስ በኋላ ላይ “መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው” በማለት ገልጾታል፤ እርሱም ኢየሱስ ራሱ ነው (ማቴ. 13:37)። ቀጥሎም ሲያብራራ “እርሻው ዓለም ነው” (ማቴ.13:38)፣ እንክርዳዱን “የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው” (ማቴ.13:39) በማለት በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለውን አለማቀፋዊ ተጋድሎ በግልፅ ያሳያል። በዓለም ላይ ክፋት ያለው ለምንድን ነው? ክፋት ጌታውን የሚቃወመው የጠላት (የዲያብሎስ) ውጤት ነው። “ጠላት ይህን አደረገ” (ማቴ. 13፡28)። + +ይህ መልስ ግን “እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን?” የሚለውን ተከታይ ጥያቄ አስነሳ (ማቴ. 13፡28)። በሌላ አገላለጽ ክፋት ለምን ወዲያውኑ አይነቀልም? የሚል ነው። ‘‘እርሱ ግን፡- እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ’’ ብሎ መለሰላቸው (ማቴ. 13፡29, 30፣ ከማር. 4፡29 ጋር ያስተያዩ)። + +በምሳሌው መሠረት እግዚአብሔር በመጨረሻ ክፋትን ያስወግዳል፣ ነገር ግን ያለጊዜው መንቀል በመልካሙ ላይ የማይቀለበስ የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትላል። + +`እንክርዳዱን ከስንዴው አሁን ለመንቀል መፈለግ የሚያመጣቸው አንዳንድ አደጋዎች ምንድን ናቸው? ይህ ሲባል ግን የሚያጋጥመንን ክፋት ችላ ማለት አለብን ማለት ነውን?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/03.md b/src/am/ss/2025-01/09/03.md new file mode 100644 index 0000000000..f3ae640cb1 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/03.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: በምድር ላይ የተጋድሎው መንስኤ +date: 24/02/2026 +--- + +በምሳሌው ላይ ባለቤቱ ጥሩ ዘር ብቻ ከዘራ በእርሻው ላይ ለምን መጥፎ ዘር በቀለ? ከሚለው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሌላው ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ዓለምን ሙሉ በሙሉ መልካም አድርጎ ከፈጠረ፣ ክፋት እንዴት ሊመጣ ቻለ? የሚለው ነው። + +`ዘፍ. 1:31ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ፍጥረትን ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ ስለ ፍጥረት ሁኔታ የተናገራቸው ቃላት የሚገልጹት ምንድን ነው? ይህስ መልስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?` + +`እንደ ዘፍ. 1:31 አባባል እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ ሲጨርስ “እጅግ መልካም” ነበር ይላል። በዘፍ. 1 ላይ እግዚአብሔር ይህችን ዓለም ሲፈጥር ምንም አይነት የክፋት ፍንጭ አልነበረም። ታዲያ ክፋት እንዴት ወደ ሰዎች መጣ? ዘፍ. 3:1-7ን ያንብቡ። ክፋት ወደ ምድር እንዴት እንደ መጣ ይህ ምን ይነግረናል? ይህ በአለማቀፋዊው ተጋድሎ ምንነት ላይ ምን ያስተምረናል? (ራዕ. 12:7–9ን ይመልከቱ)` + +በዚህ ታሪክ ውስጥ እባቡ በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ያነሳቸውን ውሸቶች እናያለን። በራዕ. 12፡7-9 ላይ እባቡ ዲያብሎስ ራሱ (“የቀደመው እባብ”) እንደሆነ ይናገራል። እባቡ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ጥርጣሬን ለመፍጠር ጥያቄን ይጠቀማል፤ በጥያቄውም እግዚአብሔር ያዘዘውን ለመቀልበስ ሞክሯል። ከዚያም እባቡ ለሔዋን “ሞትን አትሞቱም” በማለት እግዚአብሔር የተናገረውን በቀጥታ ይሞግታል (ዘፍ. 3፡4)። + +ከሁለቱ አንዳቸው ማለትም እባቡ ወይም እግዚአብሔር ሔዋንን ዋሽተዋታል፣ እርሷም አሁን እባቡ ወይም አምላክ የተናገራትን ለማመን መምረጥ ነበረባት። + +በዚህና በሌሎች ጥቅሶች ውስጥ፣ የዚህ ተጋድሎ ትኩረት በዋናነት ምንና ማንን ማመን ላይ ነው፤ ይህም ራሱ ከፍቅር ጋር የተያያዘ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ስለ አንድ ሰው ያለህ እምነት፣ በሰውየው ስብዕና እና ሊታመን በመቻሉ የተመረኮዘ ሆኖ፣ ያንን ግለሰብ ለመውደድም ሆነ ለማመን ብሎም የሚነግርህን ለመስማት ተጽእኖ ያሳድርብሃል። + +`ዘፍ. 3:15ን ያንብቡ። የሴቲቱ ዘር ማለትም መሲሑ የእባቡን ጭንቅላት እንደሚቀጠቅጠው እግዚአብሔር ለእባቡ የተናገረው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመጀመሪያው ወንጌል በመባል ይታወቃል። ይህ የተጋድሎውን እውነታ የሚያረጋግጠውና በተጋድሎውም ውስጥ ተስፋ የሚሰጠን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/04.md b/src/am/ss/2025-01/09/04.md new file mode 100644 index 0000000000..66b1ab2fea --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/04.md @@ -0,0 +1,14 @@ +--- +title: በሰማይ የተጋድሎው መንስኤ +date: 25/02/2026 +--- + +`ዘፍ. 1–3 ክፋት አዳምና ሔዋን ከመውደቃቸው በፊት እንደነበረ ያሳያል። በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ “ክፋት” “መልካሙንና ክፉውን በሚያስታውቀው ዛፍ” ስም ተከስቷል (ዘፍ. 2፡9, 17)። ከዚያም የሚዋሸው ራሱ እባቡ ሆኖ ሳለ፣ እግዚአብሔርን ይዋሻል ብሎ ከሰሰ። የእባቡ መኖርና (ራዕ. 12፡9) መዋሸቱ፣ የክፋትን እውነታ ያሳያል። ስለዚህ ከውድቀት በፊት በኤደን ውስጥ እንኳን የክፋት መኖር ተገልጧል። ሕዝ. 28:12–19ን ከዘጸ. 25:19, 20 አንጻር ያንብቡ። የዚህ ፍጡር ውድቀት ምን አይነት ነው?` + +በዚህ ጥቅስ መሠረት የክፋት መንስኤና አለማቀፋዊው ተጋድሎ የጀመረው በሰማይ ነው። ሰይጣን በመባል የሚታወቀው ፍጡር፣ ከመውደቁ በፊት የሚጋርድ ኪሩብ ነበር። በተጨማሪም “ጥበብን የተሞላህ፣ ውበትህም የተፈጸመ፣ መደምደሚያ አንተ ነህ። በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ” ይላል (ሕዝ. 28፡12, 13)። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ለሰብዓዊው የጢሮስ ንጉሥ (ወይም ለሌላ ሰው) ሊባሉ አይችልም። ስለዚህ እዚህ ላይ ስለ ሉሲፈር ውድቀት ፍንጭ እንደተሰጠን እናውቃለን። + +`ኢሳ. 14:12–15ን ንብቡ። ይህ ስለ ታላቁ ተጋድሎ መንስኤ ምን ተጨማሪ ብርሃን ይሰጠናል?` + +በኢሳ. 14 መሠረት ሉሲፈር ራሱን ከፍ ከፍ ለማድረግና እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ወሰነ። ይህ ጥቅስ በሕዝ. 28 ላይ የተመለከትነውን “በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል” (ሕዝ. 28፡17) የሚለውን የሚያጠናክር ሲሆን፣ ውበቱ ያማረ አድርጎ የፈጠረውን አምላክ እንዲያከብር ሊያደርገው ይገባ ነበር። ይልቁንም ኩሩ ሆነ። ይባስ ብሎ በትዕቢት የእግዚአብሔርን ቦታ ለመውሰድና እርሱን ለመስደብ ተነሳ። በሕዝ. 28፡16 ላይ “ንግድ” የሚለው ቃል የዕብራይጡ ትርጉም “ስም ማጥፋት” ማለት ሲሆን፣ ሰይጣን በእግዚአብሔር እና በእኛም ላይ እንዴት እንደሚሠራ የሚያመለክት ነው። + +`የወደቀው ሉሲፈር በመጀመሪያ “ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ በደል እስኪገኝበት ድረስ በመንገዱ ፍጹም ነበረ” (ሕዝ. 28:15) የሚለውን እውነታ እንዴት እንረዳዋለን? ፍጹም የሆነ ፍጡር፣ “ፍጹም” መሆን እውነተኛ የምርጫ ነፃነትን ካላካተተ በስተቀር፣ እንዴት ሊወድቅ ይችላል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/05.md b/src/am/ss/2025-01/09/05.md new file mode 100644 index 0000000000..3594f1e3d0 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/05.md @@ -0,0 +1,24 @@ +--- +title: ብትሰግድልኝ +date: 26/02/2026 +--- + +ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዙፋን ለመንጠቅ ያደረገው ጥረት በማቴ. 4 እና በሉቃ. 4 ላይ በሚገኙት ፈተናዎች ውስጥ ተገልጧል። በኢየሱስ እና በፈታኙ መካከል በነበረው አስገራሚ ፍጥጫ፣ ስለ ተጋድሎው ምንነት ብዙ ነገር ተገልጧል። እዚህ ላይ በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለውን የታላቁን ተጋድሎ እውነታ በግልጽና ስዕላዊ በሆነ መልኩ እናያለን። + +`ማቴ. 4:1-11ን ያንብቡ። እዚህ ላይ በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ያለው ታላቁ ተጋድሎ እንዴት ተገለጠ?` + +መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ የመራበት ዓላማ “ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ” ነው (ማቴ. 4፡1)። ኢየሱስ አስቀድሞ የታቀደውን ይህንን ፍጥጫ ከመጋፈጡ በፊት ለአርባ ቀናት ጾሟል። ስለዚህ ዲያብሎስ በመጣ ጊዜ፣ የኢየሱስን ከፍተኛ ረሃብ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ድንጋዮቹን ወደ እንጀራ እንዲለውጣቸው ፈተነው። + +ኢየሱስ ግን ይህንን ፈተና በቃሉ ተጋፍጦታል፤ የሰይጣንም ተንኮል ከሽፏል። + +ከዚያም ኢየሱስን በዘፈቀደ ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ እርምጃ እንዲወስድ ለማድረግ፣ ዲያብሎስ ኢየሱስን ከቤተ መቅደሱ ጫፍ ላይ ራሱን እንዲጥል ፈተነው። ሰይጣን ቃሉን በማጣመም፣ ኢየሱስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ መላእክት እንደሚጠብቁት ተናገረ ። ነገር ግን ቃሉን በትክክል በማንበቡ፣ ኢየሱስ እንደገና ፈተናውን ተቋቋመ። + +ሦስተኛው ፈተና ዲያቢሎስ ሊፈጽመው የፈለገውን በግልጽ ያሳያል። + +ኢየሱስ እንዲሰግድለት ፈልጓል። ሰይጣን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባውን አምልኮ ለመቀማት ሞክሯል። + +ይህን ለማድረግ ደግሞ ኢየሱስን “የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፣ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” ይለዋል (ማቴ. 4:8, 9 )። በእርግጥም ከማቴዎስ ጋር በሚመሳሰለው በሉቃ. 4፡6 ዲያብሎስ እንዲህ ይላል፡- “ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል፣ ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁ” (ሉቃስ 4፡6)። + +አሁንም ኢየሱስ ፈተናውን በቃሉ ተቋቋመው፤ ሰይጣንም እንደገና ሳይሳካለት ቀረ። በሦስቱም ፈተናዎች የጠላትን ጥቃት ለመከላከል ኢየሱስ ቃሉን ተጠቅሟል። + +`ኤፌ. 6፡12 “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ” በማለት ያስታውሰናል። ምንም እንኳን በፍርሃት መኖር ባይገባንም፣ በዙሪያችን ያለውን ትግል ሁልጊዜ ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/06.md b/src/am/ss/2025-01/09/06.md new file mode 100644 index 0000000000..78ac2cd28b --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/06.md @@ -0,0 +1,16 @@ +--- +title: የአለማቀፋዊው ተጋድሎ ይዘት +date: 27/02/2026 +--- + +በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ስላለው አለማቀፋዊ ተጋድሎ የሚያስተምሩ አንዳንድ ክፍሎችን ተመልክተናል። ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ተጋድሎ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ማን ሊቃወመው ይችላል? አለማቀፋዊ ተጋድሎ የኃይል ጉዳይ ቢሆን ኖሮ፣ ሳይጀመር በፊት ያበቃ ነበር። ስለዚህ የተለየ ዓይነት መሆን አለበት። በእርግጥ ቃሉ ተጋድሎው በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ የተነሳ ክርክር እንደሆነ ይገልፃል - ዲያብሎስ እግዚአብሔርን ፍጹም መልካምና አፍቃሪ አይደለም እያለ በማጥላላት ይከሰዋል። + +እንደዚህ አይነቱን ክስ የሁለቱን ተፎካካሪዎች ባሕርይ በማወዳደር እንጂ በኃይል ወይም በጉልበት መርታት አይቻልም። + +“ለኃጢአት መፍትሄ ለማምጣት እግዚአብሔር ጽድቅንና እውነትን ብቻ ይጠቀማል። ሰይጣን ግን አምላክ የማይጠቀማቸውን ሽንገላንና ማታለልን ይጠቀማል። በመላእክቱ ፊት የእግዚአብሔርን ቃል በማጣመምና የአስተዳደሩን እቅድ በተሳሳተ መንገድ በማቅረብ፣ እግዚአብሔር በሰማይ ነዋሪዎች ላይ ሕጎችንና ድንቦችን ማውጣቱ አግባብ አይደለም አለ። ፍጡራኑ እንዲገዙለትና እንዲታዘዙት የሚፈልገው ራሱን ከፍ ለማድረግ ብቻ ነው አለ። ስለዚህ በሰማይ ነዋሪዎችና በዓለማት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር መንግሥት ፍትሃዊ፣ ሕጉም ፍጹም እንደሆነ መገለጽ ነበረበት። ሰይጣን ራሱ ዓለማት መልካም እንዲሆኑ የሚፈልግ እንደሆነ አስመስሎ ነበር። ሥልጣንን በኃይል ለመንጠቅ የሚፈልገውን ጠላት እውነተኛ ባሕርይና አላማ ሁሉም ሊረዱት ይገባ ነበር። በክፉ ሥራዎቹ ማንነቱን ይገልጽ ዘንድ ጊዜ የግድ ያስፈልገው ነበር።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 498. + +`ዮሐ. 8:44, 45ን ከራዕ. 12:7–9 አንፃር ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ስለ ዲያብሎስ ባሕርይና ስለ ስልቱ ምን ይገልፃሉ?` + +ከመጀመሪያ ጀምሮ የዲያቢሎስ እቅድ እግዚአብሔር በእውነት ፍትሃዊና አፍቃሪ እንዳልሆነ እና ሕጉም ጨቋኝና ጎጂ እንደሆነ ፍጥረታት እንዲያምኑ ለማድረግ መሞከር ነው። ኢየሱስ ዲያብሎስን “ሐሰተኛ የሐሰትም አባት” ብሎ መጥራቱ ምንም አያስደንቅም (ዮሐ. 8፡44)። በአንጻሩ ኢየሱስ የመጣው “ለእውነት ለመመስከር” (ዮሐ. 18፡37) እና በቀጥታ የሰይጣንን ውሸቶችና ስድቦች ለመቃወም፣ ብሎም ዲያብሎስንና ኃይሉን ለማሸነፍና በመጨረሻም ለማጥፋት ነው (1ኛ ዮሐ. 3፡8፣ ዕብ.2፡14)። + +ራዕ. 12:9, 10 ሰይጣንን (1) “የቀደመው እባብ” ፣ (2) በሰማይ ዙፋን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚከስ እና (3) ዓለምን በማሳት የሚገዛ ዘንዶ እንደሆነ ይገልጸዋል። “ዲያብሎስ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል “ተሳዳቢ (ስም አጥፊ)” ማለት ሲሆን የተጋድሎው ምንነት በእግዚአብሔር ባሕርይ በማመን ላይ መሆኑን በድጋሚ ያሳያል። \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/07.md b/src/am/ss/2025-01/09/07.md new file mode 100644 index 0000000000..a511b28d36 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/07.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 28/02/2026 +--- + +ታላቁ ተጋድሎ ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “የክፋት መንስኤ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 492–504 ያንብቡ። + +“ለኃጢአት መከሰት እግዚአብሔር በጭራሽ ተጠያቂ እንዳልሆነ በቃሉ ውስጥ ከሚናገረው በላይ በግልጽ የተነገረ ሌላ ጉዳይ የለም፤ ለአመፅ መነሳት ምክንያት የሚሆን በዘፈቀደ የተነፈገ መለኮታዊ ፀጋ፣ በመለኮታዊውም መንግሥት ውስጥ እንከን አልነበረም። ኃጢአት ለመኖሩ ምንም ምክንያት የማይገኝለት ሰርጎ- ገብ ነው። ሚስጥራዊና ምክንያት አልባ ነው፤ ሰበብ መፈለግ የኃጢአትን መከሰት መደገፍ ነው። . . . ሰይጣን ወዲያውኑ ቢደመሰስ ኖሮ፣ የሰማይና የሌሎች ዓለማት ነዋሪዎች እግዚአብሔርን በፍቅር ሳይሆን በፍርሃት ባገለገሉት ነበር። የአሳቹ ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ባልጠፋ ነበር፤ የዓመፅ መንፈስም ፈጽሞ አይወገድም ነበር። ክፋት እንዲጎመራ መፈቀድ ነበረበት። ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት ጥቅም ሲባል፣ በመለኮታዊው መንግሥት ላይ የሰነዘራቸው ክሶች በሁሉም ፍጥረታት ዘንድ በእውነተኛው ብርሃን እንዲታዩ፣ የእግዚአብሔር ፍርድ፣ ምሕረትና የማይለወጠው ሕጉ ለዘላለም ጥያቄ እንዳይነሳባቸው፣ የሰይጣን መርሆዎች ፍሬ ማፍራት ነበረባቸው። ”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ ፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 492, 493, 499 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. ብዙ ሰዎች እንደ ሉሲፈር ያለ ኃጢአት የሌለበት ፍጡር ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ኃጢአት ሊሠራ ቻለ ብለው ይገረማሉ። ለምንድነው ኃጢአት እጅግ “ምስጢራዊ” እና “ምክንያት አልባ የሆነው”? ይህንን የመጀመሪያ ኃጢአት ያለ ሰበብ ወይም ያለ ምክንያት እንዴት ልንገልጸው እንችላለን? ይኸውም የኃጢአትን መነሻ ማስረዳት ምክንያት እንደማቅረብ የሚሆነው ለምንድነው?` + +`2. እግዚአብሔር ሰይጣንን ወዲያውኑ ያላጠፋው ለምንድን ነው? ክፋት 'እንዲጎመራ የተፈቀደው' ለምንድን ነው? ይህ “ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ሁሉ ለዓለማት የሚበጀው” እንዴት ነው?` + +`3. በእግዚአብሔርና በሰይጣን መካከል ያለው ተጋድሎ የስልጣን ሳይሆን የተለዮ መልክ ያለው መሆኑን መረዳት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የባሕርይ ተጋድሎ መሆኑን መረዳት ከስልጣን ተጋድሎ ይልቅ እንዴት ትርጉም ይሰጠናል?` + +`4. የተጋድሎውን ምንነት መረዳቱ ግርዶሹን በማስወገድ፣ የራስዎ ሕይወት የአለማትን ተጋድሎ በትንሹ እንዴት ሊያሳይ ይችላል? አሁን እንኳን የዚህን ተጋድሎ እውነታ በሕይወትዎ በምን መልክ እያለፉበት ነው? ከማን ወገን እንደሆኑ በሚያሳይ መንገድ እንዴት ምላሽ መስጠት ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/09/info.yml b/src/am/ss/2025-01/09/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..b699b3895e --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/09/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "አለማትን ያካተተው ተጋድሎ" + start_date: "22/02/2026" + end_date: "28/02/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/01.md b/src/am/ss/2025-01/10/01.md new file mode 100644 index 0000000000..333bd44130 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/01.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: የተጋድሎው መርሆዎች +date: 01/03/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ዳን. 10፡1–14፣ ራዕ. 13፡1–8፣ ኢዮ. 1፡1–12፣ ኢዮ. 2፡1–7፣ ዮሐ. 12፡31፣ ዮሐ. 14፡30፣ ማር. 6፡5፣ ማር. 9፡29። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው÷ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና። ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ::” 1ኛ ዮሐንስ 3፡8 + + + +የአለማትን ተጋድሎ ምንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ታሪክ በ1ኛ ነገ. 18፡19-40 ላይ ይገኛል። ኤልያስ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ በነበረ ጊዜ ጌታ “የአሕዛብ አማልክት” የተባሉትን ያጋልጣቸዋል። ሆኖም እነዚህ “አማልክት” የአረማውያን ምናባዊ ፈጠራዎች ከመሆናቸው ባሻገር ከበስተጀርባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በእሥራኤል ዙሪያ የነበሩ አህዛብ እያመለክን ነው ብለው ከሚያስቡት “አማልክት” ጀርባ በእርግጥም ሌላ ነገር ነበር። + +“እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ” ይላል (ዘዳ. 32፡17)። በተጨማሪም ጳውሎስ “አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም” በማለት ይናገራል (1 ቆሮ. 10፡20)። + +በእርግጥም ከአህዛብ ሐሰተኛ “አማልክት” ጀርባ የተሰወሩ አጋንንት ነበሩ። ይህ ማለት እንግዲህ ስለ ጣዖት አምልኮና ስለ ባዕድ አማልክት የሚናገሩት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች “ስለ አለማት ተጋድሎ” የሚናገሩ ናቸው ማለት ነው። + +በዚህ መሠረት የአለማት ተጋድሎ ጭብጥ በተሻለ ሁኔታ ይስተዋላል። እናም ይህ እውነት ስለዚህ ተጋድሎ ምንነት እና የክፋት ምስጢር የበለጠ ለመረዳት ትልቅ አንድምታ አለው። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/02.md b/src/am/ss/2025-01/10/02.md new file mode 100644 index 0000000000..5ce72b8547 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/02.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: እንዲዘገይ የተደረገው መልአክ +date: 02/03/2026 +--- + +ቀደም ሲል እንደተመለከትነው፣ የአሕዛብ ሐሰተኛ “አማልክት” በስውር የሚሰሩ አጋንንት ናቸው። በሌላ ቦታ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ከምድራዊ ገዥዎች ጀርባ ከፍ ባለ ስፍራ ያሉ አጋንንታዊ ገዥዎች እንዳሉ የሚያሳይ ማስረጃ እንመለከታለን። ከእግዚአብሔር የተላኩ መላእክት እንኳን በጠላት ኃይሎች ተቃውሞ ሊደርስባቸው ይችላል። + +ዳን. 10:1–14ን ያንብቡ፤ በቁጥር 12, 13 ላይ ልዩ ትኩረት ያድርጉ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ አለማቀፋዊው ተጋድሎ ምን ያስተምራሉ? እግዚአብሔር የላከው መልአክ ለሃያ አንድ ቀን “ተቃውሞ” ደረሰበት ሲባል ምን ይረዳሉ?` + +እግዚአብሔር የላከው መልአክ ለሦስት ሳምንታት እንዴት ጠላት ‘ሊቋቋመው’ ይችላል? ሁሉን ቻይ በመሆኑ፣ እግዚአብሔር ፍቃዱ ቢሆን ኖሮ ለዳንኤል ወዲያውኑ ምላሽ ለመስጠት ኃይል ነበረው። ይህን ለማድረግ ኃይሉን ቢጠቀም፣ መልአኩ ወዲያውኑ ለዳንኤል እንዲገለጥለት ማድረግ ይችል ነበር። + +ሆኖም አምላክ የላከውን መልአክ “የፋርስ መንግሥት አለቃ” ለሦስት ሳምንታት ያህል “ተቋቋመው”። እዚህ ላይ ምን እየሆነ ነው? + +“ገብርኤል በቂሮስ አእምሮ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ኃይል ለመቋቋም በመፈለግ ለሦስት ሳምንታት ከጨለማ ኃይላት ጋር ታገለ። . . . ሰማይ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ሊያደርግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። ድሉም በመጨረሻ ተገኝቷል፤ ቂሮስና ልጁም ካምባይሲዝ በኖሩበት ዘመን ሁሉ፣ የጠላት ኃይላት በአምላክ ቁጥጥር ሥር ሆነው ነበር።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ ነቢያት እና ነገሥታት፣ ገጽ. 572. + +እንዲህ ያለ ተጋድሎ እንዲካሄድ፣ እግዚአብሔር ኃይሉን ሙሉ በሙሉ አልተጠቀመም ማለት ነው። ዝርዝር ሁኔታው ባይገለጥልንም፣ ጠላት በስውር ወዲያውኑ ያልተወገደ፣ ነገር ግን በሁለቱም ወገኖች በሚታወቁ መንገዶች የተገደበ፣ እውነተኛ ነፃነትና ኃይል ተሰጥቶት ነበር። በአለማቀፋዊው ተጋድሎ የእግዚአብሔር መላእክት እንኳን የሚሠሩባቸው ገደቦች አሉ ማለት ነው፣ ይህም በሚቀጥሉት ትምህርቶች “የተጋድሎው መርሆዎች” ተብሎ ተጠቅሷል። + +በተወሰነ መልኩ፣ እግዚአብሔር የሚሠራው በፍቅር ብቻ እንደሆነ፣ የመንግሥቱም መሠረት ፍቅር እንጂ ማስገደድ እንዳልሆነ ካስተዋልን፣ እነዚህን ገደቦች መረዳት ከባድ ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር የሚሠራው ከፍቅር በሚመነጩ መርሆች ብቻ ነው የሚለው ይህ ሃሳብ ታላቁን ተጋድሎ የበለጠ እንድንረዳ ያደርገናል። + +`በግድ ሳይሆን በፍቅር መርሆች ብቻ የመሥራትን ገደብ እንዴት ነው የተለማመዱት? ስለ ኃይል (ስልጣን) ውስንነትስ ምን ትምህርት ተማሩ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/03.md b/src/am/ss/2025-01/10/03.md new file mode 100644 index 0000000000..e0dfce160e --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/03.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: በራዕይ ላይ ያለው ዘንዶ +date: 03/03/2026 +--- + +በአለማቀፋዊው ተጋድሎ ውስጥ ስላሉ ሰማያዊ ገዥዎች ጠቅለል ያለ ሐሳብ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተገልጿል። በዚያም ዲያብሎስ እግዚአብሔርን በመቃወም “ዓለሙንም ሁሉ በሚያስተው በታላቁ ዘንዶ” ተመስሏል (ራዕ.12:9)። + +`ራዕ. 13:1-8ን ያንብቡ። ይህ ስለ ዘንዶው የሥልጣን ወሰን ምን ያሳየናል?` + +ዘንዶው (ሰይጣን) እግዚአብሔርን (ራዕ. 12፡7-9) እና አገልጋዮቹን (ለምሳሌ ራዕ. 12፡1–6) ብቻ የሚቃወም ሳይሆን ፣ በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በሚያሳድዱ የምድር መንግሥታት ጀርባ ያለው ገዥ እሱ እንደሆነ ተገልጧል። ዘንዶውም ከባሕር ለወጣው አውሬ “. . . ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው” (ራዕ. 13፡2፤ ከራዕ. 13:5፣ ራዕ. 17:13, 14 ጋር ያስተያዩ)። ይህ ከባሕር የወጣው አውሬ “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ ለአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው” (ራዕ. 13፡5)። + +ስለዚህ ሰይጣን ለአውሬው (ለምድራዊው ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ኃይል) ኃይልንና የመግዛት ሥልጣንን ይሰጠዋል። ይህ ኃይል ሥራ ላይ የሚውለው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አምልኮ ለመቀማት ነው። አውሬው የእግዚአብሔርን ስም ይሳደባል፤ ደግሞም ለተወሰነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ይዋጋል፣ ያሸንፋቸውማል። ይህ ዓለም አቀፋዊ ሥልጣን የተሰጠው የዚህ ዓለም ገዥ በሆነው በዘንዶው ነው። + +ሆኖም፣ በሰይጣንና በአጀንዳ አስፈፃሚዎቹ ላይ ግልጽ የሆኑ የጊዜ ገደቦች አሉ። “ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ነዋሪዎች ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና” ይላል (ራእ. 12፡12)። + +ሰይጣን “ዘመኑ አጭር እንደ ሆነ ያውቃል” (ራዕ. 12፡12)፣ በራዕይ ላይ የተገለጹት ኩነቶች የሚፈጸሙት በትንቢታዊ የጊዜ ሰሌዳዎች ነው፣ ይህም እነዚህ የክፉ ኃይሎች የሚሰለጥኑበትን የተወሰኑ ገደቦች ያሳያል (ራዕ. 12፡14፣ ራዕ. 13፡ 5)። + +እውነት ነው - እግዚአብሔር በመጨረሻ ያሸንፋል። “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ” (ራዕ. 21:4)። + +`አሁን ለማየት ቢከብደንም፣ በመጨረሻ በጎነት ለዘላለም በክፋት ላይ ያሸንፋል። ይህን አስደናቂ ተስፋ ፈጽሞ መዘንጋት የሌለብን ለምንድን ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/04.md b/src/am/ss/2025-01/10/04.md new file mode 100644 index 0000000000..3d5d17b591 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/04.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: የኢዮብ ጉዳይ +date: 04/03/2026 +--- + +`በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ አንዳንድ አስደናቂ ግንዛቤዎች ተሰጥተውናል። ኢዮ. 1፡1–12ንና ኢዮ. 2፡1–7ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ተገልጠው የምናያቸው የታላቁ ተጋድሎ መርሆዎች ምንድን ናቸው?` + +ከእነዚህ ጥቅሶች ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል። በመጀመሪያ በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል የሚደረግ ንግግር ብቻ ሳይሆን፣ በሰማይ ምክር ቤት ያለ ይመስላል፤ ሌሎች የሰማይ ፍጥረታትም ተሳትፈውበታል። + +ሁለተኛ እግዚአብሔር ሰይጣንን ኢዮብን ተመለከትኸውን? ብሎ መጠየቁ አንዳንድ አለመግባባቶች እንዳሉ የሚጠቁም ነው። ኢዮብን ለምን ይመለከተዋል? ጥያቄው ትርጉም የሚኖረው ከፍ ባለና በመካሄድ ላይ ባለ ሙግት አውድ ውስጥ ነው። + +ሦስተኛ እግዚአብሔር ኢዮብን ነቀፋ የሌለበት፣ ጻድቅና አምላክን የሚፈራ ብሎ ሲገልፀው፣ ሰይጣን ግን ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ የሚመስለው አምላክ ስለሚጠብቀው ብቻ እንደሆነ ይሞግታል። ይህም የኢዮብን እና የእግዚአብሔርን ባሕርይ ማንቋሸሽ ነው (ከራዕ. 12፡10 እና ከዘካ. 3 ጋር ያስተያዩ)። + +አራተኛ ሰይጣን አምላክ ኢዮብን መጠበቁ (ማጠሩ) ፍትሐዊ እንዳልሆነ ይከሳል፣ ክሱንም ለማረጋገጥ እንደማያስችለው ተናግሯል። ይህም በሰይጣን ላይ አንዳንድ ገደቦች (የተጋድሎ መርሆዎች) መኖራቸውንና ሰይጣንም ኢዮብን ለመጉዳት መሞከሩን ያሳያል። + +እግዚአብሔር ለሰይጣን ክስ በሰማያዊው ምክር ቤት ፊት ምላሽ የሰጠው፣ ሰይጣን በተቀመጠለት ገደብ ብቻ ኢዮብን እንዲፈትነው በመፍቀድ ነው። በመጀመሪያ ለሰይጣን ኢዮብ “ባለው ሁሉ” ላይ ስልጣን ሰጠው፣ ነገር ግን አካላዊ ጉዳትን ይከለክል ነበር (ኢዮብ 1፡12)። በኋላ ሰይጣን ኢዮብ የሚያስበው ለራሱ ብቻ እንደሆነ ሲሞግት፣ እግዚአብሔር ለሰይጣን ኢዮብን እንዲያሠቃየው ፈቀደለት - ከሕይወቱ በስተቀር (ኢዮብ 2፡3-6)። + +`ሰይጣን በኢዮብ ቤተሰብ ላይ ብዙ መቅሰፍቶችን አመጣ፤ ሆኖም በእያንዳንዱ ሁኔታ ኢዮብ ያምላክን ስም መባረኩን በመቀጠሉ (ኢዮ. 1:20–22፣ ኢዮ. 2:9, 10)፣ የሰይጣንን ክሶች አመከነ።` + +እዚህ ላይ ብዙ ነገሮችን እንማራለን፣ ለምሳሌ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ የተጋድሎ መርሆዎች አሉ። በሰማያዊው ዙፋን በእግዚአብሔር ላይ የተነሱት ክሶች እልባት የሚያገኙበት መስፈርቶች አሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የመንግስቱ መሠረት በሆነው ፍቅር ውስጥ ያሉትን የተቀደሱ መርሆች፣ እንዲሁም አለማትንና በውስጣቸው ያሉትን የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ፍጥረታት የሚገዛባቸውን ደንቦች አይጥስም። + +`በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ሰማያዊ ትዕይንቶች፣ ስለ ታላቁ ተጋድሎና በዚህ ምድር ላይም እንዴት እንደሚከናወን አስደናቂ ማስተዋል ይሰጡናል።` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/05.md b/src/am/ss/2025-01/10/05.md new file mode 100644 index 0000000000..c1892beb2b --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/05.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: የዚህ ዓለም ጊዜያዊ ገዥ +date: 05/03/2026 +--- + +ቀደም ብለን በታላቁ ተጋድሎ ሰይጣንና ግብረ-አበሮቹ በተጋድሎው መርሆዎች ተወስነው፣ በዚህ ዓለም ውስጥ ለጊዜው ጉልህ የሆነ ስልጣን እንደተሰጣቸው አይተናል። + +እነዚህ የተጋድሎ መርሆዎች የዲያብሎስንና የአጋሮቹን ድርጊት ብቻ ሳይሆን፣ በጠላት ግዛት ውስጥ ለጊዜው የሚፈጠረውን ክፋት እንዳያስወግድ የእግዚአብሔርንም እርምጃ ይገድባሉ። ጌታ የገባውን ቃል በፍፁም ስለማያጥፍ፣ በተስማማባቸው መሠረት የተወሰነና ጊዜያዊ ስልጣን ለዲያብሎስ በመስጠቱ፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ኃይሉ ታላቅ ቢሆንም ወደፊት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ግን የተገደቡ ይሆናሉ። + +`ዮሐ. 12:31ን፣ ዮሐ. 14:30ን፣ ዮሐ. 16:11ን፣ 2 ቆር. 4:4ን፣ ሉቃ. 4:⁠6ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በዚህ ዓለም ላይ ጠላት ስላላው ስልጣን ምን ያስተምራሉ?` + +አዲስ ኪዳን የብርሃንና የጨለማ መንግሥታትን ውጊያ ይገልጻል። + +ጨለማውም ከሰይጣንና ከአመፃው የተነሳ የመጣ ነው። የክርስቶስ ተልዕኮ የሰይጣንን መንግሥት ማሸነፍ ነበር። “ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ” (1ኛ ዮሐንስ 3፡8)። + +ቢሆንም እግዚአብሔር ለመንግሥቱ መርሆዎች ታማኝ ስለሆነ፣ ሊያደርግ የሚችለው ነገር “በደንቦቹ” መሠረት የተገደበ (የተወሰነ) ነው። እነዚህ ገደቦች ቢያንስ (1) ለፍጡራኑ የምርጫ ነፃነት መስጠትን እና (2) አሁን የማናስተውለውን የተጋድሎውን ኪዳናዊ ደንቦች ማክበርን ያካትታሉ። እነዚህ ክልከላዎችና ገደቦች፣ እግዚአብሔር ክፋትን ከዓለም ላይ ለመቀነስ ወይም ወዲያውኑ ለማስወገድ እንዳያስችለው ስለሚያደርጉ፣ በመለኮት አሰራር ላይ ጉልህ አንድምታ አላቸው። + +ስለዚህ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን መኖር ወይም በጎነቱን እንዲጠራጠሩ የሚያደርግ ቀጣይ የሆነ ክፋትና መከራ እናያለን። ነገር ግን የታላቁን ተጋድሎ ምንነትና እግዚአብሔር ክፋትን የሚያስታምምበትን ምክንያቶች ከተረዳን፣ ነገሮች ለምን አሁን ባሉበት ሁኔታ እንዳሉ በተሻለ ሁኔታ እናስተውላለን - ቢያንስ እግዚአብሔር ክፋትን መጨረሻ ላይ ድል እስኪያደርግ ድረስ። + +`ኢየሱስ ሰይጣንን የዚህ ዓለም “ገዥ” ብሎ መጥራቱ፣ አሁን በዓለም ላይ ያለውን ክፋት እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ጊዜያዊ ስልጣን ብቻ መሆኑን ማወቁ ምንኛ የሚያጽናና ነው!` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/06.md b/src/am/ss/2025-01/10/06.md new file mode 100644 index 0000000000..fef5b3369c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/06.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ገደቦች እና ደንቦች +date: 06/03/2026 +--- + +ታላቁ ተጋድሎ በዋነኛነት በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ የተነሳ ውዝግብ ነው። ይህም በእግዚአብሔር መልካምነት፣ ፍትሕና አገዛዝ ላይ በዲያብሎስ የተጠነሰሰ የስም ማጥፋት ክስ ነው። + +እንዲህ ዓይነቱ ግጭት በኃይል ሊፈታ አይችልም፣ ይልቁንም ባሕርይው መገለፅ ያስፈልገዋል። ስልጣን ባለው ሰው ላይ ከባድ ውንጀላዎች ከተነሱ፣ ክሱን ለማሸነፍ የተሻለውና ምናልባትም ብቸኛው መንገድ ነፃ፣ ፍትሐዊና ግልጽ ምርመራ ማድረግ ነው። ክሱ መላውን የፍቅር መንግሥት የሚያሰጋ ከሆነ፣ ዝም ብሎ ችላ ማለት አይቻልም። + +ይህ ሁሉ ክፋትን በተመለከተ የተነሳውን ታላቁን ተጋድሎ ለመረዳት እንዴት ይረዳናል? እግዚአብሔር ቃል ከገባ፣ ቃሉን ያጥፍ ይሆን? በጭራሽ። + +እግዚአብሔር በተጋድሎው ደንቦች ከተስማማ፣ የወደፊት ድርጊቱ በስምምነቱ መሠረት የተገደበ ይሆናል። ስለዚህ አንዳንድ ክፋቶች በጊዜያዊው የጨለማው መንግሥት ግዛት ውስጥ ሊፈፀሙ ይችላሉ። + +`ማር. 6:5ንና ማር. 9:29ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች መለኮታዊው ድርጊት ከእምነትና ከጸሎት ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ምን ያሳያሉ?` + +በሁለቱም ታሪኮች፣ ከእምነትና ከጸሎት ጋር ግንኙነት ያላቸው አንዳንድ ገደቦች ወይም የተጋድሎ ደንቦች እንዳሉ የሚያመለክቱ ይመስላሉ። በሌሎች ጥቅሶችም ጸሎት በዚህ ዓለም ላይ ለውጥ እንደሚያመጣና ለመለኮታዊው አሰራር በሮችን እንደሚከፍት ብዙ ማስረጃዎችን እናያለን። ይሁን እንጂ እምነትና ጸሎት ብቻ ናቸው ወሳኞቹ ብለን በማሰብ መሳሳት የለብንም። እኛ የማናውቃቸው ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። + +ይህ ቀደም ሲል ካየናቸው ጋር ይስማማል። + +እግዚአብሔር ቃል ከገባ ወይም በተጋድሎው ደንቦች ከተስማማ፣ የወደፊት ድርጊቱ በስምምነቱ መሠረት የተገደበ ይሆናል። ስለዚህ አንዳንድ ክፋቶች በጊዜያዊው የጨለማው መንግሥት ግዛት ውስጥ ሊፈፀሙ ይችላሉ። + +`ሮሜ 8:18ንና ራዕ. 21:3, 4ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች ቢኖሩም፣ አምላክ ከሁሉ የሚሻለውን እንደሚያውቅና እንደሚፈልግ፣ እንዲሁም ለክፋት ፍፃሜ አድርጎ ዘላለማዊ ደስታን እንደሚያመጣ እንድንታመንበት የሚያደርጉን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/07.md b/src/am/ss/2025-01/10/07.md new file mode 100644 index 0000000000..66badacadf --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/07.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 07/03/2026 +--- + +የቤተክርስቲያን ምክሮች ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ ”የሰይጣን ኃይል” የተሰኘውን ርዕስ ጥራዝ 1 ከገጽ 341–347 ያንብቡ። + +"የወደቀው ሰው የሰይጣን ህጋዊ ምርኮኛ ነው። የክርስቶስ ተልዕኮ እርሱን ከክፉ ባላጋራው ኃይል ማዳን ነው። ሰው በተፈጥሮው የሰይጣንን ምክሮች የመከተል ዝንባሌ አለው። እናም ኃያል የሆነው ድል አድራጊው ክርስቶስ በእርሱ ውስጥ ካላደረ፣ ምኞቱን ካልገራውና ኃይልን ካልሰጠው በስተቀር፣ ያንን አስፈሪ ጠላት በተሳካ ሁኔታ መቋቋም አይችልም። የሰይጣንን ኃይል ገደብ የሚያበጅለት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰይጣን ምድርን ሁሉ በመዞር ይመላለስባታል። ነፍሳትን ለማጥፋት እድሉን እንዳያጣ በመፍራት፣ ለአፍታ እንኳን አያንቀላፋም። የእግዚአብሔር ሕዝብ ከወጥመድ ያመልጡ ዘንድ ይህንን መገንዘብ አለባቸው። ሰይጣን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በሚያደርገው የመጨረሻ ዘመቻ፣ እርሱ መሆኑን እንዳይረዱ በማድረግ ማታለያዎቹን እያዘጋጀ ነው። 2ኛ ቆሮ. 11:14፡- ‘ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና’ ይላል። አንዳንድ የተታለሉ ነፍሳት ሰይጣን የለም ሲሉ፣ ይማርካቸውና በእነርሱ አማካኝነት በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል። + +ኃይላቸው በክርስቶስ ሲሆን፣ በእርሱ ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ኃይል ከእግዚአብሔር ሰዎች ይልቅ ሰይጣን ያውቃል። ኃያል የሆነውን ድል አድራጊ በትሕትና እንዲረዳቸው ሲማፀኑት፣ እውነትን የሚያምነው እጅግ ደካማ ሰው እንኳን፣ በክርስቶስ በመታመን ሰይጣንንና ሠራዊቱን በሙሉ በተሳካ ሁኔታ መቃወም ይችላል። እጅግ ተንኮለኛ ስለሆነ ፈተናዎቹን በግልጽ ይዞ አይመጣም፤ ያማ ቢሆን የደነዘዘው የክርስቲያን ጉልበት ይነቃና በጠንካራውና በኃይለኛው አዳኝ ይተማመናል። እርሱ ግን ሳይታሰብ ይመጣል፣ የአምልኮ መልክ ባላቸው በማይታዘዙ ልጆች አማካኝነት በድብቅ ይሠራል።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የቤተክርስቲያን ምክሮች፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 341 + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + +`1. “የሰይጣን ህጋዊ ምርኮኛ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ዲያብሎስ በሰዎች ላይ የፈለገውን ማድረግ ይችላል ማለት ነው? አይችልም ካልን፣ ለምን አይችልም? ይህ በታላቁ ተጋድሎ "የተጋድሎው ደንቦች" ብለን ከምንጠራው ጋር እንዴት ይዛመዳል?` + +`2. አምላክ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ፣ ለጊዜውም ቢሆን፣ ለሰይጣን አንዳች ሥልጣን የሚሰጠው ለምንድን ነው? ይህ አምላክ ለሰይጣን ክሶች መልስ ለመስጠት ስለሚፈልግበት መንገድ ምን ይነግረናል?` + +`3. ክርስቲያኖችን ጨምሮ፣ ሰይጣን የሚባል ፍጡር መኖሩን ለሚክዱ ምን ምላሽ ይሰጧቸዋል? ምንም እንኳን ሰይጣን መኖሩን በአካል ማረጋገጥ ባንችልም፣ በጣም የተታለለን ሰው ሊረዳው የሚችል ምን ማስረጃ ሊያቀርቡ ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/10/info.yml b/src/am/ss/2025-01/10/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..c5df6b2f59 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/10/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "የተጋድሎው መርሆዎች" + start_date: "01/03/2026" + end_date: "07/03/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/01.md b/src/am/ss/2025-01/11/01.md new file mode 100644 index 0000000000..f5942f93df --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/01.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር? +date: 08/03/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ዮሐ. 18፡37፣ ሮሜ 3፡ 23–26፣ ሮሜ 5፡8፣ ኢሳ. 5፡1–4፣ ማቴ. 21፡33–39፣ ኢሳ. 53፡4፣ ሮሜ 3፡1–4። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “ጲላጦስም፦ እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ፡- እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው::” ዮሐ. 18፡37 + + +ከጥቂት ከዓመታት በፊት፣ ጥልቅ ትምህርት ያለው የልጆች ታሪክ በጋይድ (Guide) መጽሔት ታትሞ ነበር። ታሪኩ የሚያተኩረው በመካከለኛው ዘመን ከአንድ ቤተሰብ ጋር በማደጎ ልጅነት ይኖር በነበረ ዴኒስ በተባለ ልጅ ላይ ነው። ዴኒስ ወላጆቹ በታመሙ ጊዜ የንጉሱ ወታደሮች ስለወሰዱትና ከዚያ በኋላ እንደገና ወላጆቹን ስላላያቸው፣ የአገሩን ንጉሥ አምርሮ ይጠላው ነበር። ንጉሡ በሕይወት ያሉትን ከአስከፊው የተስቦ ወረርሽኝ ለማትረፍ ሲል እንደለያቸው የተረዳው በኋላ ነበር። ስለ ንጉሡ የተረዳው እውነት ዴኒስን ከሞላ ጎደል እድሜውን ሁሉ ይዞት ከነበረው ጥላቻ ነፃ አውጥቶታል። ንጉሡ ሁልጊዜ በማንኛውም ሁኔታ ነገሮችን ያደርግ የነበረው ለሕዝቡ ካለው ፍቅር የተነሣ ነበር። + +ዛሬም ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ዴኒስ ንጉሡን ባየበት መንገድ ይመለከቱታል። ያዩት ወይም ያጋጠማቸው ክፋት እግዚአብሔርን እንዲጠሉት ወይም የለም እንዲሉ ያደርጋቸዋል። በስቃይ ጊዜ እግዚአብሔር የት ነው? እግዚአብሔር መልካም ከሆነ፣ ክፋት ለምን በዛ? ምንም እንኳን አሁንም ብዙ ጥያቄዎች ቢኖሩንም፣ ታላቁ ተጋድሎ ይህንን ወሳኝ ጉዳይ እንድናስተውል ይረዳናል። ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ የምናደርገው ሙከራ ሁሉ ባያረካንም፣ አሁንም ያልተመለሱ ጥያቄዎች ቢኖሩንም፣ ወደ ተሰቀለው ኢየሱስ ልንመለከትና እግዚአብሔር ሊታመን እንደሚችል ልንረዳ እንችላለን። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/02.md b/src/am/ss/2025-01/11/02.md new file mode 100644 index 0000000000..d463264dd6 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/02.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ድል አድራጊው ክርስቶስ +date: 09/03/2026 +--- + +ምንም እንኳን ክርስቶስ ራሱ “የዚህ ዓለም ገዥ” ብሎ የሚጠራው በሥራ ላይ ያለ ጠላት ቢኖርም፣ እውነተኛው የዓለማት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። + +በእኛ ምትክ ድል ያደረገው ኢየሱስ ነው፤ በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን፣ በእርሱ ድል ማድረግ እንችላለን። በእርግጥም የክርስቶስ ሥራ ሁልጊዜ የጠላትን ሴራ ያከሽፋል። ቃሉ ዲያብሎስን እንዲህ ይገልፀዋል፡- +1. ከመጀመሪያው ጀምሮ ዓለምን ሁሉ የሚያስት (ራዕ. 12:9፣ ማቴ. 4:3፣ ዮሐ. 8:44፣ 2 ቆሮ. 11:3፣ 1 ዮሐ. 3:8). +2. በሰማይ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን የሚሳደብና የሚከስ (ራዕ. 12፡ 10፣ ራዕ. 13፡6፣ ኢዮ. 1–2፣ ዘካ. 3፡1, 2፣ ይሁዳ 9)። +3. ያላግባብ (በግድ) የዚህ ዓለም ገዥ የሆነ (ዮሐ. 12፡31፣ ዮሐ. 14፡30፣ ዮሐ. 16፡11፣ ሐዋ. 26፡18፣ 2 ቆሮ. 4፡4፣ ኤፌ. 2፡2፣ 1ዮሐ. 5፡19)። + +`ዮሐ. 18:37ን ያንብቡ። ይህ የጠላትን ማታለያዎች ለመቋቋም ክርስቶስ ስላደረገው ሥራ ምን ይነግረናል? ኢየሱስ ንጉሥ ነው ማለት ምን ማለት ነው?` + +ምንም እንኳን ቃሉ ሰይጣንን የዚህ ዓለም አታላይ፣ ተሳዳቢ (ስም አጥፊ)፣ ከሳሽና ገዥ እንደሆነ ቢያስተምርም፣ ኢየሱስ ደግሞ በሰይጣን ላይ በሁሉም መንገድ ድል አድራጊ እንደሆነም ያስተምራል። +1. ኢየሱስ “ወደ ዓለም የመጣው ለእውነት ሊመሰክር” ነው (ዮሐንስ 18፡37) +2. ኢየሱስ በመስቀሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ጽድቅና ፍቅር አሳይቷል (ሮሜ 3:25, 26፣ ሮሜ 5:8)፤ በዚህም የዲያብሎስን የሀሰት ክሶች ውድቅ አድርጓል (ራዕ. 12:10, 11) +3. በመጨረሻም ኢየሱስ “ዘመኑ ጥቂት እንደ ሆነ የሚያውቀውን” የዲያብሎስን መንግሥት ያጠፋል (ራዕ. 12:12፤ ከሮሜ 16:20 ጋር ያስተያዩ)፤ ክርስቶስም “ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል” (ራዕ. 11:15)። በመጨረሻ ሰይጣን ምንም ቢያደርግ፣ እሱ የተሸነፈ ጠላት ነው፤ ለእኛ ቁልፉ ነገር የክርስቶስን ድል በየዕለቱ በየደቂቃው፣ እንዲሁም መስቀሉ የሰጠንን ተስፋዎች የእኛ አድርገን መቀበል ነው። + +`በታላቁ ተጋድሎ የትኛው ወገን እንደሚያሸንፍ እናውቃለን። የዕለት ተዕለት ምርጫዎቻችን በመጨረሻ በማን ወገን እንደምንሆን ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ? አሁን እንኳን በአሸናፊው ወገን መሆናችንን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/03.md b/src/am/ss/2025-01/11/03.md new file mode 100644 index 0000000000..4ae89d5c3b --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/03.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ጻድቅና የሚያጸድቅ +date: 10/03/2026 +--- + +ሁልጊዜ የክርስቶስ ሥራ የዲያብሎስን ሥራ ይሽራል። ኢየሱስ “የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍርስ” (1ኛ ዮሐ. 3፡9) እና “በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስ ለመሻር” ነው (ዕብ. 2፡14)። ሆኖም የጠላት አገዛዝ አጠቃላይ ሽንፈት በሁለት ደረጃዎች ይከናወናል። በመጀመሪያ፣ በመስቀሉ ክርስቶስ የሰይጣንን የስም ማጥፋት ክሶች ሐሰት መሆናቸውን አረጋግጧል። + +`በኋላም ሰይጣንና መንግሥቱ ይደመሰሳል። ሮሜ 3፡23–26ንና ሮሜ 5፡8ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች ክርስቶስ የዲያብሎስን ክሶች ስለሚረታበት መንገድ ምን ይገልጻሉ?` + +አስቀድመን እንዳየነው ጠላት እግዚአብሔርን ፍፁም ጻድቅና አፍቃሪ አይደለም ይላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር ግሩም በሆነ ሁኔታ በክርስቶስ ተገልጧል፣ ይህንም ያደረገው በመስቀሉ ነው። + +ኢየሱስ ከሞተ በኋላ፣ “ሰይጣን የማታለያ ካባው እንደ ተቀደደ አየ። + +`የእርሱ አስተዳደር ባልወደቁት መላእክትና ዓለማት ፊት ተገለጠ። ራሱን ነፍሰ- ገዳይ እንደሆነ አጋለጠ። የእግዚአብሔርን ልጅ ደም በማፍሰሱ፣ በሰማይ ያሉ ፍጥረታትን አዘኔታ አጣ።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 761. ራዕ. 12፡10–12ን ከዘፍ. 3፡15 አንጻር ያንብቡ። ይህ ክፍል ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተጎናፀፈው ድል ለአለማት ሁሉ ያለውን ጠቀሜታ እንዴት ይገልፃል?` + +የመቤዠታችን ታሪክ እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚሠራው በስተመጨረሻ ለሁሉም በጎ እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ እንድንታመንበት ብዙ ማስረጃዎችን ይሰጠናል። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ሊሰራ በሚችልባቸው መንገዶች ሁሉ ሁልጊዜ መልካምና ተመራጭ የሆነውን ያደርጋል (ዘዳ. 32:4፣ 1 ሳሙ. 3:18፣ መዝ. 145:17፣ ዳን. 4:37፣ ዕን. 1፡13፣ ራዕ. 15፡3፣ ዘፍ. 18፡25)። + +`በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር በተግባር መገለፁ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በደህንነት እቅድ ውስጥ ስለ መስቀሉና ስለ ሁሉም የእግዚአብሔር ሥራዎች ስታሰላስሉ፣ አሰራሩ በፈተናና በስቃይ ውስጥ እንኳን በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ እንድትታመኑ ድፍረት የሚሰጣችሁ እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/04.md b/src/am/ss/2025-01/11/04.md new file mode 100644 index 0000000000..e952b103a5 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/04.md @@ -0,0 +1,14 @@ +--- +title: የወዳጄ ቅኔ +date: 11/03/2026 +--- + +በታላቁ ተጋድሎ ውስጥም ቢሆን፣ በአስደናቂ መንገድ እግዚአብሔር ፍቅሩንና ጽድቁን አሳይቷል። ሆኖም አንዳንዶች አምላክ ክፋትን ለመከላከል እንዲሁም ለማስወገድ ካደረገው የበለጠ ማድረግ አልነበረበትምን? ብለው ይጠይቃሉ። በታላቁ ተጋድሎ ማዕቀፍ፣ እግዚአብሔር በእርሱና በሰዎች መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያድግ አስፈላጊ የሆነውን የምርጫ ነፃነት በማክበር የሚበጀውን እንዳደረገ አይተናል። በተጨማሪም በባሕርይው ዙሪያ የተነሳው አለም አቀፋዊ ሙግትሊፈታ የሚችለው ፍቅሩን በተግባር በማሳየት ብቻ ስለነበር፣ የሞራል ገደቦችን ወይም የተጋድሎ መርሆዎችን በማክበር ሥራውን ፈፅሟል። + +`ኢሳ. 5:1-4ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የሚናገረው ማነው? ኢሳያስ ስለ ማን ነው የሚናገረው? የወይኑ ቦታ እና የወይኑ ቦታ ባለቤት ማንን ያመለክታሉ? የወይኑ ቦታ ባለቤት ለወይኑ ቦታ ያደረጋቸው ነገሮች አስፈላጊነት ምንድን ነው? ውጤቱስ ምንድን ነው?` + +በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢሳይያስ ለወይን ቦታው ቅኔ ይቀኛል። የወይኑ ቦታ ባለቤት እግዚአብሔር ራሱ ነው፣ የወይኑም ቦታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይወክላል (ለምሳሌ ኢሳ. 1፡8ን፣ ኤር. 2፡21ን ይመልከቱ)። ነገር ግን እዚህ ላይ ያለው አንድምታ፣ በዚህ ዓለም የሚደረገውን ሰፊውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሊያሳይ ይችላል። በእነዚህ ጥቅሶች መሠረት፣ የወይኑ ቦታ ባለቤት የወይኑን ቦታ ፍሬአማ ለማድረግ የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል። የወይኑ ቦታ ጥሩ የወይን ፍሬ ማፍራት ነበረበት፤ ይሁን እንጂ የማይረባ “ሆምጣጣ ፍሬ” አፈራ። በእርግጥም እዚህ ላይ ያለው የዕብራይስጥ ቃል የሸተተ ፍሬ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። + +የእግዚአብሔር የወይን ቦታ የማይረባ የወይን ፍሬ አፈራ። + +`ኢሳ. 5፡3 ላይ እግዚአብሔር ራሱ ሰዎችን በእርሱና በወይኑ ቦታው መካከል “እንዲፈርዱ” ይጋብዛል። በኢሳ. 5፡4 ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ጥያቄ ይጠይቃል፡- “ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስጠብቅ፣ ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?” ይላል። ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? እንዲያውም እርሱ ያደረገውን ነገር ሌሎች እንዲፈርዱ መጠየቁ እንዴት የሚደንቅ ነው! እግዚአብሔር ራሱን ለኃጢአታችን ሁሉ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበትን መስቀል ሲመለከቱ፣ “ለወይኔ ያላደረግሁለት፣ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው?” የሚለው ቃል እንዴት ያለ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/05.md b/src/am/ss/2025-01/11/05.md new file mode 100644 index 0000000000..a5a3a0e803 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/05.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: የክርስቶስ የወይኑ ቦታ ምሳሌ +date: 12/03/2026 +--- + +በማቴ. 21 ባለው የወይኑ ቦታ ባለቤት ምሳሌ፣ ኢየሱስ ኢሳይያስ 5 ካቆመበት ይቀጥልና የወይኑ ቦታ ባለቤት የወይን ቦታውን በተመለከተ ባለው ባሕርይና ድርጊት ላይ ተጨማሪ ብርሃን ይሰጠናል። + +`የኢሳ. 5:4ን ጥያቄ በአእምሮዎ ይዘው ማቴ. 21:33–39ን ያንብቡ። ካደረገው በላይ ምን ማድረግ ይችላል?` + +የክርስቶስ ምሳሌ የመጀመሪያው ክፍል ስለ ወይን ቦታው ባለቤትና ስለ ወይን ቦታው ከኢሳ. 5 ቅኔ በቀጥታ ይጠቅሳል። ከዚያም ኢየሱስ የወይኑ ቦታ ባለቤት የወይኑን ቦታ “ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ”በማለት ያክላል (ማቴ. 21፡33)። ሆኖም የወይኑ ቦታ ባለቤት ሁለት ጊዜ አገልጋዮቹን (ነቢያትን) ምርቱን እንዲቀበሉ ቢልካቸውም፣ የወይኑ ቦታ ተከራዮች አገልጋዮቹን ደበደቧቸው፣ ገደሏቸውም (ማቴ. 21፡34–36)። በመጨረሻም “ልጄንስ ያከብሩታል” ብሎ ልጁን (ኢየሱስን) ላከው (ማቴ. 21፡37)። ነገር ግን ልጁን ደግሞ “ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ ተባባሉ። ይዘውም ከወይኑ አትክልት አወጡና ገደሉት (ማቴ. 21፡38, 39)። + +ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? አብ እጅግ ስለ ወደደን የሚወደውን ልጁን ሰጠን (ዮሐ. 3፡16)። ታላቁ ተጋድሎ እዚህ የተጠቆመው ዓይነት ከሆነ፣ መለኮታዊ ኃይልን በመጠቀም በእንጭጩ መፍታት አይቻልም፤ ይልቁንስ በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ባሕርይ በአደባባይ በተግባር ማሳየትን ይጠይቃል። + +ይህም ደግሞ በክርስቶስ ሥራ በገሃድ ታይቷል (ሮሜ 3፡25, 26፣ ሮሜ. 5፡8)። ፍርዱንና ፍፁም ፍቅሩን በምንም ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ሳያስገባ ያጸድቀን ዘንድ፣ እግዚአብሔር (በክርስቶስ) ለእኛ ሲል ለሞት ራሱን አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ምን ልንጠይቀው እንችላለን? + +እውነተኛ ፍቅር የሚበለፅግበትን ሁኔታ ሳያዳፍን፣ መስቀሉ እግዚአብሔር ክፋትን ለመቀልበስና ለማስወገድ የሚቻለውን ሁሉ ማድረጉን ያሳያል። + +እግዚአብሔር ሌላ የሚበጅ መንገድ ቢኖር ኖሮ፣ ያን አይመርጠውም ነበርን? በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ ሰዎች እጅግ ቢሰቃዩም፣ እግዚአብሔር ራሱ ከሁሉም በላይ ይሠቃያል። መስቀሉን ስንመለከት፣ በእርግጥ ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ ያመጣውን ስቃይና ህመም ማየት እንችላለን። ሆኖም በፍቅር ውስጥ ያለው ነፃነት በጣም የከበረ ስለሆነ፣ ክርስቶስ ለእኛ ሲል ይህንን ሁሉ ለመሸከም ፈቃደኛ ሆነ። + +`ኢሳ. 53:4ን ያንብቡ። ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሸከመው የማንን "ደዌ" እና "ህመም" ነው? ይህ እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር ሁሉና የኛ መዳን ስላስከፈለው ዋጋ ምን ሊነግረን ይገባል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/06.md b/src/am/ss/2025-01/11/06.md new file mode 100644 index 0000000000..ab5d0cea95 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/06.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: የእግዚአብሔር ስም ከክስ ነፃ መሆን +date: 13/03/2026 +--- + +በመጨረሻ የእግዚአብሔር ስም ከማንኛውም ክስ ነፃ ይሆናል። በደህንት እቅድ ውስጥ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በሚያደርጉት ሥራ፣ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ጽድቅና ፍቅር ያለምንም ጥርጣሬ ይገለጣል (ሮሜ. 3፡25, 26፣ ሮሜ. 5፡8)። + +`ሮሜ 3:1–4ን ከኢሳ. 5:3, 4 አንጻር ያንብቡ። ይህ እግዚአብሔር በአለማቀፋዊው ተጋድሎ መጨረሻ ነፃ ስለመሆኑ ምን ያስተምራል? +` + +በሮሜ 3 እና በኢሳ. 5 ላይ ምንም እንኳን መብት ባይኖረንም ወይም የማይገባን ቢሆንም፣ እግዚአብሔር (በተወሰነ መልኩ) ፍጡራኑን በባሕርይው እንዲፈርዱ ሲጋብዛቸው እናያለን። በመጨረሻ ሁሉም “መጻሕፍት” ሲከፈቱ፣ እግዚአብሔር ፍጹም በጎና ጻድቅ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን እንመለከታለን። እግዚአብሔር በሚያስተውሉ ፍጥረታት ሁሉ ፊት ራሱን ከክስ (ከጥፋተኝነት) ነፃ ያደርጋል። + +`ራዕ. 15:3ንና ራዕ. 19:1–6ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በመጨረሻ የእግዚአብሔር ስም ከማንኛውም ክስ ነፃ እንደሚሆን ምን ያስተምሩናል? +` +በቃሉ ውስጥ እግዚአብሔር ለስሙ እንደሚገደው ያሳያል። ለምን? ባሕርይውን ከምትጸየፉት ወይም ከማታምኑት ሰው ጋር ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ሊኖራችሁ አይችልም። አንድ ሰው ለትዳር ጓደኛዎ ወይም ለእጮኛዎ ስለ ባሕርይዎ ዘግናኝ ውሸቶችን ቢነገግሯቸው፣ ይህን ለመቃወም የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ምክንያቱም እንደዚህ ያሉ ወሬዎች ከታመኑ፣ የፍቅር ግንኙነትዎ እንዲቋረጥብዎ ያደርጋሉና። + +በመጨረሻ እግዚአብሔር በመስቀሉና በጠቅላላው የደህንነት እቅድ ሂደት ጻድቅ መሆኑ ይረጋገጣል። በቅድመ-ምጽአት ፍርድ፣ እግዚአብሔር በሚመለከቱት አለማት ፊት ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል። + +ከዚያም ከዳግም ምፃቱ በኋላ ባለው ፍርድ የተቤዣቸው ሰዎች “በመላእክት ላይ በሚፈርዱበት” ጊዜ (1 ቆሮ. 6:2, 3)፣ የተዋጁት መዛግብትን እንዲመረምሩና የአምላክን አሰራር ራሳቸው እንዲያውቁ በሚሰጣቸው ዕድል፣ እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑ ይረጋገጣል። ፍርዱም ሁልጊዜ በፍጹም ጽድቅና ፍቅር የተሞላ እንደሆነ ያስተውላሉ። ከመካከላችን መልስ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ጥያቄዎች የሌለው ማነው? ሁሉም ነገር ከመጠናቀቁ በፊት፣ ለጥያቄዎቻችን መልስ እናገኛለን (1 ቆሮ. 4፡5ን ይመልከቱ)። + +በመጨረሻም ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክራል (ፊል. 2፡10, 11)። ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ ትክክል ነው ተብሎ የሚረጋገጥበት አሰራር አካል ነው። \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/07.md b/src/am/ss/2025-01/11/07.md new file mode 100644 index 0000000000..32ac643545 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/07.md @@ -0,0 +1,24 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 14/03/2026 +--- + +የቤተክርስቲያን ምክሮች ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ከልብ በመጣር የሚገኝ ሽልማት” የተሰኘውን ርዕስ ጥራዝ 9 ከገጽ 285–288 ያንብቡ። + +"በእግዚአብሔር ምሪት ዙሪያ ግራ ያጋባን ነገር ሁሉ በሚመጣው አለም ግልፅ ይሆንልናል። ለመረዳት የሚከብዱ ነገሮች ማብራሪያ ያገኛሉ። የጸጋው ምስጢሮች በፊታችን ይገለጣሉ። ውስን የሆነው አእምሯችን ግራ መጋባትንና ያልተፈፀሙ ተስፋዎችን ብቻ በተረዳበት፣ እጅግ ፍጹምና የሚያምር ስምምነትን እናያለን። እጅግ ፈታኝ የሚመስሉ የሕይወት ልምምዶችን ወሰን የሌለው ፍቅሩ እንዳዘዛቸው እናውቃለን። ሁሉንም ነገሮች ለበጎ እንዲሆኑልን የሚያደርገውን የእርሱን ግሩም ጥንቃቄ ስንገነዘብ፣ በማይነገርና በከበረ ሐሤት ደስ ይለናል።”— ኤለን ጂ. ዋይት፣ የቤተክርስቲያን ምክሮች፣ ጥራዝ 9፣ ገጽ 286 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. የእግዚአብሔርን ችሮታዊ ምሪቶች ለመረዳት ግራ ተጋብተው ያውቃሉ? እንዲህ ያሉት ነገሮች ሁሉ በመጨረሻ ግልጽ እንደሚሆኑ ማወቅዎ እንዴት ያጽናናዎታል?` + +`2. ክርስቶስ ሰው ለመሆንና ለዚህ ዓለም ለመሞት የተዋቸውን ነገሮች ያሰላስሉ። ይህ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ሊታመን የሚችል ስለመሆኑ ምን እንደሚነግረን ያስቡ። ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል?` + +`3. የእግዚአብሔርን “ስም” በተመለከተ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው? ይህ እራሳችንን ክርስቲያን ብለን ለምንጠራ ሰዎች ምን አንድምታ አለው? ክርስቲያኖች አንዳንድ ጊዜ በክርስቶስ ስም ላይ ውርደትን የሚያመጡት በምን መንገዶች ነው? እኛስ ክርስቶስን መከተል በተግባር ምን እንደሚመስል ለማሳየት በሰፈራችን ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን?` + +`4. አሁን ስለ ክፋት ያሉን ምርጥ "መልሶች" እንኳን ያልተሟሉ ናቸው። እግዚአብሔር ብቻ ሊያመጣ የሚችለውን የመጨረሻውን የክፋት መፍትሄ እየጠበቅን ሳለ፣ በሥቃይ ላይ ወዳሉት ለመቅረብና በዚህ ዓለም ሰቆቃዎችን ለማስወገድ ወኪሎች እንሆን ዘንድ በተግባር ምን ማድረግ እንችላለን?` + +`5. በኢሳ. 53:4 ላይ ክርስቶስ "ደዌያችንን" እና "ሕመማችንን" የመሸከሙን እውነታ ያሰላስሉ። በመስቀል ላይ የደህንነትን እቅድ እና እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የከፈለውን ዋጋ እንድንገነዘብ የሚረዳን ምን ተፈፀመ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/11/info.yml b/src/am/ss/2025-01/11/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..083227acdd --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/11/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "ከዚህ በላይ ምን ማድረግ እችል ነበር?" + start_date: "08/03/2026" + end_date: "14/03/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/01.md b/src/am/ss/2025-01/12/01.md new file mode 100644 index 0000000000..fe8a1abcba --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/01.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ፍቅር እና ፍትሕ፡- ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት +date: 15/03/2026 +--- + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ማቴ. 22፡34–40፣ ዘካ. 7፡ 9–12፣ መዝ. 82፣ ሚክ. 6፡8፣ ማቴ. 23፡23–30፣ ሉቃ 10፡25–37። + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?” 1 ዮሐ. 4:20 + + + +በመጨረሻ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደሚያስተካክል እርግጠኞች ብንሆንም፣ እንደ ክርስቲያን በዚህ ምድር አሁን የምናደርገው ነገር አስፈላጊ ነው። ምንም እንኳን እግዚአብሔር (በታላቁ ተጋድሎ መርሆዎች ምክንያት) አሁን የማያስወግዳቸው ብዙ ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶችና ክፋቶች ቢኖሩም፣ በምንችለው ሁሉ የምናየውን ማንኛውንም ስቃይና ክፋት ለማቃለል መገልገያ ልንሆን አንችልም ማለት አይደለም። እንዲያውም እንደ ክርስቲያን ይህን የማድረግ ግዴታ አለብን። + +እንዳየነው ፍቅር እና ፍትሕ የተጋመዱ ናቸው፤ ሊነጣጠሉም አይችሉም። + +እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል። በዚህ መሠረት እግዚአብሔርን የምንወድ ከሆነ፣ ፍትሕንም እንወዳለን። + +በተመሳሳይም እግዚአብሔርን የምንወደው ከሆነ፣ እርስ በርሳችን እንዋደዳለን። እርስ በርስ የመዋደዳችን አንዱ ክፍል ደግሞ በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ደህንነት ማሰብ ነው። ሌሎች በድህነት፣ በጭቆና ወይም በማንኛውም ዓይነት ግፍ ሲሰቃዩ ሊገደን ይገባል። ሌሎች ሲጨቆኑ፣ አይቶ አንዳላየ መሆን የለብንም። ይልቁንም፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ፍትሕ ለማስፈን ምን ማድረግ እንደምንችል በግልም ሆነ በጋራ ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባናል። በዚህ መልኩ ፍፁም የሆነውን የጌታችንን ባሕርይ ያውም ጽድቁንና ፍቅሩን ለተበላሸው አለማችን ማንጸባረቅ እንችላለን። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/02.md b/src/am/ss/2025-01/12/02.md new file mode 100644 index 0000000000..90bdc8fc16 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/02.md @@ -0,0 +1,22 @@ +--- +title: ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት +date: 16/03/2026 +--- + +በዓለማችን ላይ በግልም ሆነ በጋራ የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ፍትሕ ለማስፈን ምን ማድረግ እንዳለብን ለማሰላሰል፣ አምላክ ባዘዘን ነገር ላይ በማተኮር መጀመር ተገቢ ነው። + +`ማቴ. 22:34–40ን ያንብቡ። ኢየሱስ የሕግ አዋቂውን ጥያቄ የመለሰው እንዴት ነው?` + + +ኢየሱስ ራሱ እንዳለው “ፊተኛይቱና ታላቂቱ ትእዛዝ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ” የምትለው ናት። በተጨማሪም ኢየሱስ “ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ” አለው። ይሁን እንጂ ትእዛዛቱ እነዚህ ብቻ አይደሉም። + +ደግሞም ኢየሱስ “በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል (ተንጠልጥለዋል)” ብሎ አስተማራቸው (ማቴ. 22፡37–40)። በእርግጥ እነዚህ ራሳቸው ከብሉይ ኪዳን የተጠቀሱ ናቸው። + +`ማቴ. 19:16–23ን ያንብቡ። ኢየሱስ ሀብታም ለሆነው ወጣት አለቃ ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ፣ በማቴ. 22 ላይ ለሕግ አዋቂው ጥያቄ ከሰጠው መልስ ጋር እንዴት ይዛመዳል?` + + +`በዚህ ታሪክ ላይ ምን እየሆነ ነበር? ኢየሱስ ለዚህ ሰው እንደዚህ የመለሰው ለምንድን ነው? በምንም የሕይወት ደረጃ ብንሆን፣ እነዚህ ገጠመኞች ለሁላችንም ምን ሊያስተምሩን ይገባል?` + +“ክርስቶስ ወጣቱን አለቃ ፍፁም የሆነ ክርስቲያናዊ ባሕርይ ሊኖረው የሚችልበትን ብቸኛ አማራጭ ነገረው። ምንም እንኳን የተናገራቸው ቃላት ከባድና አስጨናቂ ቢመስሉም፣ የጥበብ ቃላት ነበሩ። የወጣቱ አለቃ ብቸኛ የመዳን ተስፋው እነርሱን በመቀበልና በመታዘዝ ላይ የተመሰረተ ነበር። የነበረው ስልጣንና ንብረት ወደ ክፋት እንዲያዘነብል በባሕርይው ላይ ስውር ተፅእኖ እያሳደረበት ነበር። እነዚህ ነገሮች በተለየ ሁኔታ ከተወደዱ፣ የእግዚአብሔርን ቦታ ይወስዳሉ። ከእግዚአብሔር ትንሽ ወይም ብዙ ማስቀረት፣ የሞራል ጥንካሬውንና ብቃቱን የሚሸረሽርን ነገር ማቆየት ነበር። የዚህ ዓለም ነገሮች የማያስተማምኑና የማይጠቅሙ ቢሆንም፣ በልባችን ውስጥ ልዩ ቦታ ከሰጠናቸው፣ ትኩረታችንን ሁሉ የሚስቡ ይሆናሉ።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 520. + +`ምንም እንኳን እንደ ሀብታሙ ወጣት አለቃ ሁላችንም ያለንን ሁሉ እንድንሸጥ ባንጠራም፣ በውስጥህ የያዝከውና ካልተውከው በስተቀር ወደ ዘላለማዊ ጥፋት የሚያደርስህ ምን ሊሆን ይችላል?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/03.md b/src/am/ss/2025-01/12/03.md new file mode 100644 index 0000000000..cd07b02e2c --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/03.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ሁለቱ ታላላቅ ኃጢአቶች +date: 17/03/2026 +--- + +ኢየሱስ እንደተናገረው ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት እግዚአብሔርን መውደድና እርስ በርስ መዋደድ ናቸው። እነዚህን ትእዛዛት መፈጸም ደግሞ ሌሎችን በተግባር እንደምንወድ የሚያሳዩ መሥዋዕትነቶችን ያካትታል፤ ይህ ነው የኢየሱስን ፈለግ መከተል ማለት። + +`እንግዲህ ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት እግዚአብሔርን እና ሌሎችን መውደድ ከሆኑ፣ ሁለቱ ታላላቅ ኃጢአቶች ምንድን ናቸው? መዝ. 135:13–19ን ያንብቡ። ይህ በቃሉ ውስጥ አጽንዖት ስለተሰጠው የተለመደ ኃጢአት ምን ይገልፃል?` + + +`ብሉይ ኪዳን ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ስለ መውደድ አስፈላጊነት ያለማቋረጥ ይናገራል (ዘዳ. 6፡5ን ይመልከቱ)። ይህ ታላቅ ከሆነውና እግዚአብሔርን ከመውደድ ከሚቃረነው የጣዖት አምልኮ ኃጢአት ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለው። ዘካ. 7፡9–12ን ያንብቡ። ነቢዩ ዘካርያስ በዚህ ክፍል እንደተናገረው፣ እግዚአብሔር የሚቃወመው ምንድን ነው? ይህና የጣዖት አምልኮ ኃጢአት ከሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?` + +እግዚአብሔር በፍቅር ቁጣ የሚመልሰው በጣዖት አምልኮ ብቻ ሳይሆን፣ በሕዝቡ ላይ በግልም ሆነ በጋራ ለሚደርሰው በደል ጭምር ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ ግፍ ሲፈፀም ይቆጣል። + +በብሉይ ኪዳን ውስጥ ትኩረት የተሰጣቸው ሁለቱ ታላላቅ ኃጢአቶች፣ ከሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት ማለትም እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ከመውደድ አንፃር ያሉ ድክመቶች ናቸው ። ሁለቱ ታላላቅ ኃጢአቶች እግዚአብሔርን እና ሌሎችን አለመውደድ ናቸው። በአጭሩ እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ካልወደዳችሁ ትእዛዛቱን እየጠበቃችሁ አይደለም። + +`እርግጥ ነው 1 ዮሐ. 4:20, 21 እንዲህ ይላል:- “ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።” እግዚአብሔርን መውደድ ሌሎችን ከመውደድ ሊነጠል እንደማይችል እንዴት ሊገልፁ ይችላሉ? ይህንን የማይበጠስ ግንኙነት እንዴት ሊረዱት ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/04.md b/src/am/ss/2025-01/12/04.md new file mode 100644 index 0000000000..9b217f4960 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/04.md @@ -0,0 +1,19 @@ +--- +title: እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል +date: 18/03/2026 +--- + +`ቃሉ እግዚአብሔር ፍትሕን እንደሚወድና ክፋትን እንደሚጠላ ይናገራል (ለምሳሌ መዝ. 33፡5፣ ኢሳ. 61፡8)። የፍትሕ መጓደልም እጅግ ስለሚያሳስበው፣ በፍትሕ መጓደል ለተበደሉት ሁሉ የጽድቅ ቁጣው ይነዳል። በብሉይና በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ እግዚአብሔር ለተገፉና ለተጨቆኑ ያለማቋረጥ በቅናት ይነሳል፤ በበዳዮችና በጨቋኞች ላይም የጽድቅ ቁጣውን ይገልጻል። መዝ. 82ን ያንብቡ። ይህ መዝሙር እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ፍትሕ ግድ እንደሚለው የሚገልጸው እንዴት ነው? ዛሬስ ለእኛ ምን ትርጉም ይኖረዋል?` + + +ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች እንደሚረዱት፣ ይህ ክፍል በህብረተሰቡ ውስጥ ለሚፈጠረው የፍርድ መጓደል ተጠያቂ የሆኑትን ምድራዊ ገዥዎች የሚያወግዝ ሲሆን፣ በተጨማሪም እግዚአብሔር በዘቀጡ ምድራዊ ዳኞችና ገዥዎች ጀርባ ባሉት የአጋንንት ኃይሎች ("አማልክት") ላይ የሚፈርድበትን ጊዜ ይጠቁማል። + +በተለይ ለምድራዊ ገዥዎቹ፡- “እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለኃጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል (መዝ. 82:2)። + +በተጨማሪም “ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ፤ ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው” ተብለው ታዘዋል (መዝ. 82:3, 4)። በዚህና በሌሎች ጥቅሶች፣ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ግልፅ የሆነ የፍትሕ ጥሪን አቅርበዋል። ይህ በቃሉ ውስጥ ትኩረት የተነፈገው ጉዳይ አይደለም፤ የብሉይ ኪዳን ነቢያት መልእክት እምብርት እና ኢየሱስ በምድር በሥጋ በነበረበት ጊዜ የተናገረው ዋና ነገር ነው። + +እርሱን እንደሚወዱትና እንደሚታዘዙት ከሚናገሩት እግዚአብሔር የሚሻውና የሚፈልገው ነገር የተሰወረ አይደለም። በሚክ. 6: 8 በግልፅ “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?” በማለት አስቀምጦታል። + +ይህ ሐሳብ በቃሉ ውስጥ ተስተጋብቷል። ለምሳሌ፡- ኢየሱስ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፣ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” ብሎ ተናግሯል (ዮሐ. 13፡35፤ ከ1 ዮሐ. 4፡8-16 ጋር ያስተያዩት)። + +`በሚክ. 6፡8 ላይ ብናተኩርና ሆን ብለን በቃልም ሆነ በሥራ ብንተገብረው፣ ቤተሰቦቻችን እና ቤተክርስቲያኖቻችን ምን ይመስሉ ነበር? በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን፣ እነዚህ መርሆዎች እንዴት በተሻለ ሁኔታ ሊተገበሩ ይችላሉ?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/05.md b/src/am/ss/2025-01/12/05.md new file mode 100644 index 0000000000..fdbfbe5e64 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/05.md @@ -0,0 +1,15 @@ +--- +title: ፍትሕ ለማስፈን ተጠርተናል +date: 19/03/2026 +--- + +በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነቢያት በማህበረሰብ መካከል ፍትሕ እንዲኖር የእግዚአብሔርን ጥሪ ያለማቋረጥ አቅርበዋል። በተደጋጋሚ ቃሉ የኢ- ፍትሐዊነትንና የጭቆናን አስከፊነት ከማጉላት ወደ ኋላ አይልም። በእርግጥ እግዚአብሔርን እንዲፈርድ መጠየቅ በራሱ፣ ፍትሕን እንዲያሰፍን መለመን ነው። + +ለምሳሌ ነቢዩ ኢሳይያስ በጊዜው በእሥራኤል የነበረውን ግፍ በቀጥታ ይኮንናል። የፍትሕ ጥሪው ግልፅና ከፍ ባለ ድምፅ ዛሬም በጆሯችን ሊሰማን ይገባል። "መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ” (ኢሳ. 1፡17)። ከዚህም በተጨማሪ “የግፍን ትእዛዛት ለሚያዙ፣ የድሀውንም ፍርድ ለሚያጣምሙ ወዮላቸው” በማለት ያውጃል (ኢሳ. 10:1, 2)። “በተጎበኛችሁበት ቀን፥ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለረድኤትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ክብራችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?” እያለም ያስጠነቅቃቸዋል (ኢሳ. 10:3)። + +`በተመሳሳይም ነቢዩ ኤርምያስ የእግዚአብሔርን መልእክት እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዓመፅ ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው… ወዮለት! በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። የድሀውንና የችግረኛውን ፍርድ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።” (ኤር. 22:13, 15, 16 ) ማቴ. 23:23–30ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ኢየሱስ በጣም አስፈላጊ ስለሆነው ነገር ምን ያስተምረናል? “ዋና ነገሮች” ሲልስ ምን ማለቱ ይመስልዎታል?` + + +አንድ ሰው የፍትሕ መጓደል የብሉይ ኪዳን ነቢያት ጉዳይ ብቻ እንደሆነ እንዳያስብ፣ በዚህና በሌሎች ጥቅሶች ይህ ነገር በአገልግሎቱ ወቅት ኢየሱስን ራሱን እጅግ ያሳስበው እንደነበር በግልጽ እንመለከታለን። እንዲህ ነበር ያለው፡ - “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር” (ማቴ. 23፡23)። በሉቃስ ውስጥ ባለው ተመሳሳይ ክፍል፣ ኢየሱስ “ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ ስለሚተላለፉ” ያዝናል (ሉቃ. 11፡42)። + +`ዛሬ “በዋና ነገሮች” ላይ ማተኮር ቢኖርብዎት፣ በምትኩ ከምናተኩርበት “ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ከማውጣት” በተቃራኒ፣ ምን ሊመስል ይችላል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/06.md b/src/am/ss/2025-01/12/06.md new file mode 100644 index 0000000000..9314125058 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/06.md @@ -0,0 +1,18 @@ +--- +title: ባልንጀራዬ ማን ነው? +date: 20/03/2026 +--- + +ሉቃስ እንደዘገበው፣ ኢየሱስ እግዚአብሔርን ስለ መውደድ እና ባልንጀራን ስለ መውደድ ሁለቱን ታላላቅ ትእዛዛት ከተናገረ በኋላ፣ አንድ ሕግ አዋቂ “ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን፡- ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው” ሉቃ. 10፡29)። ለዚህ ምላሽ ኢየሱስ አሁን እጅግ የሚታወቀውን፣ በዚያን ጊዜ ግን አስደንጋጭ የነበረውን፣ የመልካሙን ሳምራዊ ምሳሌ ተናገረ። + +`በሉቃ. 10፡25-37 ላይ የሚገኘውን የመልካሙን ሳምራዊ ምሳሌ ያንብቡ። ይህ ክፍል፣ ነቢያት ለምሕረትና ለፍትሕ እንዲሁም የተለያዩ ቡድኖች በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ "በሌሎች" ላይ ስላደረሱት ግፎች ካስተጋቡት ጩኸት አንፃር፣ ምን እያለ ነው?` + +ኢየሱስ ስለ ፍትሕ ለመናገር ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕን ሊያሰፍን መጣ። + +እርሱ ያኔም ሆነ ወደፊት የነቢያት የፍትሕ ጥሪና ናፍቆት ፍጻሜ ነው (ሉቃ. 4፡ 16–21ን ከኢሳ. 61፡1, 2 አንፃር ይመልከቱ)። እርሱ የአህዛብ ሁሉ ምኞት ነው – በተለይም አዳኝ እንደሚያስፈልጋቸው ለሚገነዘቡ ሰዎች። + +`ሥልጣን ለመያዝና የእግዚአብሔርን ዙፋን በኃይል ለመቀማት ከፈለገው ጠላት በተቃራኒ፣ ኃጢአት የሌለበት ኢየሱስ ራሱን ዝቅ በማድረግ በኃጢአት፣ በግፍና በጭቆና ሥር ከነበሩት ጋር ተቆጠረ። ፍትሕን ያሰፍን ዘንድ፣ ጻድቅ እንዲሆንና በእርሱም የሚያምኑትን ሁሉ ያጸድቅ ዘንድ፣ በፍቅር ራሱን አሳልፎ በመስጠት ጠላትን ድል አደረገ። ክርስቶስ የሕጉ ዋና ነገሮች ብሎ ለሚጠራቸው ደንታ ከሌለን፣ ክርስቶስ ሊያፀናው ለሞተው ሕግ ግድ ይለናል ማለት የምንችለው እንዴት ነው?` + +መዝ. 9:8, 9 “እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል። እግዚአብሔርም ለድሆች (ለተጨቆኑ) መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው” ይላል። በተመሳሳይም መዝ. 146:7–9 እንዲህ በማለት ያክላል፡- እግዚአብሔር “ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታል፤ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፤ ድሀ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል፤ የኃጢአተኞችንም መንገድ ያጠፋል።” + +`በዙሪያችን የተቸገሩትንና የሚሰቃዩትን ለማገልገል መፈለግ እንዳለብን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከዚህ በላይ ምን ያህል ግልጽ ሊሆን ይችላል? የተቸገሩትን ለመርዳት ከኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ምን እንማራለን? ምንም እንኳን እንደርሱ ተአምራትን ማድረግ ባንችልም፣ ለሚሰቃዩ ብዙ ሰዎች የእኛ እርዳታ እንዴት "ተአምር" ሊሆን ይችላል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/07.md b/src/am/ss/2025-01/12/07.md new file mode 100644 index 0000000000..7c1c5241ee --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/07.md @@ -0,0 +1,28 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 21/03/2026 +--- + +የዘመናት ምኞት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ሰንበት” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 281–289 ያንብቡ። + +“ሰላዮቹ ችግር እንዳይገጥማቸው በመፍራት፣ በሕዝቡ ፊት ለክርስቶስ መልስ ለመስጠት አልደፈሩም። እውነትን እንደተናገረ ያውቁ ነበር። ወጋቸውን ከመተላለፍ ይልቅ አንድን ሰው እንዲሰቃይ ይተውት ነበር፤ ነገር ግን ችላ ከተባለ በባለቤቱ ላይ የገንዘብ ኪሳራ ስለሚያደርስ እንሰሳውን ይንከባከቡ ነበር። በእግዚአብሔር አምሳል ከተፈጠረው ሰው ይልቅ ለእንስሳ የበለጠ ጥንቃቄ ይደረግለት ነበር። ይህም የሐሰተኛ ሃይማኖቶችን ሥራ ያሳያል። እነርሱ የሚመነጩት የሰው ልጅ ራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ለማድረግ ካለው ፍላጎት ነው፣ ነገር ግን ሰውን ከእንሰሳ በታች ያዋርዳሉ። + +የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት የሚቃወም ማንኛውም ሃይማኖት፣ ሰው በፍጥረት ጊዜ የተጎናፀፈውንና በክርስቶስ የሚመለስለትን ክብር ይገፈዋል። ማንኛውም የሐሰት ሃይማኖት ተከታዮቹን ለሰዎች ችግር፣ ስቃይና መብት ግድየለሾች እንዲሆኑ ያስተምራል። ወንጌል በክርስቶስ ደም ለተገዛው የሰው ልጅ ከፍ ያለ ዋጋ ይሰጠዋል፣ እናም ለሰው ልጅ ችግርና አበሳ እንድንራራ ያስተምራል። + +ጌታ፡- ‘ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፥ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል’ ይላል (ኢሳ. 13፡12)። + +“ኢየሱስ ፈሪሳውያንን በሰንበት ቀን መልካም ወይስ ክፉ ማድረግ፣ ሕይወት ማዳን ወይስ መግደል ተፈቅዶ እንደሆነ ሲጠይቃቸው፣ የነበራቸውን ክፉ ዓላማ እየተገዳደረ ነበር። እርሱ ሕይወትን እያዳነ ለብዙዎች ደስታን ሲያመጣ፣ እነርሱ ግን በመራር ጥላቻ ህይወቱን ለማጥፋት ያሳድዱት ነበር። በሰንበት እርሱ እንዳደረገው ድውያንን መፈወስ ወይስ እነርሱ ሊያደርጉ እንዳሰቡት መግደል ይሻል ነበር? በእግዚአብሔር ቅዱስ ቀን በልብ ውስጥ ያለ የመግደል ሐሳብ፣ ከፍቅር የተነሳ ለሰው ሁሉ በርኅራኄ ከሚገለጽ መልካም ሥራ ይልቅ ጽድቅ ነበርን?”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 286–287 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + + +`1. “ማንኛውም የሐሰት ሃይማኖት ተከታዮቹን ለሰዎች ችግር ግድየለሾች እንዲሆኑ ያስተምራል” የሚለው እውነት የሆነው ለምንድን ነው? በቤተ-ክርስቲያናችንም ሆነ በውጭ እንደዚህ አይነት ግድየለሽነትን ለማስወገድ ሆን ብለን እንዴት መንቀሳቀስ እንችላለን?` + +`2. ባልንጀራዬ ማን ነው? ባልንጀራህስ ማን ነው? ክርስቶስን መከተላችን፣ ፍቅርን በተግባር ለማሳየት በዘመኑ የነበረውን የጥል ግድግዳ እንዳፈረሰው ሳምራዊ እንድንሆን የሚያደርገን በምን በምን መንገዶች ነው?` + +`3. እግዚአብሔር ፍትሕንና ምሕረትን የሚወድ ከሆነ፣ በእርሱ ዘንድ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ኢየሱስ “የሕጉ ዋና ነገሮች” ባላቸው ላይ ይበልጥ የምናተኩረው እንዴት ነው?` + +`4. ስለ ፍርድ ስናስብና ስንነጋገር፣ ኢየሱስ ስለ ፍርድ የተናገረበት ዋናው መንገድ ሌሎችን በተለይም የተጨቆኑትንና የተገፉትን በተግባር መውደድን አስመልክቶ መሆኑን ምን ያህል አጽንዖት እንሰጠዋለን? ይህንን ከማቴ. 25፡31-46 አንፃር ያሰላስሉ።` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/12/info.yml b/src/am/ss/2025-01/12/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..31a1dc1b2e --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/12/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "ፍቅር እና ፍትሕ፡- ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት" + start_date: "15/03/2026" + end_date: "21/03/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/01.md b/src/am/ss/2025-01/13/01.md new file mode 100644 index 0000000000..8087bf4d33 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/01.md @@ -0,0 +1,20 @@ +--- +title: ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው +date: 22/03/2026 +--- + + +### ለዚህ ሳምንት ጥናት፡ +ዘጸ. 20:1–17፣ ሮሜ 6፡ 1–3፣ ሮሜ 7:7–12፣ ኤር. 31:31–34፣ ማቴ. 23:23, 24፣ ያዕቆብ 2፡1-9 + +>

የመታሰቢያ ጥቅስ

+> “እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።” ሮሜ 13፡8 + + +በቦርድ ስብሰባ ላይ ስለ አንድ አስቸጋሪ የቤተክርስቲያን አባል ሲነጋገሩ፣ አንድ ሰው ቄሱን፣ “በርኅራኄ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማድረግ አንችልም” አለው። አንችልም እንዴ? ቄሱ ይህ ሰው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሕጉ ያለው ግንዛቤ ምን እንደሆነ ግራ ሳይጋባ አይቀርም። ከሰዎች፣ በተለይም ከተሳሳቱት፣ ጋር ባለን ግንኙነት ርኅራኄ ማዕከላዊ መሆን አለበት። ርኅራኄ የፍቅር አንዱ ክፍል ነው፣ እናም ሮሜ 13፡8 እንደሚናገረው ባልንጀራችንን መውደድ ሕግን መፈጸም ነው። + +በእርግጥ ፍቅር የሕግ ፍፃሜ ከሆነ፣ ሕግን ከፍቅር ነጥለን ወይም ፍቅርን ከሕግ ጋር እንደማይገናኝ አድርገን እንዳናስብ መጠንቀቅ አለብን። በቃሉ ውስጥ ፍቅር እና ሕግ የማይነጣጠሉ ናቸው። ሕግን የሰጠን አምላክ ፍቅር ነው፣ በዚህም መሠረት የእግዚአብሔር ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ኤለን ጂ. ኋይት እንደፃፈችው፣ ሕጉ የእግዚአብሔር ባሕርይ መግለጫ ነው። (የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 305ን ይመልከቱ) + +የእግዚአብሔር ሕግ የማይስተዋል የመርሆች ስብስብ አይደለም፣ ነገር ግን ይሳካልን ዘንድ የተሰጡን ትዕዛዛቶችና መመሪያዎች ናቸው። እግዚአብሔር ራሱ እንደገለፀው፣ ሕጉ የፍቅር መግለጫ ነው። + +_የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።_ \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/02.md b/src/am/ss/2025-01/13/02.md new file mode 100644 index 0000000000..e588839692 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/02.md @@ -0,0 +1,19 @@ +--- +title: የፍቅር ሕግ +date: 23/03/2026 +--- + +የእግዚአብሔር ሕግ የማይስተዋሉ መርሆዎችን የያዘ አይደለም፣ ይልቁንም ግንኙነትን የሚያሳይ ነው። ይህ ደግሞ በአሥርቱ ትእዛዛት በግልፅ ይታያል። የአሥርቱ ትእዛዛት መሠረታዊ መርሆች በኤደን ገነትም ነበሩ፣ በእግዚአብሔር እና በሰዎች እንዲሁም በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚቆጣጠሩት የፍቅር መርሆዎች ነበሩ። + +በዘጸ. 20 ላይ አሥርቱ ትእዛዛት በድንጋይ ጽላት ሲጻፉ፣ ለእሥራኤል የተሰጡት በቃል ኪዳን ግንኙነት አውድ ነው። ትእዛዛቱ የተጻፉት ጌታ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣቸው በኋላ ነው፣ ትእዛዛቱም የተመሰረቱት በእግዚአብሔር ፍቅርና ለሕዝቡ በገባው ተስፋዎች ላይ ነው (ዘጸ. 6፡7, 8 እና ዘሌ. 26፡12)። በአሥሩ ትእዛዛት ውስጥ ያሉት ሁለት ክፍሎች ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በርስ ያለው ግንኙነት እንዲሰምር ያለሙ መሆኑን ማየት ይቻላል። + +`ዘጸ. 20:1-17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔርን መውደድ እና ሌሎችን መውደድ የሚለውን ሁለቱን መርሆዎች የሚገልጹት እንዴት ነው?` + + +የመጀመሪያዎቹ አራት ትእዛዛት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያመለክቱ ሲሆን፣ የመጨረሻዎቹ ስድስት ትእዛዛት ደግሞ በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳያሉ። ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በእግዚአብሔር ሕግ መርሆዎች መመራት አለበት። + +እነዚህ የሕጉ ሁለት ክፍሎች ኢየሱስ ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት ብሎ ከገለጸላቸው ጋር በቀጥታ ይዛመዳሉ—“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ ውደድ” (ማቴ. 22:37፤ ከዘዳ. 6፡ 5 ጋር ያስተያዩ) እና “ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ” (ማቴ. 22፡39፤ ከዘሌ. 19፡18 ጋር ያስተያዩ)። + +የመጀመሪያዎቹ አራት ትእዛዛት እግዚአብሔርን በሙሉ ማንነታችን የምንወድባቸው መንገዶች ሲሆኑ፣ የመጨረሻዎቹ ስድስት ትእዛዛት ደግሞ እርስ በርሳችን እንደ ራሳችን የምንዋደድባቸው መንገዶች ናቸው። ኢየሱስ እነዚህ ሁለት ታላላቅ የፍቅር ትእዛዛት ከሕጉ ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን በግልፅ ተናግሯል። "በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል" አላቸው (ማቴ. 22:40)። + +`ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር እና ሕግ የማይነጣጠሉ ናቸው። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሕጉን መጠበቅ አያስፈልገንም፣ እግዚአብሔርን እና ሌሎችን መውደድ ነው የሚገባን ሲሉ እንሰማለን። ለምንድነው ይህ ሐሳብ ትርጉም የማይሰጠው? ከአሥርቱ ትእዛዛት አንዱን የምተላለፍ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወይም ለሌሎች ያለንን ፍቅር እንዴት ልንገልጽ እንችላለን?` diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/03.md b/src/am/ss/2025-01/13/03.md new file mode 100644 index 0000000000..04e23005ff --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/03.md @@ -0,0 +1,21 @@ +--- +title: ሕጉ ቅዱስና ጻድቅ በጎም ነው +date: 24/03/2026 +--- + +ፍቅር የእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ነው። እግዚአብሔር ሕግን ሲያፀና፣ ፍቅርንም እንዲሁ ያፀናል። ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን የሞተው ሕግን ሲያፀና ሳለ፣ ለእኛም ጸጋውን ይሰጥ ዘንድ ነው። ስለዚህ እርሱ ጻድቅ እና በእርሱ የሚያምኑትን የሚያጸድቅ ሊሆን ይችላል (ሮሜ 3፡25, 26)። እንዴት ያለ የፍቅር መግለጫ ነው! በዚህ መሠረት ሕጉ በደህንነት ሂደት አልተሻረም፤ ይልቁንም የበለጠ ፀና እንጂ። + +`ሮሜ 6፡1–3ን፣ ከዚያም ሮሜ 7፡7–12ን (ቁጥር 12 ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ) ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ ከሞተ በኋላም ስለ ሕጉ ምን ይነግሩናል?` + + +አንዳንዶች ጸጋና ቤዛ መሆን ሕግን ያስወግዳሉ ብለው ቢያምኑም፣ ጳውሎስ ግን ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት መቀጠል እንደሌለብን በግልጽ ይናገራል። + +ይልቁንም በእምነት በክርስቶስ የሆኑት “ከሞቱ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ተጠምቀዋል።” ስለዚህ ራሳቸውን ለኃጢአት እንደሞቱና ለክርስቶስ ሕያዋን እንደሆኑ መቁጠር አለባቸው። + +የእግዚአብሔር ሕግ ኃጢአት አይደለም፣ ነገር ግን ኃጢአትንና ኃጢአተኛነታችንን በግልጽ ያሳየናል። ለዚህ ነው “ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት” የሚለው (ሮሜ. 7፡12)። ሕጉ መዳንና መቤዠት እጅግ እንደሚያስፈልገን፣ ያም መዳን እና መቤዠት ደግሞ በክርስቶስ ብቻ እንደሚገኝ ያሳየናል። “እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ” (ሮሜ. 3፡31)። + +ክርስቶስ የመጣው ሕግን ለመሻር ሳይሆን በሕግና በነቢያት የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሁሉ ሊፈጽም ነው። ስለዚህ “ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም” በማለት በአጽንዖት ተናግሯል (ማቴ. 5፡18)። + +የእግዚአብሔር ሕግ የአምላክን ቅድስና ያሳያል - ያውም ፍጹም የሆነውን የፍቅር፣ የጽድቅ፣ የበጎነትና የእውነት ባሕርይውን (ዘሌ. 19:2፣ መዝ. 19:7, 8፣ መዝ. 119:142, 172)። በዚህ ረገድ እንደ ዘጸ. 31፡18 እግዚአብሔር አሥርቱን ትእዛዛት በድንጋይ ጽላቶች ላይ ራሱ መጻፉ ትልቅ ትርጉም አለው። በድንጋይ የተጻፉት እነዚህ ሕጎች ስለማይለወጠው የእግዚአብሔር ባሕርይና በፍቅር ላይ ስለተመሰረተው የእርሱ የሞራል መንግሥት ምስክሮች ናቸው— ይህም የታላቁ ተጋድሎ ዋና ጭብጥ ነው። + +`ይህ በሕግ እና በፍቅር መካከል ያለው ግንኙነት የኢየሱስን “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ. 14፡15) የሚለውን ቃል የበለጠ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/04.md b/src/am/ss/2025-01/13/04.md new file mode 100644 index 0000000000..9cee174f5d --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/04.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: ሕግ እና ጸጋ +date: 25/03/2026 +--- + +እንዳየነው ሕግና ጸጋ እርስ በርሳቸው አይቃረኑም። ይልቅስ በእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ የተመሰረተ የተለያየ ጥቅም አላቸው። በሕግ እና በጸጋ መካከል አሁን የሚታየው (አላስፈላጊ የሆነ) የጎላ ንፅፅር የጥንት እሥራኤላውያንን ግራ ሊያጋባቸው ይችል ነበር፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕጉን የሰጣቸው የጸጋውን ታላቅነት ሊያሳያቸው እንደሆነ አድርገው ይመለከቱት ስለነበር ነው። በዙሪያቸው የነበሩት ህዝቦች “አማልክቶቻቸው” ተለዋዋጭና ግራ የሚያጋቡ በመሆናቸው፣ ሰዎች “አማልክት” ምን እንደሚፈልጉና ምን እንደሚያስደስታቸው የሚያውቁበት መንገድ አልነበረም። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ግን ለሕዝቡ እርሱን የሚያስደስተውን ነገር በግልጽ ያስተምራቸዋል። + +እርሱን የሚያስደስተውም ለሕዝቡ በሙሉ በግልና በጋራ የሚበጃቸው ነው። + +ሆኖም ሕጉ ከኃጢአት ሊያድነን ወይም ልባችንን ሊለውጠው አይችልም። በተፈጥሯችን ኃጢአተኛ ስለሆንን፣ መንፈሳዊ የሆነ የልብ ንቅለ- ተከላ ያስፈልገናል። + +ኤር.31:31-34ን ያንብቡ። ይህ እግዚአብሔር አዲስ ልብ ሊሰጠን ስለገባቸው ተስፋዎች ምን ያስተምረናል? ይህንን ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐ. 3፡1-21 ላይ እንደገና ስለ መወለድ ከተናገረው ጋር ያስተያዩ። ደግሞም ዕብ. 8፡10ን ይመልከቱ። + + +አሥርቱን ትእዛዛት በድንጋይ ጽላቶች ላይ የፃፋቸው እግዚአብሔር ራሱ ነበር (ዘጸ. 31፡18)፣ ሆኖም ሕጉ በእግዚአብሔር ሕዝብ ልብ ውስጥም መፃፍ ነበረበት (መዝ. 37፡30, 31)። የእግዚአብሔር የፍቅር ሕግ ለኛ ውጫዊ ሳይሆን የባሕርያችን ክፍል ሊሆን ይገባ ነበር። በሰዎች ልብ ውስጥ ሕጉን መፃፍ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ይህንንም ለማድረግ ለቃል ኪዳን ሕዝቡ ቃል ገብቷል (ዕብ. 8፡10ን ይመልከቱ)። + +ሕግን በመጠበቅ ራሳችንን ማዳን አንችልም። ይልቁንም የዳንነው በጸጋው በእምነት ነው፣ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በራሳችን አይደለም (ኤፌ. 2፡8)። ሕጉን የምንጠብቀው ለመዳን አይደለም፤ አስቀድመን ስለዳንን እንጂ። + +ሕጉን የምንጠብቀው ለመወደድ አይደለም፤ ስለተወደድን ነው እንጂ፣ ስለዚህ እግዚአብሔርንና ሌሎችን ለመውደድ እንፈልጋለን (ዮሐ. 14፡15ን ይመልከቱ)። + +ሕጉ ኃጢአታችንን ያሳየናል (ያዕ. 1፡22-25፣ ሮሜ 3፡20፣ ሮሜ 7፡ 7)፣ አዳኝ እንደሚያስፈልገን ይጠቁመናል (ገላ. 3፡22-24)፣ መልካም በሆነው የሕይወት ጎዳና ይመራናል፣ የእግዚአብሔርንም የፍቅር ባሕርይ ይገልፅልናል። + +`በፍርድ ጊዜ ያለህ ተስፋ ምንድን ነው? ተግተህ በታማኝነት ሕጉን መጠበቅህ ነው ወይስ የክርስቶስ ጽድቅ ነው የሚሸፍንህ? መልስህ የእግዚአብሔር ሕግ ሊያደርግ የሚችለውን ወይም የማይችለውን ተግባር በተመለከተ ምን ይነግርሃል?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/05.md b/src/am/ss/2025-01/13/05.md new file mode 100644 index 0000000000..2a8b8e8b8e --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/05.md @@ -0,0 +1,17 @@ +--- +title: ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው +date: 26/03/2026 +--- + +በፍቅር እና በሕግ መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ ነው። + +በእርግጥ ቃሉ እንደሚናገረው ፍቅር ማለት ሕግን መፈጸም ነው። + +`በሮሜ 13፡8-10 ጳውሎስ “ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል” ሲል አስተምሯል (ሮሜ 13፡8)። ከአሥርቱ ትእዛዛት ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ከስድስቱ ብዙዎቹን ከዘረዘረ በኋላ፣ ጳውሎስ እነዚህ ሁሉ "ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልለዋል" ይላል (ሮሜ. 13፡9)። በእርግጥም ጳውሎስ በግልጽ “ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው” በማለት ያስተምራል (ሮሜ. 13፡10)። በገላ. 5፡ 14 ደግሞ ጳውሎስ “ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፡- ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው” ሲል ገልጿል (ገላ. 5፡14)። ሕግን የሚፈጽመው ግን ምን ዓይነት ፍቅር ነው? እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ምን ይመስላል? ማቴ. 23:23, 24ን ያንብቡ። “የሕጉ ዋና ነገሮች” ምንድን ናቸው? ዘዳ. 5:12–15ን እና ኢሳ. 58:13, 14ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በሕጉ (በተለይም በሰንበት ትእዛዝ) እና አምላክ ለፍትሕና ለነፃነት ባለው ትኩረት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?` + + +ኢየሱስ “የሕጉ ዋና ነገሮች” ሲል የገለፃቸው “ፍርድና ምሕረት ታማኝነትም ” ናቸው። በተለይም አንዱን ሕግ (ሰንበትን) በተመለከተ፣ በቃሉ ውስጥ ሰንበት ነጻ ከመውጣትና ከፍትሕ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እናያለን። + +በዘዳ. 5 ላይ የሰንበት ትእዛዝ የተመሰረተው እግዚአብሔር እሥራኤልን ከባርነት ነፃ ከማውጣቱ ጋር በተገናኘ ነው። ይኸውም ሰንበት የፍጥረት መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን፣ ከባርነት እና ከጭቆናም ነፃ የመውጣት መታሰቢያ ነው። ፈቃዳችንን ከማድረግ ተመልሰን ሰንበትን ደስታ ብንለው በጌታም ደስ ብንሰኝ (ኢሳ. 58:13, 14) የሚለው ትኩረቱ ለሌሎች የፍቅርና የፍትሕ ሥራዎችን መፈፀም ላይ ነው፡- ይህም በጎ ማድረግ፣ የተራቡትን መመገብ፣ ቤት የሌላቸውን ማስጠጋት ናቸው (ኢሳ. 58፡3–10ን ይመልከቱ)። + +ከእነዚህና ሌሎችም ብዙ ትምህርቶች የተነሳ፣ ሕግን በፍቅር ለመፈጸም የሚፈልጉ፣ የሚፈፅሟቸው ኃጢአቶች ብቻ ሳይሆን፣ በጎ መሆናቸውን እያወቁ በቸልተኝነት የማያደርጓቸው ነገሮች ጭምር ሊያሳስቧቸው ይገባል። ፍቅር የሕግ ፍጻሜ እንደመሆኑ መጠን፣ ሕግን መጠበቅ ኃጢአትን ከመሥራት መቆጠብ ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕንና ምሕረትን በታማኝነት የሚያሰፍኑ በጎ የፍቅር ሥራዎችን በትጋት መሥራትን ይጨምራል። ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን የፊደል ሕጉን ካለመተላለፍ በላይ ነው። diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/06.md b/src/am/ss/2025-01/13/06.md new file mode 100644 index 0000000000..1623236211 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/06.md @@ -0,0 +1,26 @@ +--- +title: ከሁሉም በላይ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ +date: 27/03/2026 +--- + +ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ከሆነ፣ አንድ ሰው ስህተት የሆኑ ነገሮችን ከማድረግ በመቆጠብ ብቻ የእግዚአብሔርን ሕግ በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ አይችልም። + +በቃሉ የተገለፀው የፍቅር ሕግ ክፉ እንዳናደርግ የሚያዘን ብቻ ሳይሆን፣ ሕጉ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች የሚገልፁ ተግባራትን እንድንፈጽም ይገፋፋናል። + +ይህም ለቤተ ክርስቲያን አባላት ብቻ ሳይሆን በአለም ላሉ ሁሉ ጭምር እንጂ ምክንያቱም አለማችን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ምሥክርነት እጅግ ያስፈገዋልና። + +`ያዕ. 2፡1-9ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ምን ወሳኝ የሆነ መልእክት ተሰጥቶናል?` + +እዚህ ላይ ያዕቆብ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት፣ በተለይም ድሆችን ማዋረድንና የአንዳንድ ሀብታሞችን ጭቆና ይኮንናል። ከዚያም ለባልንጀራችን ወደተሰጠን የፍቅር ሕግ ትኩረታችንን ስቦ፣ ይህንን ሕግ ብትፈጽሙ "መልካም ታደርጋላችሁ " ይላል (ያዕ. 2፡8)። + +ኤለን ጂ. ዋይት እንደገለፀችው፡- “ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር የምንገልፀው ለሰው ባለን ፍቅር ነው። ይህንን ፍቅር በውስጣችን ለማሳደር፣ የአንድ ቤተሰብ ልጆችም ሊያደርገን፣ የክብር ንጉሥ ከእኛ ጋር አንድ ሆነ። እናም ‘እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ’ (ዮሐ. 15፡12) የሚለው የስንብት ቃሉ ሲተገበር፣ ማለትም እርሱ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን መውደድ ስንችል፣ ያን ጊዜ ለእኛ ያለው ተልዕኮ ይፈፀማል። ለሰማይም ገጣሚዎች እንሆናለን፣ ምክንያቱም በልባችን ውስጥ ሰማይ አለና።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 641 + +ክርስቶስ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን ስንወድ፣ ያኔ ለሰማይ ገጣሚዎች እንሆናለን። የኢየሱስ ተከታይ ስለ መሆን እንዴት ያለ ግሩም መግለጫ ነው! + +ኢየሱስ ተከታዮቹን “እኔ እንደ ወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" ብሎ ያዛቸዋል (ዮሐ. 13:34)። ደግሞም ኢየሱስ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” ይላል (ዮሐ. 13፡35)። + +ፍቅር የክርስቲያን እምነት ማዕከል ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና (1 ዮሐ. 4: 8, 16)። እግዚአብሔርን እንወዳለን የሚሉም እርስ በርሳቸው ሊዋደዱ ይገባል (ከ1ኛ ዮሐ. 3፡11፤ 4፡20, 21 ጋር ያስተያዩ)። + +በዚህም መሠረት 1 ጴጥ. 4: 8 ክርስቲያኖችን:- “ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ " በማለት ይመክራል። + +ክርስቶስ አለምን እንደ ወደደ፣ እኛም እንደ እርሱ አለምን መውደድ ይኖርብናል የሚለውን ሃሳብ ያሰላስሉ። ይህ ስለ ክርስቲያን ፍጽምና ጽንሰ-ሐሳብ እና ለዘለአለም ሕይወት እንዴት ገጣሚ እንደምንሆን በተሻለ ሁኔታ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው? መልስዎን በሰንበት ወደ ክፍልዎ ይዘው ይምጡ። \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/07.md b/src/am/ss/2025-01/13/07.md new file mode 100644 index 0000000000..833e3f97c8 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/07.md @@ -0,0 +1,23 @@ +--- +title: ተጨማሪ ሀሳብ +date: 28/03/2026 +--- + +የዘመናት ምኞት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 637–641 ያንብቡ። + +“ሌሎችን የሚያገለግሉ፣ በእረኞቹ አለቃ አገልግሎትን ያገኛሉ። እነርሱ ራሳቸው የሕይወትን ውኃ ይጠጣሉ፣ ይረካሉም። አስደሳች ፈንጠዝያዎችን ወይም በሕይወታቸው ውስጥ ለውጦችን አይመኙም። የሚያንገበግባቸው ርዕስ የሚጠፉ ነፍሳትን እንዴት እናድን የሚለው ይሆናል። ማህበራዊ ግንኙነታቸውም ፍሬአማ ይሆናል። ለዋጃቸው ያላቸው ፍቅር ልቦናቸውን አንድ ያደርገዋል። + +“ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ መሆናችንን ስንገነዘብ፣ የሰጠንን የተስፋ ቃሎች በግዴለሽነት አንናገራቸውም። ተስፋዎቹ በልባችን ውስጥ ይቀጣጠላሉ፣ በከናፍሮቻችንም ላይ ይንቦገቦጋሉ። እግዚአብሔር ሙሴን አላዋቂ፣ ሥነ-ምግባር የጎደለውን እና ዓመፀኛ ሕዝብን እንዲያገለግል በጠራው ጊዜ፡- ‘እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ' ብሎ ተስፋ ሰጠው (ዘፀ. 33:14)። ደግሞም 'በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ' አለው (ዘፀ. 3፡12)። ይህ ተስፋ የክርስቶስ ወኪል ሆነው የተቸገሩትንና የሚሰቃዩትን ለሚያገለግሉ ሁሉ የተሰጠ ነው።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 641 + + + +**የመወያያ ጥያቄዎች** + + +`1. 1 ቆሮ. 13:4–8ን ያንብቡ። 1ኛ ቆሮ. 13 ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን የሚገልጸው እንዴት ነው?` + +`2. በማቴ. 25፡31-46 በጎቹን ከፍየሎቹ የሚለያቸው ምንድን ነው? ኢየሱስ እዚህ ላይ የተናገረውን፣ መዳን በሥራ እንደሆነ በማያስተምር መልኩ፣ እንዴት ልናስተውለው እንችላለን?` + +`3. "እርሱ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን መውደድ ስንችል፣ ያን ጊዜ ለእኛ ያለው ተልዕኮ ይፈፀማል። ለሰማይም ገጣሚዎች እንሆናለን፣ ምክንያቱም በልባችን ውስጥ ሰማይ አለና” የሚለው አባባል ለእርስዎ ምን ማለት ነው? (የሐሙሱን ጥናት ይመልከቱ) ይህ ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ስለ ሰማይ ሁኔታ ምን ይገልጽልናል? የእግዚአብሔርን ፍቅር ለተጨቆኑ ተስፋንና ፍትሕን በሚያመጣ መልኩ በማስፋፋት፣ እንደ ሰማይ ዜጎች መኖር የምንችለው እንዴት ነው?` + +`4. እግዚአብሔር ለፍቅር እና ለፍትሕ ያለውን ተቆርቋሪነት በዙሪያችሁ ላሉ ለማሳየት፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያንዎ ምን ተግባራዊ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው? በማህበረሰባችሁ ውስጥ እየሰራችኋቸው ያሉ መልካም ነገሮች ምንድን ናቸው? ማሻሻልና የበለጠ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ነገሮችስ ምንድን ናቸው? ስለ አምላክ ፍቅርና ፍትሕ የተማርነውን ተግባራዊ ለማድረግ፣ በግልም ሆነ በቡድን ምን ዓይነት ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንችላለን?` \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/13/info.yml b/src/am/ss/2025-01/13/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..98b21eee6a --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/13/info.yml @@ -0,0 +1,4 @@ +--- + title: "ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው" + start_date: "22/03/2026" + end_date: "28/03/2026" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/assets/cover-landscape.png b/src/am/ss/2025-01/assets/cover-landscape.png new file mode 100644 index 0000000000..cd129fa76d Binary files /dev/null and b/src/am/ss/2025-01/assets/cover-landscape.png differ diff --git a/src/am/ss/2025-01/assets/cover-square.png b/src/am/ss/2025-01/assets/cover-square.png new file mode 100644 index 0000000000..a1c7357b0e Binary files /dev/null and b/src/am/ss/2025-01/assets/cover-square.png differ diff --git a/src/am/ss/2025-01/assets/cover.png b/src/am/ss/2025-01/assets/cover.png new file mode 100644 index 0000000000..eb38ff5716 Binary files /dev/null and b/src/am/ss/2025-01/assets/cover.png differ diff --git a/src/am/ss/2025-01/info.yml b/src/am/ss/2025-01/info.yml new file mode 100644 index 0000000000..d7a3b3a561 --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/info.yml @@ -0,0 +1,8 @@ +--- + title: "የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ" + description: "1 ዮሐ. 4:8 እና 16 እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል። መላው መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እውነታ ይመሰክራል። የክርስትና እምነት ማዕከሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ማንነት እምብርት ነው፤ እኛም የምናምነውና የምንሰራው ነገር ሁሉ ማዕከል ፍቅር መሆን አለበት። በዚህ መሠረት ፍቅርን የምንረዳበት መንገድ በእምነታችን እና በድርጊታችን ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።" + human_date: "1ኛ ሩብ ዓመት 2025" + start_date: "28/12/2025" + end_date: "28/03/2026" + color_primary: "#304465" + color_primary_dark: "#032C48" \ No newline at end of file diff --git a/src/am/ss/2025-01/introduction.md b/src/am/ss/2025-01/introduction.md new file mode 100644 index 0000000000..5891b0be0a --- /dev/null +++ b/src/am/ss/2025-01/introduction.md @@ -0,0 +1,23 @@ +### የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ + +1 ዮሐ. 4:8 እና 16 እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላል። መላው መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እውነታ ይመሰክራል። የክርስትና እምነት ማዕከሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ማንነት እምብርት ነው፤ እኛም የምናምነውና የምንሰራው ነገር ሁሉ ማዕከል ፍቅር መሆን አለበት። በዚህ መሠረት ፍቅርን የምንረዳበት መንገድ በእምነታችን እና በድርጊታችን ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል። + +ለምሳሌ አንድ ሰው የእግዚአብሔር ፍቅር በሥራ ይገኛል ብሎ ካመነ፣ ኃጢአተኛና ያልበቃ ስለሆነ እግዚአብሔር እንደማይወደው ሊያስብ ይችላል። ከሌሎችም ጋር ባለው ግንኙነት፣ ሰዎችን ይወዳቸው ዘንድ፣ እነርሱ አስቀድመው መልካም ነገር ማድረግ ይኖረባቸዋል ብሎ ያስባል፡- ይህም ለውድቀት መንስኤ ይሆናል። + +ስለዚህ የእግዚአብሔርን ፍቅር የምንረዳበት መንገድ በእምነታችን እና በልምምዳችን ላይ ትልቅ አንድምታ አለው። ለመሆኑ ፍቅር ምንድን ነው? ፍቅርን እንዲገልጹ አሥር ሰዎችን ቢጠይቋቸው፣ አሥር የተለያዩ ምላሾችን ሊያገኙ ይችላሉ። በክርስቲያኖች መካከል እንኳን፣ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብዙ አፈ-ታሪኮች እና የተሳሳቱ መረዳቶች አሉ። + +ለምሳሌ ክርስቲያኖች ለሚቀጥሉት ጥያቄዎች የተለያዩ ምላሾችን ይሰጣሉ፡ - የእግዚአብሔር ፍቅር መስጠት ብቻ እንጂ ምላሽ አይጠብቅምን? መለኮታዊው ፍቅር ራሱን መስዋዕት የሚያደርግ ብቻ ነው ወይስ እግዚአብሔር በሰዎች ሐሴት ሊያደርግ ይችላል? የእግዚአብሔር ፍቅር ስሜታዊ ነው? በእርግጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይጠነቀቃል? የእግዚአብሔር ፍቅር ቸል ሊባል ወይም ሊገፋ ይችላል? እግዚአብሔር ከፍጡራን ጋር የሰጥቶ መቀበል የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ይገባል? ቁጣ ከፍቅር ጋር አይጣጣምም? ፍቅር እና ፍትሕ እንዴት አብረው ይኖራሉ? እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ፣ ክፋት በዚህ ዓለም ላይ ለምን እጅግ በዛ? ሰዎች እንደ እግዚአብሔር ሊወዱ ይችላሉ? ከሆነ ያ ምን ሊመስል ይችላል? + +ከላይ ለተጠቀሱት ለአንዳንዶቹ ጥያቄዎች የሚሰጡት መልሶች ግልጽ ሊመስሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን ክርስቲያኖች ለመለኮታዊው ፍቅር ያላቸውን አመለካከት አስመልክቶ ብዙ ጊዜ ክርክሮች ይነሳሉ። ግልጽ የሚመስሉ ብዙ ምላሾች በጥልቀት ስንመረምራቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ከሚያስተምረው ጋር የማይጣጣሙ ሆነው ይገኛሉ። + +እነዚህን ጥያቄዎች ሁሉ በአንድ ጊዜ አንፈታቸውም፤ ነገር ግን እነዚህን እና ሌሎች ጥያቄዎችን በዚህ ሩብ አመት እንዳስሳለን። በዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር ከምናስበው በላይ እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን እናያለን። በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተገለጸው የእግዚአብሔር ፍቅር፣ በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን "ስለ ፍቅር" ከሚነገሩ ሃሳቦች እጅግ የላቀ ነው። በሚቀጥሉት ሳምንታት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር የተገለጹትን አንኳር እና ውብ ገጽታዎች በጥልቀት እንመለከታለን። + +ጥናታችንን ስንቀጥልም መለኮታዊው ፍቅር እና ፍትሕ እንዳይነጣጠሉ ሆነው የተጋመዱ መሆናቸውን እናያለን። በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው እግዚአብሔር ፍትሕን ይወዳል (ለምሳሌ፡- ኢሳ. 61፡8ን ይመልከቱ)። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጠው፣ መለኮታዊው ፍቅር እና ፍትሕ ስለማይነጣጠሉ፣ አንዱ ከሌላው ውጭ ሊኖር አይችልም። እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ፣ በዚህ ዓለም ያለው ኢ-ፍትሃዊነትና ስቃይ እጅግ ያሳስበዋል፤ ራሱንም ከተጨቆኑና ከተሰቃዩት ጋር አንድ አድርጎ በመቁጠር፣ ክፋት በፍጥረት ላይ ባመጣው ስቃይና ሀዘን ውስጥ በፈቃዱ ራሱን ሰጠ—ራሱ ከሁሉም በላይ ተሰቃየ። ስለዚህም እግዚአብሔር ራሱ ከሁሉ ይልቅ የክፋት ተጠቂ ሆነ። + +እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ከምንገምተው በላይ ስለሚወድ፣ በክፋት እና በስቃይ በተደጋጋሚ ማዘኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። + +የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር፣ ክርስቶስ በሕዝቡ ላይ፡- “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፣ ዶሮ ጫጩቶቿን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም” እያለ በተናገረው እንጉርጉሮ ውስጥ ማየት ይቻላል (ማቴ. 23፡37)። + +ፍቅር የሆነው የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ፣ ያ ፍቅር ችላ ስለተባለና ስለተገፋ ልቡ እንደተሰበረና እንዳዘነ በቃሉ ውስጥ ተገልጧል። ቃሉ እግዚአብሔር ፍቅሩን በዓለማት ሁሉ ለማስፈን ስላደረገውና እያደረገ ስላለው ነገር ይተርካል። ይህ የዚህ ሩብ ዓመት ትምህርት ርዕስ ነው። + +ጆን ሲ. ፔካም የአድቬንቲስት ሪቪው ተባባሪ አርታኢ ናቸው። ይህ የጥናት መመሪያ በተጻፈበት ጊዜ፣ እሳቸው በአንድርውዝ ዩኒቨርሲቲ በሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ስነመለኮት ሴሚነሪ የነገረ መለኮት እና የክርስቲያን ፍልስፍና ፕሮፌሰር ነበሩ።